NEAEA: Grade 12 national examination result will be announced until August 1

ADDIS ABABA (ENA)–The National Educational Assessment and Examinations Agency (NEAEA) announced that the Grade 12 national examination result will be announced to students before 1st August 2018, the Ethiopian News Agency (ENA) reported on Monday 23rd July 2018.

According to NEAEA’s Director-General Ato Araya Gebregziabher disclosure to ENA, the Agency has already made grading the examinations and other necessary preparation so as to make the announcement of the results to students by August 1, 2018.

Furthermore, Ato Araya said that the Grade 10 national examination result well also be announced right after the Grade 12 national examination result announcement in one month time, that is, until August 31, 2018.

SCHOLARSHIPS: Opportunities for Ethiopian student to study abroad

The Grade 12 national examination, which Ethiopian high school students take as an entrance exam to higher (university and college) education, was given from 4th June to 7th June 2018 and it was reported that about 284,000 students took the examination.

In related news, NEAEA staff and officials had annual meeting on 9th July 2018 and evaluated the 2017/18 Annual Progress Report of the Agency. The meeting was led by the Director-General of the Agency, Ato Araya Gebregziabher and the Deputy Director, Dr. Zerihun Duresa, in the assembly hall of the Agency.

[Amharic-version] የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እስከ ሐምሌ 25 ድረስ ይገለጻል

አዲስ አበባ (ኢዜአ)–የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እስከ ሐምሌ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ይፋ እንደሚደረግ የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሔር ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) እንደገለጹት፤ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እስከ ሐምሌ 25 ቀን 2010 ዓ.ም ባሉ ቀናት ውስጥ ይገለጻል።

የ10ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ደግሞ የ12ኛ ውጤት ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ይፋ እንደሚደረግም ጠቁመዋል።

የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ብሄራዊ ፈተና ከግንቦት 27 ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 2010 ዓ.ም ድረስ መሰጠቱ የሚታወስ ነው።

በዘንድሮው ዓመት 284 ሺህ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደዋል።

ነጻ የትምህርት ዕድሎች፦ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርታቸውን በውጭ ሀገራት እንዲማሩ የሚያስችሉ እድሎች

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ሠራተኞችና ኃላፊዎች ሐምሌ 2 ቀን 2010 ዓ.ም የተቋሙ የ2010 ዓ.ም ዓመታዊ ዕቅድ አፈፃፀም በጋራ በመገምገም የቀጣዩን በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ለይተዋል። በኤጀንሲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተደረገውን የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ የመሩት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርዓያ ገ/እግዚአብሔር እና ም/ዋ/ዳይሬክተሩ ዶ/ር ዘርይሁን ዱሬሳ ነበሩ።

——
Semonegna.com