Home › Forums › Semonegna Stories › ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በኪነ ህንፃ ትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ
Tagged: ሙሉቀን አዳነ, ኪነ ህንፃ, ደሳለኝ መንገሻ, ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ, ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
- This topic has 1 reply, 2 voices, and was last updated 5 years, 10 months ago by Semonegna.
-
AuthorPosts
-
February 17, 2019 at 7:48 pm #9765AnonymousInactive
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በኪነ ህንፃ ሲያስመርቅ ዘንድሮ ለሦስተኛ ጊዜ ሲሆን፥ ዘንድሮ የተመረቁት 18 ወንዶችና 16 ሴቶች በአጠቃላይ 34 የኪነ ህንፃ ሙያተኞች መሆናቸውን በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።
ጎንደር (ሰሞነኛ)–የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለአምስት ዓመት ተኩል በኪነ ህንፃ ትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ቅዳሜ፥ የካቲት 9 ቀን 2011 ዓ.ም. በባችለር ዲግሪ (BSc in Architecture) አስመረቀ።
በምረቃ ሥነ ስርአቱ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ያስተላለፉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ፥ ዩኒቨርሲቲው በኪነ ህንፃ የትምህርት ዘርፍ ዘንድሮ ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑን ገልፀዋል።
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት በቴክኖሎጂ የትምህርት መስኮች ከ5 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያሰለጠነ እንደሚገኝ የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፥ ቅዳሜ ዕለት የተመረቁት 18 ወንዶችና 16 ሴቶች በአጠቃላይ 34 የኪነ ህንፃ ሙያተኞችም በሀገራችን የሚታየውን የህንፃ ጥበብ ችግር ለማስተካከልም ሆነ በሙያው የሚታየውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ለመቅረፍ እንዲተጉ አሳስበዋል።
◌ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ማሰገንቢያ የሚውል አስር ሚሊዮን ብር ለገሰ
የጎንደር ከተማ ም/ከንቲባ ዶ/ር ሙሉቀን አዳነ በምርቃቱ ሥነ ስርዓት ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው የተመራቂዎቹ የምርቃት ዕለት የልጅነት ዘመን አብቅቶ ለሀገር ብቁ የሆነ የኪነ ህንፃ ባለሙያ የሚሆኑበት ዕለት እንደሆነ አስገንዝበዋል። ከዚህ በኋላም ተመራቂዎቹ ሀገሪቱ ለረዥም ዓመታት የምትጠራበትና የምትታወስበትን የኪነ ህንፃ ጥበብ እንደሚያበረክቱ እምነታቸውን ገልፀዋል።
ተመራቂዎቹም በሙያቸው ሀገራቸውን ለማገልገል የገቡትን ቃል ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ከዩኒቨርሲቲው ዜና ጋር በተያያዘ የዩኒቨርሲቲው ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የማኔጅመንትና የህዝብ አስተዳደር ት/ቤት “በወቅታዊ የፖለቲካ ለውጥ ዘላቂነት ላይ የምሁራን ሚና” (‘The Role of Academicians in Sustaining the Current Political Reforms’) በሚል ርዕስ ዙሪያ ከካቲት 6 እስከ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. ኮንፈረንስ አካሂዷል።
በዕለቱ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ፣ በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት አማካሪ ዶ/ር አምባቸው መኮንን፣ የጎንደር ከተማ ም/ከንቲባ ዶ/ር ሙሉቀን አዳነ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ፖለቲከኛ ፕ/ር መረራ ጉዲና፣ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ ደራሲና የታሪክ ተመራማሪው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የጎንደር ከተማ የልማትና የሰላም ሸንጎ አባላት የዩኒቨርሲቲው ም/ፕሬዚዳንቶች፣ ዲኖች፣ መምህራን፣ ተማሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ምንጮች፦ ፋና ብሮድካስቲንግ እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
——
ሌሎች ዜናዎች፦- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለስድስት ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ
- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የኮምፒዩተር ድጋፍ አደረገ
- ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ የመጣው የማኅበረሰብ አገልግሎቱ
- የአርሲ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ4ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 388 የህክምናና የጤና ተማሪዎች አስመረቀ
- በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነው የቀጠና/ወረዳ ጤና መረጃ ስርዓት አካዳሚ (DHIS2) በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተከፈተ
February 23, 2019 at 6:17 pm #9848SemonegnaKeymasterድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሲያስተምር የቆያቸውን የህክምና ት/ቤት ዕጩ ዶክተር ምሩቃንን እና የአርክቴክቸር ት/ክፍል ዕጬ ምሩቃንን በዛሬው እለት የካቱት 16/2011 ዓ.ም በደማቅ ሥነስርዓት አስመረቀ።
-
AuthorPosts
- You must be logged in to reply to this topic.