በቤንሻንጉል ጉሙዝ በተፈጠረ ግጭት ከ70 ሺህ ሰዎች በላይ ሲፈናቀሉ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ተሰማ

Home Forums Semonegna Stories በቤንሻንጉል ጉሙዝ በተፈጠረ ግጭት ከ70 ሺህ ሰዎች በላይ ሲፈናቀሉ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ተሰማ

Viewing 1 post (of 1 total)
  • Author
    Posts
  • #7837
    Semonegna
    Keymaster

    ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ በተፈጠረ ግጭት ከ70 ሺህ ሰዎች በላይ ሲፈናቀሉ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ተሰማ (BBC News Amharic)

    መስከረም 16/2011 ዓ.ም የካማሼ ዞን (ቤንሻንጉል ጉሙዝ – ኦሮሚያ አዋሳኝ ላይ ያለ ዞን) አመራሮች ከምዕራብ ኦሮሚያ አስተዳደር ጥምር ኮሚቴ ጋር የነበራቸውን ስብሰባ አጠናቅቀው እየተመለሱ በነበሩ የዞን፣ የወረዳ አመራሮችና የፀጥታ ኃይሎች ላይ በተከፈተው ተኩስ የ4 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በተወሰኑ ከኦሮሚያ ጋር በሚዋሰኑ ስፍራዎች በተከሰተ ግጭት ሰዎች መሞታቸውን፣ መፈናቀላቸውን ቤቶች መቃጠላቸውን የቤንሻንጉል ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አበራ ባይታ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

    በተለይ በበሎይ ጅጋንፎይ ወረዳ ስር ሳይ ዳለቻ ቀበሌ ግጭት የነበረ ሲሆን በግጭቱም 75 ቤቶች ተቃጥለዋል ብለዋል። በዚሁ ወረዳ ጅጋንፎይ ቀበሌ በጭበጭ በምትባል አካባቢ ላይ ቤቶች መቃጠላቸውን ጠቅሰው ሌሎች ቀበሌዎችም ላይ ተመሳሳይ ግጭቶች መከሰሰታቸውን ተናግረዋል።

    በበሎይ ጅጋንፎ ሶቤይ ከተማ ላይ በርካታ ሰዎች ተፈናቅለዋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ በሶጌ ዙሪያ ባሉ ቀበሌዎች ልቢጋ፣ ሳይ ዳላቻ፣ ታንካራ ቀበሌዎች በርካታ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን አስረድተዋል።

    ቤንሻንጉል ጉሙዝ

    “በተንካራ 105 ቤቶች ተቃጥለዋል 3 ሰዎችም ህይወታቸው አልፏል” ያሉት መስተዳድሩ በበጭበጭ 1 ሰው መሞቱንና አንገርባጃ ቀበሌ 2 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው አስረድተዋል። እንደ ክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ገለፃ ወደ ኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ እና በስጋት ምክንያት ወደ ጫካ የገቡ ሰዎች ያሉ ሲሆን ቁጥራቸው ምን ያህል ነው የሚለውን ግን የተጠናቀረ መረጃ የለኝም በማለት ሳይናገሩ ቀርተዋል።

    የተፈናቀሉት ሰዎች ከቤንሻንጉል ብቻ ሳይሆን ክልሉን ከሚያዋስኑት የኦሮሚያ ቀበሌዎችም እንደሆነ የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ሳስጋ ወረዳ ዱራበሎ፣ ካምፕ፣ በሎበሬዳ፣ ስምንተኛ ከሚባሉት ቀበሌዎች በስጋት ምክንያት ወደ ነቀምትና በሎበሬዳ ወደሚገኙ ማዕከሎች ተፈናቅለው እንደሚገኙ ተናግረዋል።

    የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ የሆኑት አቶ ታከለ ቶሎሳ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በቤንሻንጉል ክልል የኦሮሚያ አዋሳኝ ቀበሌዎች በተከሰተው ግጭት 12 ሰዎች ሲሞቱ 14 ሰዎች እንደቆሰሉ የነገሩን ቢሆንም አሁን ግን የሟቾች ቁጥር 23 መድረሱን ገልፀውልናል። ከዚህ በተጨማሪም ከ70 በላይ የሚሆኑ የቀንድ ከብቶች እንደተወሰዱባቸውም ጨምረው ተናግረዋል።

    ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በሳስጋ ወረዳ ጤና ጣቢያና በነቀምት ሆስፒታል ህክምና እያገኙ መሆናቸውን ገልፀዋል።

    እንደ ኃላፊው ገለፃ ከሆነ ቀያቸውን ጥለው ወደ ኦሮሚያ የተሰደዱ ሰዎች ቁጥር 50 ሺህ ደርሷል ያሉን ቢሆንም አሁን ግን የተፈናቃዮቹ ቁጥር ከ70 ሺህ በላይ እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እነዚህ ሰዎች የተፈናቀሉት ከበሎይ ጅጋንፎና ያሶ ሲሆን ከኦሮሚያ አዋሳኝ ወረዳዎች ደግሞ ሀሮ ሊሙ፣ ሶጌና ሳስጋ አካባቢዎች ነው።

    ማንበብዎን ይቀጥሉ፦ በቤንሻንጉል ጉምዝ በተፈጠረ ግጭት ከ70 ሺህ ሰዎች በላይ ሲፈናቀሉ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ተሰማ

Viewing 1 post (of 1 total)
  • You must be logged in to reply to this topic.