Semonegna

Forum Replies Created

Viewing 12 posts - 121 through 132 (of 132 total)
  • Author
    Posts
  • Semonegna
    Keymaster

    በቪክቶሪያ እና አልበርት ሙዚየም የሚገኙ የመቅደላ ስብስብ ቅርሶች በአጭር ጊዜ ሊመለሱ ይችላሉ
    —–

    ለንደን የሚገኙ ቅርሶች የሚያዙበት ሁኔታና የሚተዳደሩበት ሕግ በጣም ጠንካራ ነው። በየትኛውም አጋጣሚ እጃቸው ላይ የገባ ቅርስ በሕጉ መሠረት ይተዳደራል። ስለሆነም የእኛም ቅርሶች የዚሁ አካል ናቸው ማለት ነው። ይሁን እንጂ እነዚህ ቅርሶች ለኢትዮጵያውያን የማንነትና የእድገት መሠረቶች ናቸውና ሊመለሱልን እንደሚገባ በተደጋጋሚ ሲጠየቁ ቆይተዋል።

    እ.ኤ.አ በ2018 ከወደ ቪክቶሪያ እና አልበርት ሙዚየም ብቅ ያለው መረጃ በረጅም ጊዜ ውሰት ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ማድረግ እንደሚቻል ገለጸ። የማንን ቅርስ ማን አበዳሪ? ማንስ ተበዳሪ? እንዴት አይነት ድፍረት ነው?ወዘተ… ብለን ተቆጨን። እነሆ የይመለሱልን የሕዝብ ጥያቄው በክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው (የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር)፣ በልዑካን ቡድኑና በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ቅርሶቹ ተጎበኙ፤ ጥያቄውም ቀረበ ሰፊ ውይይትም ተደረገ። ዳይሬክተሩ ዶ/ር ትሪስትራም ኸንት /Tristram Hunt/ ጥያቄው ተገቢ መሆኑን ‘ውሰት’ የሚለው ቃልም ለኢትዮጵያውያን ከባድ መሆኑን እንደተረዱት በመግለጽ የተቸገሩት የሕግ ጉዳይ በመሆኑና ምላሽ ለመስጠት ያለን አማራጭ ይህ ብቻ ስለሆነ ነው አሉ። አክለውም ያለን አማራጭ ይህን ቀዳዳ በመጠቀም ሊስተካከሉ የሚችሉ አባባሎችን ተጠቅመን የሚመለሱበትን ሁኔታ መፍጠር ይህን ካላደረግን ግን በሕጉ ላይ ጸንተን ወደፊት የሚሆነውን ነገር መመልከት ይኖርብናል ብለዋል። በመቀጠልም ከክብርት ሚንስትሯም የተለያዩ ማሳመኛ ምክንያቶች ከቀረቡ በኋላ በሙዚየሙ፣ በኤምባሲውና በሚንስቴር መሥሪያ ቤቱ በኩል ጊዜ ሳይሰጠው በአስቸኳይ መግባቢያ ሰነዱን ካለው ሕግ ጋር በማይጋጭና የኢትዮጵያን ጥያቄ ሊመልስ በሚችልበት ሁኔታ ሠርተን በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት እልባት እንደሚያገኝ ዳይሬክተሩ ገልጸው ስምምነት ላይ ተደርሷል።

    በፈጣንና ታታሪ አመራሮችና ባለሙያዎች የተደራጀው ኤምባሲም ባለው ሙሉ አቅምና ጊዜ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በመወጣት ቅርሶቹ ወደ አገራቸው እንዲገቡ እንደሚያደርጉ ሃላፊነቱን መቀበላቸውን ክቡር አምባሳደሩ ፍሰሃ ሻወል ገልጸዋል።

    ምንጭ፦ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር

    Semonegna
    Keymaster

    “የሠራዊቱ ሁኔታ ከፍተኛ የህሊና መረበሽ ውስጥ ከቶኛል” አቶ ነአምን ዘለቀ
    —–

    ላለፉት 26 ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎ ሲያደርጉ የቆዩት የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ከፍተኛ አመራርና ሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ ነአምን ዘለቀ ከፓርቲ መልቀቃቸውን ተከትሎ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

    ቢቢሲ፡ የአርበኞች ግንቦት 7 የሠራዊ አባላት አሁን ያሉበት ሁኔታ ትንሽ ያስጨነቀዎት ይመስላል። ግን ደግሞ ለመልቀቅ ከወሰኑ ቆይተዋል፤ እርስዎም በጽሑፍዎ እንደጠቀሱት። እና ዝም ብሎ ከመውጣት፣ መልቀቅዎን ከአንድ ጉዳይ ጋ ሆን ብለው ለማያያዝ የሞከሩ ይመስላል።

    አቶ ነአምን፡ (ዘለግ ካለ ሳቅ በኋላ) ምን እላለሁ እንግዲህ። አንተ የመሰልህን (ማሰብ ትችላለህ). . .። መጀመሪያ (ከጽሑፌ) አንተ ይሄን ብቻ ነጥለህ ለምን እንዳወጣኽው አላወቅኩም። እዚያ ላይ ሠራዊቱን በሚመለከት የተደረገው ጥረት በዝርዝር ተቀምጧል። እስካሁን ድረስ እነኚህ የሠራዊት አባላት በከፍተኛ ችግር ላይ ነው ያሉት፤ ላለፉት ሰባት ወራት።

    መንግሥት የእነርሱን ጉዳይ በተደረገው ስምምነት መሠረት (ማለትም) ቶሎ በሁለትና በሦስት ወር ውስጥ መልሰው ይቋቋማሉ፣ ድጎማ ይሰጣቸዋል አለ፤ የጀርመን መንግሥት ገንዘብ ለመስጠት ቃል ገባ፤ ነገር ግን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት የተቋቋመው ቢሮ ምንም አቅም ስላልነበረው እስካሁን ድረስ ሲጓተት ቆይቶ አሁን ገና ወደ ኮሚሽን ጉዳዩ ተመርቶ ያው ኮሚሽኑ ኃላፊነት ተሰጥቶት በብሔራዊ አደጋ መከላከል ኮሚሽን በኩል የእነርሱ ጉዳይ እንዲካሄድ ነው እየተደረገ ያለው።

    ቢቢሲ፡ ለመሆኑ የሠራዊቱን አባላት በአካል አግኝተዋቸዋል?

    ሙሉውን ቢቢሲ አማርኛ ላይ ያንብቡ

    Semonegna
    Keymaster

    የሕክምና መሣሪያዎችን በሀገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ
    —–

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ)– የሕክምና መሣሪያዎችን በሀገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል ስምምነት መጋቢት 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ተፈረመ።
    ስምምነቱ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር፣ በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ፥ በጤና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን መካከል ነው የተፈረመው።
    ስምምነቱ በሀገሪቱ ያለውን የሕክምና መሳሪዎችን ፍላጎት ለማሟላትና ለግዢ የሚወጣውን የውጪ ምንዛሪ ለመቀነስ ያስችላል።

    ምንጭ፦ የጤና ሚኒስቴር / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    Semonegna
    Keymaster

    ወሎ ዩኒቨርሲቲ በሥነ-ህንጻ ተማሪዎችን አስመረቀ
    —–

    ወሎ ዩኒቨርሲቲ፥ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለ5 ዓመት ተኩል በሥነ-ህንጻ (አርክቴክቸር) የትምህርት መስክ ያስተማራቸውን 20 ተማሪዎች መጋቢት 7 ቀን 2011 ዓ.ም. አስመረቀ።

    ምንጭ፦ ወሎ ዩኒቨርሲቲ

    Semonegna
    Keymaster

    የህንድ መንግስት በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት ለ3,500 ኢትዮጵያውያን ነጻ የትምህርት ዕድል ይሰጣል
    —–

    የህንድ መንግስት እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ2019 ብቻ ለ3ሺህ500 ያህል ኢትዮጵያውያን ነጻ የትምህርት ዕድል ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ።

    ‘ስተዲ ኢን ኢንዲያ’ (Study in India) በተሰኘው ተቋም አማካኝነት የሚሰጠው የትምህርት ዕድል የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠናን ያካተተ እንደሚሆን ታውቋል።

    የህንድ መንግስት በሚሰጠው ነጻ የትምህርት ዕድል ከመላው አፍሪካ ተጠቃሚ የሚሆኑ ዜጎች ቁጥር ከ20 ሺህ የሚልቅ እንደሆነ ‘ስተዲ ኢን ኢንዲያ’ አስታውቋል።

    ትምህርትና ስልጠና የሚሰጥባቸው መስኮች በርካታ ሲሆኑ የህክምና ዘርፍን የማያካትት መሆኑ ተገልጿል።

    በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኑራግ ስሪቫስታቫ እንደገለጹት፤ የህንድ መንግስት ለአፍሪካ አገሮች እየሰጠውን ያለው የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠና አጠናክሮ የማስቀጠል ፍላጎት አለው።

    አክለውም ተቋሙ አጫጭር ስልጠናዎችን በማዘጋጀትና ነጻ የትምህርት እድል ሲሰጥ የቆየ መሆኑን ገልጸው አሁን ደግሞ በፊት ይሰጠው የነበረውን ቁጥር በማስፋትና ረጅም ስልጠናዎችንም ለመስጠት ማሰቡን ገልጸዋል።

    38 ሺ ኮሌጆችና 800 ዩኒቨርሲቲዎች ያሏት ህንድ በትምህርት ተቋማት ብዛትና የትምህርት እድሎችንም በማመቻቸት ረገድ ትታወቃለች።

    ምንጭ፦ ኢዜአ

    Semonegna
    Keymaster

    የድሬዳዋ ከንቲባ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ
    —–

    የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኢብራሂም ዑስማን ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ ለከተማ አስተዳደሩ ያቀረቡት ጥያቄ በምክር ቤቱ ተቀባይነት አገኘ።

    የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶሕዴፓ) አባል የሆኑት አቶ ኢብራሂም ለሦስት ዓመታት ከመንፈቅ በከንቲባነት ያገለገሉ ሲሆን፣ በተደጋጋሚ በሚደረጉ ሠልፎች ተቃውሞ ይቀርብባቸው ነበር።

    ምክር ቤቱ በምትካቸው አቶ መሐዲ ዲሬን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ በማድረግ ሹሟል።

    ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ

    Semonegna
    Keymaster

    በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ እና በሞናኮ ኢንስቲትዩት (Institut de Paléontologie Humaine, Fondation Prince Albert Ier de Monaco) መካከል በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ።
    —–

    ስምምነቱን የድሬዳዋ ከንቲባና የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ኢብራሂም ኡስማን እና የኢንስቲትዩቱ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ሄነሪ ዲ ሉምሌይ (Henry de Lumley) ፈርመዋል ።

    ስምምነቱ ለዩኒቨርስቲው መምህራንና ተማሪዎች የሁለተኛና የሦስተኛ ዲግሪ የትምህርት ዕድልና አጫጭር ስልጠናዎችን የሚያስገኝ ነው ተብሏል።

    በተጨማሪም ስምምነቱ የምርምር ሥራዎችን በጋራ ለመሥራት ዕድል የሚፈጥር ሲሆን በዋናነት በጂኦሎጂና በቅድመ ታሪክ ጥናት ላይ ያተኮረ እንደሚሆን በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል ።

    ከንቲባ ኢብራሂም ኡስማን የስምምነቱ መፈረም በድሬዳዋና በአካባቢው ቅድመ ታሪክ ላይ ጥናትና ምርምር ለማድረግ እድል ከመፍጠሩም ባሻገር ዩኒቨርሲቲውን በሰው ሀይል ለማጠናከር ትልቅ እገዛ ይኖረዋል ሲሉ በፊርማ ስነስርአቱ ወቅት ተናግረዋል።

    ምንጭ፦ የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት

    in reply to: የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተመረቀ #10014
    Semonegna
    Keymaster

    የደብረብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድና በኬንያው ፕሬዝዳንት ዑሁሩ ኬንያታ ተመረቀ
    —–

    የደብረብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድና በኬንያው ፕሬዝዳንት ዑሁሩ ኬንያታ ተመረቀ። የኢንዱስትሪ ፓርኩ ግንባታው በ2009ዓ.ም ነበር በ75 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጭ የተጀመረው፡፡ የኢንዱስትሪ ፓርኩ 8 ሼዶች ያሉት ሆኖ በ75 ሄክታር መሬት ላይ አርፏል።

    የኢንዱስትሪ ፓርኩ ከደብረ ብርሃን ከተማ 6 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።

    ምንጭ፦ የአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት

    Semonegna
    Keymaster

    ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሲያስተምር የቆያቸውን የህክምና ት/ቤት ዕጩ ዶክተር ምሩቃንን እና የአርክቴክቸር ት/ክፍል ዕጬ ምሩቃንን በዛሬው እለት የካቱት 16/2011 ዓ.ም በደማቅ ሥነስርዓት አስመረቀ።
    Dire Dawa University

    Semonegna
    Keymaster

    ምክትል ከንቲባው የራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቀጥል የመፍትሔ አማራጭ አስቀመጡ
    —–
    የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ከራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ከወ/ሪት ሳምራዊት ፍቅሩ ጋር በመወያየት፣ ራይድ የጀመረው ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠናክሮ መቀጠል በሚችልበት አማራጭ መፍትሔ ዙሪያ መከሩ።
    ሪፖርተር: https://www.ethiopianreporter.com/article/13863

    Semonegna
    Keymaster

    ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በቁጥጥር ስር ውለው ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ነው
    ****************************************************

    የቀድሞ የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በቁጥጥር ስር ዋሉ።

    ከኮርፖሬሽኑ አሰራር ጋር በተያያዘ በወንጀል ተጠርጣሪ የሆኑት የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በምዕራባዊ ትግራይ በኩል ባታር በተሰኘው አካባቢ ነው በህብረተሰቡ እና በመከላከያ ኃይል ትብብር የተያዙት።

    በአሁኑ ሰዓትም ወደ አዲስ አበባ ተይዘው እየመጡ ነው።

    በትናንትናው እለት የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ከፍተኛ የገንዘብ ምዝበራ በመፈፀማቸው የተጠረጠሩ 27 ከፍተኛ የሜቴክ አመራሮች እና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ማስታወቁን ሪፖርተራችን አብዲ ከማል ከስፍራው ዘግቧል።

    Semonegna
    Keymaster

    የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት የሚሰጥበት ጊዜ ተራዘመ

    የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት የሚሰጥበት ቀን መራዘሙን የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታወቀ።

    ክትባቱ በኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎች በጥቅምት ወር እና ከስድስት ወራት በኋላ ደግሞ ለሁለተኛ ዙር ሊሰጥ ታቅዶ ነበር። በቢሮው የክትባት መርሃ ግብር የቴክኒክ አማካሪ አቶ ሙሉጌታ አድማሱ እንደገለፁት ለክትባት የሚሆነው መድሃኒት በመዘግየቱ ምክንያት ክትባት የሚሰጥበት ቀን ወደ ህዳር 5/2011 ዓ.ም ተራዝሟል።

    በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚሰጠው የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዉጤታማነት በአማራ ክልል በሁሉም ዞኖች እና ወረዳዎች ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱንም አቶ ሙሉጌታ ነግረውናል። ከጤና ጥበቃ ቢሮ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው በክልሉ ከ4 መቶ 50 ሺህ በላይ ልጃገረዶች ክትባቱን ይወስዳሉ። እድሜያቸው 14 ዓመት የሆናቸው ልጃገረዶች ብቻ የክትባቱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ለማወቅ ተችሏል።

    የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት እድሜያቸው ከ9 እስከ 14 ዓመት የሆናቸው ልጃገረዶችን የግብረ ስጋ ግንኙነት ከመፈጸማቸው በፊት ከበሽታው ለመከላከል ሲባል በዓለማቀፍ ደረጃ ይሰጣል። ይሁን እንጅ በኢትዮጵያ ደረጃ ለሁሉም ልጃገረዶች የሚበቃ መድኃኒት ገዝቶ ማቅረብ ባለመቻሉ ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑት ላይ ክትባቱ እንደሚሰጥ ጤና ጥበቃ ቢሮው ገልጿል።

Viewing 12 posts - 121 through 132 (of 132 total)