የኢትዮጵያን ሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ የሚገመግም ሰነድ ቀረበ

Home Forums Semonegna Stories የኢትዮጵያን ሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ የሚገመግም ሰነድ ቀረበ

Viewing 1 post (of 1 total)
  • Author
    Posts
  • #7901
    Semonegna
    Keymaster

    የኢትዮጵያን ሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ የሚገመግም ሰነድ በተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተጠናቅሮ ቀረበ። በየአራት ዓመቱ በሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት መድረክ ላይ ኢትዮጵያ ለሦስተኛ ጊዜ ተሳታፊ ሆና ትቀርባለች።

    አቅራቢ፦ ጽዮን ግርማ (ቪኦኤ አማርኛ)

    ዋሽንግተን ዲሲ፦ በየአራት ዓመቱ ለሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት የአገራት የሰብዓዊ መብት መገማገሚያ መድረክ ላይ የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ ለመገምገም የሚያስችል ሰነድ ቀረበ። ሰነዱን ካቀረቡት የዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ታዋቂ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ውስጥ፤ ሲቪከስ (CIVICUS)፣ ሲፒጄ (CPJ)፣ ዲፌንድ ዲፌንደርስ (Defend Defenders)፣ አርቲክል 19 (Article 19)፣ አክሰስ ናው (Access Now)፣ ፔን ኢንተርናሽናል (PEN International) እና የኢትዮጵያ የመብት ድርጅቶች ኅብረት (ኢመድህ) ይገኙበታል።

    በየአራት ዓመቱ በሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት (United Nations Human Rights Council/UNHRC) መድረክ ላይ ኢትዮጵያ ለሦስተኛ ጊዜ ተሳታፊ ሆና ትቀርባለች። በዚህ ጉባዔ ላይ ውይይት የሚደረገው ከ197 በላይ የዓለም ሀገሮች መካከል ሲሆን ሀገራቱ የሰብዓዊ መብት አያያዛቸውን በሚመለከት ሪፖርት የሚያቀርቡበት እንዲሁም የሚቀርብባቸውን ወቀሳና ትችት አዳምጠው የሚያሳሽሉትን “አሻሽላለሁ” የሚሉበት ያልተስማሙበትን ደግሞ ያልተስማሙበትን ምክንያት የሚያስረዱበት ስብሰባ ነው።

    ሀገራቱ እንዲያሻሽሉ የሚነገራቸውና ምክረ ሀሳብ የሚቀርበው በሰብዓዊ መብት ዙሪያ የሚሠሩ ድርጅቶች አጠናቅረው በሚያቀርቡት ሪፖርት መሠረት ነው። ከዚያም ከአራት ዓመት በኋላ ሲመለሱ አሻሽለው እንደሆነ ወይም ደግሞ የባሰ ሁኔታ ተፈጥሮ እንደሆነ ይጠየቃሉ።

    ከአራት ዓመት በኋላ ዘንድሮ ለሚደረገው ሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ ሪፖርትም ዘጠኝ የሚሆኑ ድርጅቶች ኢትዮጵያን የተመለከተ ሰነድ አደራጅተው አቅርበዋል። በዚህ ሰነድ ውስጥ ኢትዮጵያ መሻሻል አሳይታበታለች የተባለው ተጠቅሷል። በቀጣይ ልታሻሽል ይገባታል የተባለውም በምክረ ሀሳብ ሰፍሯል።

    ከእነዚህ ድርጅቶች ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያን የሚመሩት (የኢመድህ ዳይሬክተር) አቶ ያሬድ ኃይለማርያም ስለሰነዱ ተጠይቀዋል።

    በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ ሪፖርት ሙሉውን እዚህ ጋር ማንበብ ይችላሉ

    ቃለምልልሱን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ

    ምንጭ፦ ቪኦኤ አማርኛ

    About the Association for Human Rights in Ethiopia (AHRE)

    Association for Human Rights in Ethiopia (AHRE) is a non-governmental, non-partisan, and not-for-profit organization dedicated to the advancement of human rights protection in Ethiopia by providing support to the work of Ethiopian Human Rights Defenders and performing advocacy and other related tasks that cannot be carried out effectively by human rights organizations based in Ethiopia because of administrative and legal restrictions, security risks and resource constraints.

    ሰብዓዊ መብት

Viewing 1 post (of 1 total)
  • You must be logged in to reply to this topic.