-
Search Results
-
አዲስ አበባ (ኢዜአ)፦ መንግሥት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአገራቸው ልማት ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዲሆኑ እያደረገ ያለውን ሁሉን አቀፍ ጥሪ ከግምት ያስገባ አዲስ አቅጣጫ እየቀየሰ መሆኑን የኢትዮጵያ የዲያስፖራ ማኅበር አስታወቀ።
አገሪቱ የጀመረችውን የለውጥ ሥራ ለማገዝ፣ እንደዚሁም በውጭ የሚኖረው ዜጋ በሌሎችም አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ለማስቻል ማህበሩ አደረጃጀቱን መልሶ በማዋቀር ላይ ነው ተብሏል።
በሽርክና ወይንም በሌላ መንገድ በመደራጀት በአገሪቱ የልማት እድገት ውስጥ የራሳቸውን አሻራ ለማሳረፍ ዝግጁ መሆናቸውን ኢትዮጵያዊያን የዲያስፖራ አባላት ገልፀዋል።
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መዋዕለ ንዋያቸውን በማቀናጀት አገር ውስጥ መሥራት የሚሹ ከሆነ መንግሥት የተለየ ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ መስከረም 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዳማ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ ባስተለላፉት መልዕክት፤ በውጭ የመኖሩ ኢትዮጵያዊያን በአገሪቱ ልማት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።
በተለይም በስቶክ ማርኬት ወይንም በአክሲዮን ንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራ አባላት በተናጠልም ሆነ በመደራጀት ወደ አገራቸው ተመልሰው በልማት እንዲሰመሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል።
ያላቸውን እውቀትና ገንዘብ በማደራጀት መቅረብ ለሚችሉ የዲያስፖራ አባላት መንግሥት የተለየ ድጋፍ እንደሚያቀርብ ነው ዶ/ር አብይ ያረጋገጡት።
ቪድዮ፦ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች ሀገር ውስጥ ለመሥራት ያላቸው ፍላጎት እና የሚያጋጥማቸው የቢሮክራሲ ችግር
ኢትዮጵያዊያኑ ዲያስፖራዎች በበኩላቸው መንግሥት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እያደረገ ያለውን ጥሪ በአዎንታዊ መልኩ እንደሚመለከቱት ገልጸዋል።
በዚህም በተለይም በሽርክና ወይንም በሌላ መንገድ በመደራጀት በአገሪቱ የልማት እድገት ውስጥ የራሳቸውን አሻራ ለማሳረፍ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በተደራጀ አግባብ ከጓደኞቻቸው ጋር ተነጋግረው ትልቅ ካምፓኒ ይዘው ለመምጣት ሃሳብ እንዳላቸው የተናገሩት በውጭ የሚኖሩት ወይዘሮ አማኒ መሃመድ ናቸው።
“የሥራ ሁኔታ እየተመቻቸ ነው፤ ሁሉም ሰው እውቀቱንና ገንዘቡን ኢንቨስት በማድረግ የአገሪቱን እድገት ለማረጋገጥ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ መልካም ነው። እኔም እንደ አንድ ውጭ አገር እንደሚኖር ዜጋ ወደ ሃገሬ መጥቼ ለመሥራት ትልቅ እቅድ ይዤ እንደምመጣ ተስፋ አደርጋለሁ” ያሉት ደግሞ አቶ አማን አህመድ ናቸው።
የኢትዮጵያ የዲያስፖራ ማኅበር ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ስዩም በበኩላቸው ማኅበራቸው ከሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ጋር በመሆን የዲያስፖራውን የልማት ተሳትፎ ለማሳደግ እየሠራ ነው።
በተለይ ደግሞ በኢንደዱትሪ ፓርኮች ላይ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሊኖራቸው የሚችለውን ተሳትፎ ለማጎልበት ፓርኮቹን የሚጎበኙበት ሁኔታ እየተመቻቸ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህም ዲያስፖራው ስለ ፓርኮቹ በቂ መረጃ እንዲኖረው ትልቅ እድል እንደሚከፍት ገልጸው ማኅበሩ መረጃ ከመስጠቱ ሥራ ጎን ለጎን ሌሎች የውጭ ዜጎችም በዘርፉ እንዲሰማሩ የበኩሉን ጥረት ያደርጋል ብለዋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ)
Topic: የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተመረቀ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያስገነባው የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የግንባታ ሥራው የተጀመረው በጥቅምት ወር 2009 ዓ.ም ሲሆን የቻይናው ግዙፍ ኩባንያ ቻይና ሲቪል እንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ግንባታውን ሲያከናውን ነበር።
አዳማ (Semonegna) – በኦሮሚያ ክልል፣ አዳማ ከተማ የተገነባው የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በዛሬው ዕለት (መስከረም 27 ቀን 2011 ዓ.ም.) ተመርቋል። በምርቃቱ ስነ ስርዓት ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ለማ መገርሳ፣ የአማራ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የእንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ እና የኮርፖሬሽኑዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ት ሌሊሴ ነሜ እንዲሁም ሌሎች የክልልና የፌደራል ባለስልጣናት ከፍተኛ ተገኝተዋል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያስገነባው የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የግንባታ ሥራው የተጀመረው በጥቅምት ወር 2009 ዓ.ም ሲሆን የቻይናው ግዙፍ ኩባንያ ቻይና ሲቪል እንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (China Civil Engineering Construction Corporation/ CCCC) ግንባታውን ሲያከናውን ነበር።
ከአዲስ አበበ ከተማ 99 ኪሎ ሜትሮች ርቆ የሚገኘው የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተለያየ ዘርፍ ለሚሰማሩ አምራች ኩባንያዎች የሚያገለግሉ በአጠቃላይ 19 (በዝርዝር፦ ስድስት 11 ሺህ ካሬ ሜትር፣ ዘጠኝ 5 ሺህ 500 ካሬ ሜትር፣ አራቱ ደግሞ በ3 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፉ) የመሥሪያ ጠለላዎች ወይም የመሥሪያ ቦታዎችን (shades) የያዘ ነው። የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአጠቃላይ ሊለማ ከታቀደው 2 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ በመጀመሪያው ዙር ልማት 354 ሄክታር መሬት የሚይዝ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለምቶ ለዛሬ ምረቃ የበቃው በ100 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባው ክፍል መሆኑን፣ ይህም ግንባታ 4.1 ቢልዮን ብር መፍጀቱን፣ እንዲሁም ፓርኩ በመጀመሪያው ምዕራፍ በሙሉ አቅም ወደ ምርት ሲገባ እስከ 25 ሺህ ለሚደርሱ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ወ/ት ሌሊሴ ነሜ በምረቃው ንግግራቸው ላይ አስታውቀዋል።
◌ RELATED: A visit to Hawassa Industrial Park by Dire Dawa Industrial Park & City’s Administration people
የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተመርቆ ሥራ መጀመር በሀገሪቱ ወደማምረት የገቡ የኢንዱስትሪ ፓርክኮች ቁጥር ወደ አምስት የሚያሳድገው ሲሆን፥ ከሌሎቹ አራቱ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለየት የሚያደርገው ፓርኩ ያለበት ከተማ (አዳማ) በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ አስተዋጽዖ ያመጣል ተብሎ የታመነበተና አምና ሥራ የጀመረው የአዲስ አበባ-ጅቡቲ የባቡር መስመር በሚያልፍባት የአዳማ ከተማ መገኘቱ ነው። ይህ የባቡር መስመርና የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ እርስ በርሳቸው ጉልህ የሆነ የጥቅም ግንኙነት ይኖራቸዋል ተብሎ ይታመናል። ከዚህ በተጨማሪ የኢንዱስትሪ ፓሩኩ በከተማ ከሚገኘው የአዳማ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ጋር በማምረት ዘርፍ እና በመማር፣ ማስተማርና ምርምር ዘርፎች መካከል ቁልፍ የሆነ ግንኙነት ይፈጥራሉ ይጠበቃል።
የሀገሪቱ የማኑፋክቸሪንግ ሴክተር (manufacturing sector) ከኢትዮጵያ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) መጠን አራት ነጥብ አምስት በመቶ (4.5%) ድርሻ ብቻ የሚሸፍን ሲሆን፥ መንግስት እስከ 2022 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ይህን አናሳ ድርሻ ወደ ሀያሁለት በመቶ (22%) ለማሳደግ አቅዳለች። ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ እስከ 2025 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) አሁን ያሏትን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ቁጥር ከአምስት ወደ ሀያ አምስት የማሳደግ ዕቅድ አላት። በያዝነው ዓመት ስድስት የኢንዱስትሪ ፓርኮች (ድሬ ዳዋ፣ ቂሊንጦ II፣ ቦሌ ለሚ II፣ ጅማ፣ ባህር ዳር እና ደብረ ብርሃን) ግንባታቸው ተጠናቆ ወደምርት ተግባር እንደሚገቡ ዶክተር አርከበ ዕቁባይ አስታውቀዋል።
በኢትዮጵያ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የጤናውን ዘርፍ ለማገዝ የተሰራችው ሰው አልባ አውሮፕላን (drone) ከቢሾፍቱ አየር ኃይል ወደ አዳማ ከተማ የተሳካ በረራ አድርጋለች።
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሰው አልባ አውሮፕላንን በመጠቀም የህክምና መሣርያዎችን እና መድኃኒቶችን ለማጓጓዝ የሚያስችል ስምምነትም ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ በ6 ጣቢያዎች 24 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም እስከ 5ኪ.ግ. የህክምና ቁሳቁሶችንና መድኃኒቶችን ለማድረስ የሚያስችል ነው።
ስምምነቱን የተፈራረሙት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስተር ጌታሁን መኩርያ (ዶ/ር ኢንጂ.) እና የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን ናቸው።የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጌታሁን መኩርያ (ዶ/ር ኢንጂ.) ሰው አልባ አውሮፕላንኗ በሳይንስና ቴክኖሎጂ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዞች መሠራቷን ጠቅሰው ለሳይንስና ቴክኖሎጂ መዳበር የበለጠ አስተዋጽዖ ሊያደርጉ የሚችሉ የሙያ ማኅበራትንና ወጣት የፈጠራ ባለሙያዎችን በመደገፍ በቀጣይ መሰል ቴክኖሎጂዎች ሽግግር ዙርያ ከቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዞች ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።
ምንጭ፦ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
በኦሮሚያ ውስጥ ከፍተኛ ተቃውሞን ቀስቅሶ የነበረው አዲስ አበባን በዙሪያዋ ካሉ የኦሮሚያ ከተሞች ጋር ያስተሳስራል የተባለው ማስተር ፕላን ተራማጅና አንድ ቀን ተመልሶ ይመጣል ብለው እንደሚያስቡ ኦህዴድ ሊቀ መንበር እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ኩማ ደመቅሳ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ባለፈው ሳምንት ኦዴፓ (የቀድሞው ኦህዴድ) በጅማ ከተማ ድርጅታዊ ጉባኤውን ባደረገበት ወቅት ተሳታፊ የነበሩት አቶ ኩማ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ አወዛጋቢ ስለነበሩና እርሳቸው በከፍተኛ የስልጣን ሃላፊነት ላይ በነበሩበት ጊዜ ስለታቀዱና ተግባራዊ ስለተደረጉ ጉዳዮች ምላሽ ሰጥተዋል።
«ኦሮሞ እና አማራን የሚነጣጥሉ አይሳካላቸውም»
በተለይ በኦሮሚያ ውስጥ ተቀስቅሶ ለረጅም ጊዜ ለዘለቀው ሕዝባዊ ተቃውሞ መነሻ ምክንያት እንደሆነ የሚነገርለትና ከ2006 ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የነበረው የአዲስ አበባና በዙሪያዋ ያሉ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጀ ማስተር ፕላንን በተመለከተ የተሳሳተ አመለካከት እንዳለ ተናግረዋል።
ጉዳዩ ከመፈናቀል ጋር አብሮ ስለመጣ እንጂ «ተራማጅ አስተሳሰብ ነው ብዬ አስባለሁ» በማለት የሚናገሩት አቶ ኩማ፤ ጊዜ ሊወስድ ይችላል እንጂ ማስተር ፕላኑ አንድ ቀን ተመልሶ ይመጣል ብለው እንደሚያስቡ ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በተመሳሳይ ኦሮሚያ ውስጥ ለጠንካራ ጥያቄና ተቃውሞ ምክያት የነበረው የአዳማ ከተማን የኦሮሚያ ክልል መዲና እንድትሆንና የክልሉ መስሪያ ቤቶች ወደዚያው እንዲዘዋወሩ መደረጋቸው ይጠቀሳል።
ስለዚህ ጉዳይ የተጠየቁት አቶ ኩማ ውሳኔው ስህተት እነደሌለበት ያምናሉ። አሁንም ወደኋላ መለስ ብለው ሲመለከቱ «አሁንም ያኔ የነበረኝ አቋም ስህተት ነው ብዬ አላምንም» ካሉ በኋላ፤ «አዳማ የክልሉ ዋና ከተማ ሆና እንደተቀየረች ብትዘልቅ ኖሮ ከተማዋ ታድግ እንደነበር» ሲሉ ገልጸዋል።
ማንበብዎን ይቀጥሉ፦ «ማስተር ፕላኑ ተመልሶ ይመጣል» አቶ ኩማ ደመቅሳ