ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአርሶ አደሩን ሕይወት ለመቀየር እያከናወነ ያለው በምርምር የታገዘ የዘር ማባዛት ተግባር

Home Forums Semonegna Stories ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአርሶ አደሩን ሕይወት ለመቀየር እያከናወነ ያለው በምርምር የታገዘ የዘር ማባዛት ተግባር

Viewing 1 post (of 1 total)
  • Author
    Posts
  • #8029
    Semonegna
    Keymaster

    ወደ 300 የሚጠጉ አባላት ያሉት ‹ንጋት› የዘር ብዜትና መሰረታዊ ሁለገብ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ማኅበር በ14 ሺህ ብር ካፒታል ሥራውን ጀምሮ የተለያየ ዓይነት ዝርያ ያላቸውን ዘሮች በማባዛት ሌሎች አባል ያልሆኑ አርሶአደሮች የምርጥ ዘር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እያበረከተ ይገኛል። በአሁኑ ሰዓት 700 ሺህ ብር ካፒታል የደረሰው ማኅበሩ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በምርምር የታገዘ ድጋፍ ይደረግለታል።

    ጎንደር (ጎዩ) – ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ዘርፎች የማህበረሰብ አገልግሎትን እየሰጠ የሚገኝ አንጋፋ የትምህርትና የምርምር ተቋም ነው።

    ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር እና ምርምር ሥራ ባሻገር፥ የተለያዩ የህክምና አገልግሎቶችን በመስጠጥ፣ የጤና በለሙያዎችን በማሰልጠን፣ ልዩ ልዩ የቁሳቁስ ድጋፍ በመስጠት፣ ለኅብረተሰቡ የስልጠና እና የልምድ ልውውጥ ዕድሎችን በማመቻቸት መጠነ-ሰፊ የማኅበረሰብ አገልግሎቶችን እያከናወነ ይገኛል።

    በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በግብርናና ገጠር ትራንስፎርሜሽን ኮሌጅ የገጠር ልማትና ሰብል ስርፀት ትምህርት ክፍል ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ድጋፍና ክትትል እያደረገላቸው ከሚገኙት ማኅበራት ‹ንጋት› የዘር ብዜትና መሰረታዊ ሁለገብ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ማኅበር አንዱ ነው። ማኅበሩ በማዕከላዊ ጎንደር ወገራ ወረዳ ደብር ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን በ2002 ዓ.ም በኦክስፋምና በአመልድ ሁለት ድርጅቶች ትብብር የተመሠረተ መሆኑን ከተለያዩ ማኅበሩ ከመዘገባቸው ማስረጃዎች (ዶክዩሜንቶች) ማረጋገጥ ተችሏል።

    ወደ 300 የሚጠጉ አባላት ያሉት ‹ንጋት› የዘር ብዜትና መሰረታዊ ሁለገብ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ማኅበር በ14 ሺህ ብር ካፒታል ሥራውን ጀምሮ የተለያየ ዓይነት ዝርያ ያላቸውን ዘሮች በማባዛት ሌሎች አባል ያልሆኑ አርሶአደሮች የምርጥ ዘር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እያበረከተ ይገኛል። በአሁኑ ሰዓት 700 ሺህ ብር ካፒታል የደረሰው ማኅበሩ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በምርምር የታገዘ ድጋፍ እየተደረገለት መሆኑን በአካል ማረጋገጥ ተችሏል።

    በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ዳይሬክተሮች፣ የሥራ ኃላፊዎችና የጋዜጠኞች አባላት ያሉት ቡድን በወገራ ወረዳ ደብር ቀበሌ ማኅበሩ እያከናወነ ያለውን ተግባር መስከረም 24/2011 ዓ.ም ጎብኝቷል። በጉብኝቱ በተለያዩ የአርሶ አደሮች ማሳ ላይ በመዘዋወር በቢራ ገብስ ላይ እየተካሄደ ያለውን የዘር ማባዛት ሂደት ተመልክቷል። በተጨማሪም ማኅበሩ ያካሄደውን ዓመታዊ ርፖርትና ግምገማ ቡድኑ አዳምጧል።

    በመጨረሻም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በግብርናና ገጠር ትራንስፎርሜሽን ኮሌጅ የገጠር ልማትና ሰብል ስርፀት ትምህርት ክፍል መምህርና የተቀናጀ የዘር ዘርፍ ልማት ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ በየነ ደርሶና የዕፀዋት ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህርና የፕሮግራሙ አባል አቶ ዳንኤል ታደሰ በቀረበው ሪፖርት የማጠቃለያ አስተያየት ሰጥተው ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

    ዘገባ፡-በላይ መስፍን፣ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (ጎዩ)

    ጎንደር ዩኒቨርሲቲ

Viewing 1 post (of 1 total)
  • You must be logged in to reply to this topic.