Home › Forums › Semonegna Stories › የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ መቋቋሙን ተከትሎ ወደ ተግባር ለመግባት የመዋቅርና የሕግ ማዕቀፍ ሥራን አጠናቀቀ
- This topic has 2 replies, 2 voices, and was last updated 5 years, 11 months ago by Anonymous.
-
AuthorPosts
-
January 5, 2019 at 8:34 pm #9112SemonegnaKeymaster
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በቅርቡ ሥራውን በይፋ የሚጀምርበት በዳያስፖራው ማህበረሰብ እና በባለድርሻ አካላት ዘንድ ተልዕኮው በግልፅ ታዉቆ በጋራ እና በቅንጅት ሥራው እንደሚሰራ መገለጹን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመልክታል።
አዲስ አበባ (ሰሞነኛ)– የኢትዮጵያውያንን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን አገራዊ ተሳትፎ ለማረጋገጥና መብታቸውን ለማስከበር በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስር የተቋቋመው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ሥራ ለመጀመር የመዋቅርና የሕግ ማዕቀፍ ሥራን ማጠናቀቁን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት እና ምክትል ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እንድሪስ ታህሳስ 26 ቀን 2011 ዓ.ም. ለአገር ውስጥ እና ለዉጭ አገር መገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ የመዋቅርና የሕግ ማዕቀፍ ሥራን ማጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡ የኤጀንሲው ወደ ሥራ መግባት ዳያስፖራው በአገሩ ጉዳይ ብርቱ ተዋናይ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።
በዉጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን መብትና ጥቅሞችን ለማስጠበቅ የዳያስፖራ ምዝገባ እና መረጃ አያያዝ ስርዓት መዘርጋት፣ ዳያስፖራው በዕውቀትና በተክኖሎጂ ሽግግር አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ማስቻል እንዲሁም በኢንቨስትመንት፣ በንግድና በቱሪዝም ተሳትፎውን ማጎልበት የኤጀንሲው ዋና ዓላማዎች መሆናቸውን አስረድተዋል።
ኤጀንሲው በቅርቡ ሥራውን በይፋ የሚጀምርበት በዳያስፖራው ማህበረሰብ እና በባለድርሻ አካላት ዘንድ ተልዕኮው በግልፅ ታዉቆ በጋራ እና በቅንጅት ሥራው እንደሚሰራ መገለጹን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመልክታል።
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህን ኤጀንሲ ለማቋቋም የወሰነው በጳጉሜን ወር 2010 ዓ.ም. ሲሆን፥ በዚያን ጊዜ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በትውልድ ሀገራቸው እድገት ላይ የራሳቸውን አስተዋጽዖ ለማድረግ ከምን ጊዜውም በበለጠ እንደተነሳሱ ገልጸው ነበር።
በተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከሦስት እስከ አምስት ሚሊዮን እንደሚገመትና ከእነዚህም ውስጥ አብዛኛዎቹ በሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ እንደሚኖሩ ዘገባዎች ያመለክታሉ። እ.ኤ.አ ከ2009 በፊት ኢትዮጵያ ከእነዚህ የዳያስፖራ አባላት የምታገኘው ገቢ (remittance) ከ400 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በታች እንደነበረና ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ይህ አሀዝ እየጨመረ መምጣቱ ተጠቁሟል።
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች ወደ ትውልድ ሀገራቸው የሚልኩት የገንዘብ መጠን ከአራት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ እንደሆነና ይህም ሀገሪቱ ከወጪ ንግድ (ኤክስፖርት) ከምታገኘው ገቢ ጋር ሲነጻጸር በአንድ ቢሊዮን ዶላር አካባቢ ብልጫ አለው።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
