የዓለም የውሃ ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ ተከበረ።

Home Forums Semonegna Stories የዓለም የውሃ ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ ተከበረ።

Viewing 2 posts - 1 through 2 (of 2 total)
  • Author
    Posts
  • #10359
    Semonegna
    Keymaster

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ)– የዓለም የውሃ ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ መጋቢት 13 ቀን 2011 ዓ.ም. “ማንንም ባለመተው” (“Leaving no one behind”) በሚል መሪ ቃል ተከብሯል። የዓለም የውሃ ቀን በዓለም አቀፍ ለ27ኛ ጊዜ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ26ኛ ጊዜ የተከበረ ሲሆን፥ በሥነ ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር፣ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴርና ሌሎች ተቋማት ተዎካዮችና የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

    በበዓሉ መርሀግብር ላይ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት የሚተገበር የሁለተኛው ዋን ዋሽ ብሔራዊ መርሃ ግብር (One WASH National Program) ይፋ መደረጉን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

    የሁለተኛው ዋን ዋሽ ብሔራዊ መርሃ የገጠር፣ የከተማና የተቋማት ንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ ንጽሕና እና የጤና ንጽሕና አጠባበቅ (water, sanitation and hygiene) የሚያካትትና በሀገር አቀፍ (ብሔራዊ) ደረጃ የሚተገበር፣ የመጠጥ ውሃ፣ሳኒቴሽንና ሃይጅንን በገጠር፣ በከተማ፣ በት/ቤቶችና በጤና ጣቢያዎች ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን የሚረዳ እንደሆነ ተገልጿል።

    ● SEMONEGNA on Social Media: FacebookTwitterInstagramPinterest

    ይህ መርሀግብር (ፕሮግራም) በውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ በትምህርት ሚኒስቴር፣ በጤና ሚኒስቴር፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር፣ በልማት አጋር አካላትና በህብረተሰቡ ቅንጅት የሚተገበር ነው።

    የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ ዋን ዋሽ መርሀግብር (One WASH Program) በዓለም አቀፍ ደረጃ ለየት ያለ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ እየተተገበረ ያለ ፕሮግራም መሆኑን ጠቁመው፥ መንግሥት፣ የልማት አጋሮችና ሕብረተሰቡ አንድ ላይ ሀብት በማሰባሰብና ወደ አንድ ቋት በማስገባት፣ አንድ ላይ በማቀድ፣ አንድ ላይ አፈጻጸሙን በመከታተልና በመገምገም፣ አንድ ላይ ሪፖርትም በማድረግ የሚፈጸም ፕሮግራም መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።

    የመጀመሪያው የዋን ዋሽ ፕሮግራም ባለፉት አራት ዓመታት ከስድስት ወራት ሲተገበር መቆየቱን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታው፥ ሁለተኛው የዋን ዋሽ ፕሮግራም ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ትግበራ እንደሚገባና የአምስት ዓመታት ፕሮግራም መሆኑን ተናግረዋል። በመጀመሪያው ፕሮግራም 3ነጥብ6 ሚሊየን ሰዎችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን፥ 90 በመቶ ያህል ተግባራዊ መደረጉ ነው የተገለጸው። በሚቀጥሉት ወራትም እቅዱን በመቶ በመቶ ለማካናዎን እንደሚሰራ ተጠቁሟል።

    ሁተለኛው ዋሽ በመጀመሪያው የዋን ዋሽ ፕሮግራም ይተገበር ከነበረው በገጠርና በከተማ፣ በጤና ተቋማትና በት/ቤቶች የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽንን ለህብረተሰቡ ከማቅረብ በተጨማሪ ለድርቅ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚተገበረውን ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የመጠጥ ውሃ ፕሮግራም (Climate Resilient WASH) የተካተተበት እንደሆነ ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ ተናግረዋል።

    በሁለተኛው የዋን ዋሽ ፕሮግራም ከመንግሥት፣ ከልማት አጋሮች፣ ከህብረተሰቡ ቀጥተኛ ተሳትፎ፣ በአነስተኛ ወለድና በረጅም ጊዜ ክፍያ የሚከፈል ብድር ከአበዳሪ ተቋማት በጠቅላላው 6.5 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሀብት ተሰባስቦ ለፕሮግራሙ ማስተግበሪያ ይውላል ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታው በመግለጫቸው።

    ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    የዓለም የውሃ ቀን


    #10442
    Anonymous
    Inactive

    የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ አንድ ቋት ዋሽ አካውንት ፕሮግራምን ተቀላቀለ
    —–

    የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (KOICA) የዋን ዋሽ ብሔራዊ ፕሮግራም አካል የሆነውን አንድ ቋት ዋሽ አካውንት (Consolidated WASH Account) ፕሮግራም ተቀላቀለ።

    የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (KOICA) ላለፉት በርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን፤ በመስኖ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ህብረተሰብን ተጠቃሚ በሚያደርጉ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።
    ኤጀንሲው በመደበኛ ፕሮግራሙ ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጨማሪ ከ2012 በጀት ዓመት ጀምሮ በሚከናወነው የሁለተኛው ዙር አንድ ቋት ዋሽ አካውንት (Consolidated WASH Account) ፕሮግራም በመቀላቀል ፕሮግራሙን ለመደገፍ 10 (አሥር) ሚሊን ዶላር የድጋፍ ስምምነትን የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ዳይሬክተር የሆኑ ሚስተር ዶንግ ሆ ኪም እና የውሃ ፤ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ መጋቢት 18/2011 ዓ.ም ተፈራርመዋል።

    የሁለቱ ሀገራት የረጅም ዘመናት ትብብር ይበልጥ እየተጠናከረ መምጣቱን ሚኒስቴር ዴኤታው በማስታወስ ከዚህ ከተመደበው በጀት ውስጥ 7 ሚለዮን ዶላር ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት እና ቀሪው 3 ሚሊዮን ዶላር ኮይካ ከዚህ በፊት የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በሚያከናውንባቸው አከባቢዎች የገጠር ሳኒቴሽንን ሽፋን ለማሳደግ የሚውል በጀት መሆኑን አስረድተዋል።

    ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

Viewing 2 posts - 1 through 2 (of 2 total)
  • You must be logged in to reply to this topic.