Home › Forums › Semonegna Stories › ኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኛዎቹ የታሸጉ ውሃዎች የጥራት ችግር ይታይባቸዋል
- This topic has 1 reply, 2 voices, and was last updated 5 years, 10 months ago by Anonymous.
-
AuthorPosts
-
February 4, 2019 at 8:47 am #9479SemonegnaKeymaster
አዲስ አበባ (ዋልታ)– ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ድርጅቶች የሚመረቱ የታሸጉ ውሃዎች ላይ ሁነኛ የሆነ የጥራት ችግር እንዳለ ተገለፀ።
በአገሪቱ ለመጠጥ ውሃ የሚውሉት የታሸጉ ውሃዎች ላይ በሚታየው የጥራት መጓደል ምክንያትም በኅብረተሰቡ ላይ አሉታዊ የጤና ችግር መንስዔ ከመሆናቸው ባሻገር አገሪቱ ማግኘት ያለባትን ገቢ አለማግኘቷም ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ በውሃ ምርቶች ላይ የሚስተዋሉትን ችግሮችና የጥራት ማስጠበቅ ሥራዎች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ጥር 23 ቀን 2011 ዓ.ም. አካሄዷል።
◌ ቪዲዮ፦ የታሸጉ ውሃዎች በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ የመጣው ፍላጎት እና የውሃዎቹ ያልተመጣጠነ ዋጋ
በመጠጥ ውሃ የፕላስቲክ ማሻጊያዎቹ ክዳን ላይ የሚለጠፉትና ከፍተኛ የውጭ ምናዛሬን የሚጠይቁ ግብዓቶች ተመሳስለው በሀገር ውስጥ የሚሠሩ በመሆኑ የማሸጊያዎችም የምርት ጥራት ላይ ችግር እየተስተዋለ በመሆኑ ይህን ለማስቀረት እየተሠራ ይገኛል።
በሀገሪቱ እየተስፋፉ ያሉ የውሃ ማምረቻ ተቋማት ንፁ ውሃን በማቅረብ እና ኢኮኖሚውን ከመደገፍ አንጻር አበረታታች ሥራ ቢሠሩም አሁንም ግን ዘርፉ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚንስትር ዴኤታ አቶ እሸቱ አስፋው ተናግረዋል።
በርካታ በሀገሪቱ የሚኖሩ ኤምባሲዎችና የውጭ ኮሚኒቲ አካላት የታሸጉ ውሃዎችን ወደ አገር ውስጥ እያስገቡ በመሆኑ፤ በዘርፉ ያለውን የጥራት ችግር ያሳያል።
የምርቶቹን የጥራት ደረጃ በማሻሻል ለውጭ ገበያ እንዲቀርቡ በማድረግ ሀገሪቱን ከዘርፉ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ለማሳደግ መሥራት እንደሚገባ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
የምርቶችን የአመራረት፣ የአስተሻሸግ፣፤ የማጓጓዝ እና የአቀማመጥ ሆነ ለገበያ በሚቀርቡበት ጊዜ ያለው አያያዝ ችግር ምርቶቹን በከፍተኛ ሁኔታ የጥራት ችግር እንዲጋለጡ ማድረጉን ሚኒስትር ዲኤታው አክለው ገልጸዋል።
አሁን በሥራ ላይ የሚገኙ ከ 65 በላይ የታሸጉ ውሃ አምራቾች አለም አቀፉን የጥራት ደረጃ በጠበቀ መልኩ እንዲያመርቱ እየተሠራ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ይልማ መንግስቱ ተናግረዋል።
ምንጭ፦ ዋልታ ሚዲያ / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
——
ሌሎች ዜናዎች፦- ባለፉት 6 ወራት 7ሺህ 8 መቶ ባለቤት አልባ ውሾችን ማስወገዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ
- አዳማ ከተማ ውስጥ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው እና ጥቅም ላይ የማይውሉ መድኃኒቶችን ማስወገጃ ማዕከል ተገነባ
