Search Results for 'አያኖ በራሶ'

Home Forums Search Search Results for 'አያኖ በራሶ'

Viewing 5 results - 1 through 5 (of 5 total)
  • Author
    Search Results
  • Semonegna
    Keymaster

    ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ 2891 ተማሪዎችን በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመረቀ

    ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በድህረ ምረቃ፣ በቅድመ ምረቃ እና ዲፕሎማ ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን 2891 ተማሪዎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ሐምሌ 10 ቀን፥ 2014 ዓ.ም በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስመርቋል።

    የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶክተር ብርሃነመስቀል ጠና ለዕለቱ ተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ባሰሙበት ንግግራቸው፥ ነባሩ እና አንጋፋው ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ በማታና በተከታታይ የዲፕሎማ፣ የዲግሪ እና የማስትሬት መርሐግብሮች ትምህርታቸውን በሚገባ አጠናቀው፣ አስፈላጊውን የምረቃ መስፈርት አሟልተው በዕለቱ ለምረቃ የበቁት የ2014 ዓ.ም ተመራቂዎች 2891 መሆናቸውን ተናግረዋል። ከእነዚህም ተመራቂዎች መካከል ወንድ 1409፣ ሴት ደግሞ 1482 ሲሆኑ፣ ይህም የሴት ተመራቂዎች ቁጥር ብልጫ ያለው መሆኑንና ዩኒቨርሲቲውም ለሴቶች ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጥ ያሳያል ሲሉ ዶክተር ብርሃነመስቀል ተናግረዋል። በመጨረሻም ፕሬዝዳንቱ የዕለቱ ተመራቂዎች በዩኒቨርሲቲው አዲሱ ስያሜ፣ ተልዕኮ፣ ሎጎ እና ህብረ ዝማሬ በመመረቃቸው የተቋሙ ታሪክ አካል እንደሚያደርጋቸው አስገንዝበዋል።

    የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የዕለቱ የክብር እንግዳ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአዲስ መልክ እየተዋቀረ ያለው ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሀገሪቱን የትምህርት ችግሮች ለመቅረፍ በከፍተኛ ደረጃ ኃላፊነት የተጣለበት በመሆኑ፣ ይህንን ልዩ ተልዕኮውን ለመወጣት በሚያደርገው ጥረትም የትምህርት ሚኒስቴር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግለት ገልጸዋል።

    በሥነ ሥርዓቱ ላይም በትምህርታቸው ብልጫ ላሳዩ ተመራቂዎች የዋንጫ እና ሌሎች ሽልማቶች ተሰጥቷቸዋል። እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የሽግግር ወቅት ልዩ ልዩ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላትም የዕውቅና ምስክር ወረቀትና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡

    ከከፍተኛ ትምህርት ዜና ሳንወጣ፥ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጀርመን ስቱትጋርት ከተማ ውስጥከሚገኘው የሆኸንሃየም ዩኒቨርሲቲ (University of Hohenheim) ጋር የአጋርነት ስምምነት ተፈራርሟል።

    የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ ከዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝደንት እና ከዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች ጋር በመሆን በጀርመን ሀገር በግብርናና በሥነ ምግብ ሳይንስ ቀዳሚ ከሆነው ከሆኸንሃየም ዩኒቨርሲቲ (University of Hohenheim) ጋር ላለፉት 8 ዓመታት ሲተገበር በነበረው የCLIFOOD ፕሮጀክት ወርክሾፕ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ተመራማሪ በዶ/ር ስንታየሁ ይግረም አስተባባሪነት የሚመራው ይህ የCLIFOOD ፕሮጀክት በአየር ንብረት ለውጥና በምግብ ዋስትና ዙሪያ የሚሠራ ሲሆን ለ27 የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሦስትኛ ዲግሪና የድኅረ-ዶክትሬት (postdoctoral)  ትምህርት እንዲማሩና፣ የዩኒቨርሲቲው የምርምር ላቦራቶሪዎች አቅም እንዲያድግ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡ በዚሁ አጋጣሚ ሁለቱ አንጋፋ የትምህርትና ምርምር ተቋማት ግንኙነታቸውን ለማደስና በሌሎች ዘርፎችም አብረው ለመሥራት የሚያስችላቸውን ውል ተፈራርመዋል፡፡

    ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ

    Semonegna

    Anonymous
    Inactive

    ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 4,700 ተማሪዎችን ዛሬ አስመረቀ

    ሐዋሳ (ኢዜአ/HU) – ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በበይነ-መረብ (virtual) ትምህርታቸውን እንዲጨርሱ ያስቻለቸውን የድኅረ ምረቃ (ሁለተኛ እና ሦስተኛ ዲግሪ) ተማሪዎች እንዲሁም ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት በፊት በእንስሳት ሕክምና እና በሌሎች መርሀ-ግብሮች ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ የመጀመሪያ ዲግሪ 4,780 ተማሪዎችን ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም አስመረቀ።

    ዩኒቨርሲቲው ለ21ኛ ጊዜ ካስመረቃቸው መካከል 2,866 በመጀመሪያ፣ 1,900 በሁለተኛ እና 12 ደግሞ በሦስተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸው መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ ገልጸዋል።

    ተማሪቂዎችና ቤተሰቦቻቸው በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ (ኮቪድ-19) ምክንያት የተፈጠረውን አስቸጋሪ ሁኔታ ተቋቁመው ለመመረቅ በመብቃታቸው እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው ወረርሽኙን ከመከላከሉ ሥራ በተጓዳኝ ችግር ፈቺ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎች ላይ ትኩረት በመስጠት እና የመንግሥትን የልማት እንቅስቃሴ በጥናት ለመደገፍ ጥረት እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ወረርሽኙን እየተከላከሉ መደበኛ የትምህርት ሥራቸውን ለመጀመር እየተዘጋጁ መሆኑን ገልጸዋል።

    ዶ/ር አያኖ በአዲሱ ፍኖተ-ካርታ መሠረት የምርምር ዩኒቨርሲቲ (Research University) ለመሆን ከሚጠበቁት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በቀዳሚነት ለማሰለፍ በቁርጠኝነት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

    የዩኒቨርሲቲው ምክትል ቦርድ ሰብሳቢና የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው ተመራቂዎች የቀሰሙትን ዕውቀት በተግባር በማዋል የሀገሪቱን ዕድገት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። ተቋሙ በተደራረበ ጫና ውስጥ እያለ ተማሪዎችን ማስመረቁ፥ ምርምርና የማኅበረሰብ አገልግሎቶችን አጠናክሮ መቀጠሉ የአመራሩንና የሠራተኞችን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል።

    በእንስሳት ሕክምና ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የተመረቀው ዶ/ር ግርማ በዳዳ በሰጠው አስተያየት፥ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ጫና በመቋቋምና ጥናቱ ላይ በመትጋት ለምርቃ መብቃቱን ተናግሯል። ለዚህም ዩኒቨርሲቲውን አመሰግኗል።

    ሌላዋ በሶሻል ሣይኮሎጂ የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ ማርታ ማጋ በበኩሏ፥ ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት የክፍል ትምህርት ማጠናቀቃቸውን ጠቅሳ፤ የምርምር ሥራዋን ከዩኒቨርሲቲው ውጭ በማካሄድ ለመመረቅ እንደበቃች ገልጻለች።

    ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና ተከታታይ የትምህርት መርሀ-ግብር የሚያስተምራቸው ከ43,000 በላይ ተማሪዎች እንዳሉት ከዩኒቨርሲቲው ድረ-ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ዩኒቨርