Home › Forums › Semonegna Stories › ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በዘንድሮ የትምህርት ዘመን 1ሺህ 500 ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረገ ነው
Tagged: ጂንካ ዩኒቨርሲቲ, ገብሬ ሌንቲሶ, ገብሬ ይንቲሶ
- This topic has 3 replies, 2 voices, and was last updated 5 years, 10 months ago by Anonymous.
-
AuthorPosts
-
October 20, 2018 at 5:53 pm #8176SemonegnaKeymaster
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ እስካሁን ድረስ በ14 የትምህርት ክፍሎችን በመክፈት ተማሪዎችን እያስተማረ መሆኑንና የኒቨርሲቲው የትምህርት ክፍሎቹን ወደ 41 ለማሳደግ ዕቅድ ይዞ እየሠራ መሆኑንም የኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ተናግረዋል።
ጂንካ፣ ደቡብ ኦሞ ዞን (ዋልታ) – ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን 1ሺ 500 አዳዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ገብሬ ይንቲሶ ለዋልታ እንደገለጹት በዘንድሮ የበጀት ዓመት እና የትምህርት ዘመን የተማሪዎችን ቅበላ የተሳካ ለማድረግ በሁለት ዘርፍ የተከፈሉ ዝግጅቶች እየተካሄዱ ይገኛሉ።
የኒቨርሲቲው የዘንድሮ ዓመትን የመማርና ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር የመምህራን ዝግጅትን ጨምሮ የተማሪዎች የአገልግሎት መስጪያ ተቋማት የሆኑት ቤተ መጽሐፍትና የመመዝገቢያ ሥፍራዎች በቴክኖሎጂ የታገዙ እንዲሆኑ የማስቻል ሥራዎች ተከናውነዋል ብለዋል ፕሬዚደንቱ።
በጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች አገልግሎት መስጪያ ህንጻዎች ግንባታ መዘግየታቸውን የገለጹት ፕሮፌሰር ገብሬ አዳዲስ ተማሪዎችን በጊዚያዊ የመጠሊያ ህንጻዎች እንዲገቡ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል። የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የዘንድሮ ዓመት የተማሪዎች የመግቢያ ቀንም እስካሁን አለመቆረጡን ፕሬዚደንቱ አያይዘው ገልጸዋል።
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ እስካሁን ድረስ በ14 የትምህርት ክፍሎችን በመክፈት ተማሪዎችን እያስተማረ መሆኑንና የኒቨርሲቲው የትምህርት ክፍሎቹን ወደ 41 ለማሳደግ ዕቅድ ይዞ እየሠራ መሆኑንም ፕሬዚደንቱ አብራርተዋል።
አዳዲስ የሚከፈቱት የትምህርት ዘርፎችም በደቡብ ኦሞ ዞን የሚታዩ የሙያ ክፍተቶችን ለመሙላት በሚያስችል መልኩ የሚከፈቱ መሆኑም ተገልጿል።
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ዓመት 1ሺህ 100 ያህል ተማሪዎችን የተቀበለ ሲሆን በዘንድሮ ዓመት 1ሺ500 አዳዲስ ተማሪዎችን በመቀበል በአጠቃላይ ተማሪዎችን 2ሺህ 600 ለማድረስ እየሠራ ይገኛል።
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል (ደብብሕክ)፣ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ጂንካ የሚገኘው ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በ2010 ዓ.ም. በትምህርት ሚኒስቴር ስር ከተከፈቱት 11 አዳዲስ የሕዝብ ዩኒቨርሲቲዎች (public universities) አንዱ ነው።
ምንጭ፦ ዋልታ
ተመሳሳይ ዜናዎች፦
- የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻሉን አሳወቀ
- የወንዶ ገነት ኮሌጅ ከ400ሺ በላይ ሀገር በቀል የዛፍ ችግኞችን ለኅብረተሰቡ አከፋፈለ
- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከ41 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ለማስተናገድ መዘጋጀቱን አስታወቀ
- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ከ37 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ ለሠራተኞቹ ያስገነባቸውን ቤቶች አስረከበ
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአርሶ አደሩን ሕይወት ለመቀየር እያከናወነ ያለው በምርምር የታገዘ የዘር ማባዛት ተግባር
- የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በትምህርት ጥራትና ለኅብረተሰቡ ንጹህ ውሃ ለማቅረብ እየሠራ ነው
- ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ እና ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና በሶስተኛ ዲግሪዎች በርካታ መርሀ ግብሮችን ከፈቱ
December 18, 2018 at 9:45 pm #8972AnonymousInactiveJinka University:
===============
Jinka University received 1212 first year students on 8th and 9th of December 2018. Classes were supposed to start after an official welcome ceremony on the 10th of December and this is to be followed by orientation, departmental placement, and registration scheduled to take place until 13 December 2018.Read more: https://tinyurl.com/y7wqk3ho
December 18, 2018 at 10:40 pm #8977AnonymousInactiveጂንካ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተገንብተው በ2010 ዓ.ም. ወደ ሥራ ከገቡት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ምንም እንኳን ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል።
ዩኒቨርሲቲው በማኅበረሰብ-አቀፍ አገልግሎት (community-based service) በደቡብ ኦሞ ዞን ውስጥ ለሚገኙ 18 ሁለተኛ ደረጃ እና አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በጥቅሉ ለ19 ትምህርት ቤቶች 510 ኮምፒዩተሮችን ከአንድ ደርጅት እንዲሁም በውጭ ሀገር ከሚኖር አንድ የአካባቢው ተወላጅ ጋር በመተባበር ለእያንዳንዳቸው ሃያ አምስት፣ ሃያ አምስት ኮምቲዩተሮችን ለትምህርት ቤቶቹ የሰጠ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕ/ር ገብሬ ይንቲሶ ገልጸዋል።
Read more: bit.ly/2PKUi2R
December 18, 2018 at 10:41 pm #8978AnonymousInactiveጂንካ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተገንብተው በ2010 ዓ.ም. ወደ ሥራ ከገቡት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ምንም እንኳን ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል።
ዩኒቨርሲቲው በማኅበረሰብ-አቀፍ አገልግሎት (community-based service) በደቡብ ኦሞ ዞን ውስጥ ለሚገኙ 18 ሁለተኛ ደረጃ እና አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በጥቅሉ ለ19 ትምህርት ቤቶች 510 ኮምፒዩተሮችን ከአንድ ደርጅት እንዲሁም በውጭ ሀገር ከሚኖር አንድ የአካባቢው ተወላጅ ጋር በመተባበር ለእያንዳንዳቸው ሃያ አምስት፣ ሃያ አምስት ኮምቲዩተሮችን ለትምህርት ቤቶቹ የሰጠ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕ/ር ገብሬ ይንቲሶ ገልጸዋል።
Read more: bit.ly/2PKUi2R
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.