February 16, 2019 at 4:59 pm #9738AnonymousInactiveበአሜሪካ ሀገር የሚኖሩ የዲያሥፖራ ማህበር አባላት ስልጠና ሰጡ።
—–በውጪ አገራት ዩኒቨርስቲዎች የሚያስተምሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሙሁራንና ተመራማሪዎች /TASFA/ በሚል ተደራጅተው ስልጠና እየሰጡ ይገኛሉ።
ከ 08-10/06/2011 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ በአዲስ አበባ ከተማ ኦሮሞ ባህል አደራሽ የኢፌዲሪ የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ የውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚንስቴር፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የህግ ባለሙያዎች እና ከኦሮሚያ ትምህርት፣ ሲቢል ሰርቪስ እና ከተለያዩ ቢሮዎች ለሚሰሩ አመራሮችና ባለሙያዎች የፕሮጀክት ማኔጅሜት ስልጠና በመስጠት ላይ ናቸው።
ፕሮግራሙን የከፈቱት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት የሳይንስና አካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል ዶክተር ኤባ ሚጃና እያንዳንዳችን ያስተማረችንን ድሀ አገራችንን አቅማችን በፈቀደው ብድሯን ለመመለስ ተረባርበን መስራት አለብን ብለዋል።
የማህበሩ አመራሮችና አባላትም በበኩላቸው በራሳቸው ፈቃድና ወጭ መጥተው ያለባቸውን የሙያ ግዴታ ለመወጣት እየሰሩ ሲሆን ይሄን ተግባር በማስፍት ስልጠናው በቴክኖጂ ታግዞ ኦንላይን ትምህርት ጭምር እንደሚሰጥ 1000 ሰልጣኞች ለማሰልጠን ከመንግስት ጋር በመተባበር በታቀደው መሰረትየዛሬው ለ4ኛ ዙር 400 ሰልጣኞች ናቸው ቀጣይም በተመሳሳይ እንሰራለን ማለታቸውን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘግቧል፡፡
February 17, 2019 at 7:25 pm #9760AnonymousInactiveውክልናን በቪድዮ፡ የውክልና ሂደትን በ20 ደቂቃ
—–ኬብሮን ነዋሪነቱ በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ሲሆን ኢትዮጵያ ለሚገኙ ወዳጅ ዘመዶቹ ውክልና ለመስጠት አስቦ ሂደቱን በአሜሪካን ሃገር ቢጀምርም ነገሮች እንዳሰባቸው ቀላል ሆነው አላገኛቸውም። በዚህ ምክንያት የተነሳም የውክልና አሰጣጥ ሥርዓቱን ለመቀየር ቆርጬ ተነሳሁ ይላል፤ ኬብሮን ።
እንዳለውም አደረገው። የውክልና ሥርዓቱን በማዘመን የሚወስደውን ጊዜ ከወራት ወደ ደቂቃዎች ለማሳጠር ችሏል። እንዴት?
ኬብሮን ደጀኔ ‘ሲሊከን ቫሊ’ በመባል የሚታወቀው የአሜሪካ ቴክኖሎጂ እምብርት ውስጥ ‘ቪዲቸር’ የሚባል ድርጅት ካቋቋመ አምስት ዓመት ሊሆነው ነው። አሁን ደግሞ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን የውልና ማስረጃን አሠራር ለማፋጠን ትልቅ ሚና ለመጫወት በቅቷል።
በዛሬው ዕለት በ’ቪዲቸር’ የተደገፈው የውክልና አሠራር በዋሺንግተን ዲሲ ባለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተመርቋል። ለሕዝብ አገልግሎትም ሥራ ላይ እንዲውል ይፋ ተደርጓል።
የተጓተተ የውክልና ሂደት
ከሁለት ዓመት በፊት ነበር ከውክልና አሠራር ጋር ኬብሮን ግብ ግብ የገጠመው። በኢትዮጵያ ያለን የንግድ ተቋም ዘመድ እንዲያንቀሳቅስለት በማሰብ የውክልና ሂደቱን ቢጀምርም በካሊፎርኒያና በአካባቢው ውክልና የሚጽፍለትም ሆነ የሚያረጋግጥለት ማግኘት ሳይችል ቀረ። ከስድሰት ሰዓታት የአየር ጉዞ በኋላ በዋሽንግተን ዲሲ ሂደቱን አስጀመረ። ውክልና የመስጠት ተግባሩ ግን ቀላል አልነበረም።
11 የተለያዩ ነገሮችን ማሟላት ይጠይቅ እንደነበር እንዲሁም በሕግ ባለሙያ አረጋግጦ ቢያንስ 40 ቀናት መጠበቅ ግድ እንሆነ ይናገራል። ከስንት ወጣ ውረድ በኋላ ኢትዮጵያ የደረሰው የውክልና ወረቀት ስህተት አለበት በመባሉ በድጋሚ ለማሠራት መገደዱንም ኬብሮን ይናገራል።
እንደዚህ ዓይነት ችግሮች መኖራቸውን ከዚህ ቀደም ከብዙ ሰዎች ይሰማ የነበረ ቢሆንም በእርሱ ላይ ከደረሰበት በኋላ አሠራሩን ለመቀየር ቆርጦ እንደተነሳ ይናገራል። በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ‘ቪዲቸር’ መካከል በተደረሰው ስምምነት መሰረት የውልና ማስረጃን አሠራር ለመቀየርና ‘ዲጂታላይዝ’ ወይም ‘አውቶሜት’ ለማድረግም ‘ቪዲቸር’ ለተሰኘው የኬብሮን ተቋም ፈቃድ ተሰጠ።
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.