- ኬር ኢትዮጵያ በ7 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ወጭ ያስገነባውን የምርምርና የስልጠና ማዕከል ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አስረከበ
- “ከተሽከርካሪ ፍሰት ነፃ የሆኑ መንገዶች ቀን” – መንገዶችን በወር አንድ ቀን የእግር ጉዞና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረጊያ
- ደኅንነታቸውና ያልተረጋገጠ የስፈተ ወሲብና ጸጉርን ለማሳድግ የሚረዱ እና የከንሰር መድኃኒቶች በህገወጥ መንገድ ሊገቡ ሲሉ ተያዙ
February 10, 2019 at 6:51 am #9617AnonymousInactiveየታሸጉ ውሃዎችና ተግዳሮቶቻቸው
—–የታሸገ ውሃ (ቦትልድ ዋተር) ለመጀመርያ ጊዜ የተመረተው በእንግሊዝ እ.ኤ.አ. በ1621 ነው፡፡ በ17ኛው ክፍለ ዘመን በአሜሪካና በአውሮፓ አገሮች እየተስፋፉ የመጡበት ሁኔታ መኖሩ፣ የታሸገ ውሃ እንደ ፀበል በሽታን ይፈውሳል የሚል እምነት አሳድሮም ነበር፡፡ በኢትዮጵያ የታሸገ ውሃ መጠቀም ከተጀመረ ወደ ሁለት አሠርታት ቢሆንም በፍጥነት እያደገ የመጣ ዘርፍ ነው፡፡
አቶ ደሴ አበጀ የምግብ፣ መጠጥና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የፓኬጂንግ ዳይሬክተር እንደተናገሩት፣ በ2006 ዓ.ም. 33 የነበሩት የውሃ ፋብሪካዎች አሁን ላይ 80 ደርሰዋል፡፡ በሥራ ዕድል ፈጠራው፣ በቴክኖሎጂ ሽግግሩና ኅብረተሰቡን በማርካት ደረጃ ሲታዩ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጠቀሜታም አስገኝተዋል፡፡
በቴክኖሎጂ ሽግግር ረገድ በ1993 ዓ.ም. በትንሽ መሣሪያ ይገለገሉ የነበሩ ፋብሪካዎች፣ በአሁኑ ሰዓት እጅግ ትልልቅና በጣም ውስብስብ የሆኑ የውሃ ማምረቻ መሣሪያዎችን መጠቀም ጀምረዋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ፋብሪካዎችም በብዛት ተገንብተው በሥራ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ከተወሰደው መረጃ ለማወቅ እንደተቻለው፣ ከ100 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ባለበት አገር ውስጥ በቀን ለአንድ ሰው በአማካይ 100 ሚሊ ሊትር የታሸገ ውሃ ይመረታል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ 3.5 ቢሊዮን ጠርሙስ ውሃ እንደሚመረት ይገመታል፡፡ ይህም ፍላጎትን እንደማያሟላ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
የውሃ አምራች ተቋማት እያደጉና እየተስፋፉ ቢመጡም፣ በርካታ ችግሮች እንዳሉባቸው ይነገራል፡፡ ከችግሮቹም መካከል ደረጃ ባለማሟላታቸው የተነሳ የመታሸግ፣ ከተቆጣጣሪ አካላት በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ መሰጠት፣ የብሔራዊ ደረጃን ምልክት ሳይለጥፉ ማምረትና መሸጥ ተጠቃሾ ናቸው፡፡
የማምረቻ ቦታና አካባቢ ንፅህና ደረጃ አናሳ መሆን፣ የታሸገን ውሃ የምርት ደኅንትና ጥራት ሊያጓድሉ ከሚችሉ ነገር ጋር ተቀላቅሎ ማከማቸትና ማጓጓዝ፣ በየሱቁ በታሸጉ ውሃዎች ላይ ኬሚካልና የፍሳሽ ሳሙና ተደርድረው መታየት፣ በሐሩራማና በጣም ከባድ በሆነ ፀሐይ አካባቢ የታሸጉ ውሃዎችን ማከማቸት እየተለመደ መምጣቱ፣ የውሃና የማሸጊያ ማምረቻዎችን በአንድ የሥራ ክፍል ውስጥ ማምረቱ ችግሮች ናቸው፡፡
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.