Home › Forums › Semonegna Stories › የመጀመሪያው የአፍሪካ-ቻይና የንግድ ትርዒት አዲስ አበባ ውስጥ ይካሄዳል
Tagged: CIEC, ECCSA, ዓይናለም ዓባይነህ, የአፍሪካ-ቻይና የንግድ ትርዒት, የኢትዮጵያ ምክር ቤት
- This topic has 1 reply, 2 voices, and was last updated 5 years, 6 months ago by Anonymous.
-
AuthorPosts
-
November 28, 2018 at 8:54 am #8715SemonegnaKeymaster
አዲስ አበባ (ሰሞነኛ)–የአፍሪካን እና የቻይናን የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል ተብሎ የሚጠበቀው የአፍሪካ-ቻይና የንግድ ትርዒት ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ (አዲስ አበባ) ይካሄዳል።
የአፍሪካ-ቻይና የንግድ ትርዒት በመጪው ሳምንት ከኅዳር 24 እስከ 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባ አግዚቢሽን ማዕከል “የቻይና-ኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ አቅም ትብብር ትርዒት” በሚል ርዕስ እንደሚደረግ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት (ECCSA)፣ የኢፌዴሪ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የቻይና ዓለም አቀፍ ንግድ ማስፋፊያ ምክር ቤት (China International Exhibition Center – CIEC) በኅብረት በመሆን ያዘጋጁትን የአፍሪካ-ቻይና የንግድ ትርዒት በተመለከተ በጋራ ጋዜጣዊ መግለቻ የሰጡ ሲሆን፥ ትርዒቱ (Expo) የቻይና የንግድ ኩባንያዎችና በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሠማሩ አካላት በአፍሪካ ካሉ አቻዎቻቸው ጋር የሚኖራቸውን ትስስር ይበልጥ ያጠናክራል ተብሎ ይገመታል ብለዋል። የቻይናው ሲጂቲኤን አፍሪካ (CGTN Africa) እንደዘገበው በቁጥር 29 በሚሆኑ የተለያዩ ዓይነት የኢንዱስትሪ ዘርፎች (sectors) ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች ትርዒቱ ላይ ይሳተፋሉ።
በመግለጫው ላይ እንደተጠቀሰው በቻይና በመሠረተ ልማት፣ በትራንስፖርት ሎጂስቲክስ፣ በጠቅላላ ንግድ፣ በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ የመረጃ ግንኙነት (information communication) ቁሳቁስ፣ ከከባድ እስከ ቀላል የሆኑ የማሽነሪ መሣርያዎች፣ እንዲሁም በኃይል እና አካባቢ ጥበቃ ላይ ያታኮሩ ምርቶችን የሚያመርቱና የሚያቀርቡ ከአርባ በላይ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉበት ተገልጿል።
◌ The 1st China–Africa Expo at Addis Ababa Exhibition Center, Ethiopia
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የቦርድ አባል ዓይናለም ዓባይነህ (ዶ/ር) እንደገለጹት ትርዒቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሔድ ቢሆንም ከአሁን በኋላ በየዓመቱ እንደሚከናወንና የተሳታፊዎችን ቁጥር በመጨመርና በዓይነት በማስፋት እያደገ እንደሚሔድ ገልጸዋል።
የቻይና ዓለም አቀፍ ንግድ ማስፋፊያ ምክር ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሊኡ ዢያን (Liu Jian) በመግለጫቸው እንደተናገሩት፥ ትርዒቱን ስፖንሰር ያደረጉት የቻይና ዓለም አቀፍ ንግድ ማስፋፊያ ምክር ቤት (China Council for the Promotion of International Trade)፣ ከቻይና አፍሪካ ልማት ፈንድ (China-Africa Development Fund) እና ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር ሲሆን፥ የትርዒቱ ዋነኛ ዓላማም በአፍሪካውያን እና በቻይናውያን የንግድ ማኅበረሰብና ግለሰቦች መካከል ጠንካራ ግንኙነት መፍጠር ነው ብለዋል።
ይህንን የአፍሪካ-ቻይና የንግድ ትርዒት በየዓመቱ በቋሚነት ለማከናወን የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና የቻይና ዓለም አቀፍ ንግድ ማስፋፊያ ምክር ቤት የመስማሚያ ሰነድ መፈራረምቸውም ተጠቁሟል። ሁለቱ ተቋማት በሁለቱ ሀገራት የሚገኙ የንግድና ኢንቨስትመንት ተቋማትን ለማገናኘት በሚረዳ መልኩ ከዚህ በፊት የቢዝነስ ፎረሞችን፣ ጉባዔያትን፣ ቢዝነስ-ቱ-ቢዝንስ ቁርኝቶችን (B2Bs) ማድረጋቸውንም የኢትዮጵያው ምክር ቤት አስታውቋል።
May 28, 2019 at 9:26 am #10966AnonymousInactiveኢትዮጵያና ቻይና የኮሙኒኬሽንና ብሮድካስት ሳተላይት በጋራ ለመገንባት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ
—–
ኢትዮጵያና ቻይና የኮሙኒኬሽንና ብሮድካስት ሳተላይት በጋራ ለመገንባት የሚያስችላቸውን ፍሬምወርክ ስምምነት ተፈራረሙ።ስምምነቱን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር ዶክተር ሰለሞን በላይ እና የቻይና ሮኬት ካምፓኒ ምክትል ፕሬዝዳንት ሃን ቺንፒንግ ተፈራርመውታል።
ግንባታው በኢትዮጵያና ቻይና ባለሙያዎች ትብብር የሚከናወን ሲሆን÷ 50 በመቶ የሀገር ውስጥ እሴት እንደሚጠቀም ነው የተገለጸው።
በግንባታው የሚሳተፉ ኢትዮጵውያን ከቻይና የቴክኖሎጂ ልምዱን ይወስዳሉ ነው የተባለው።
ተጠቃሚ መለየት፣ ማስተባበር፣ ፍላጎትና ቦታ መረጣ የመሳሰሉት ተግባራት ሰኔ ወር ላይ ይጀመራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የአሁኑ የሳተላይት ግንባታ ፍሬምወርክ ስምምነት ሳተላይትን የስራ እድል መፍጠሪያና ሃብት ማመንጫ ማድረግን ታሳቢ ያዳረገ እንደሆነ ነው የተገለጸው።
በሁለቱ ሀገራት ትብብር የተሰራችው የመጀመሪያዋ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ህዳር 20 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ህዋ ትላካላች ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው ከኢፌዴሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው።
ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.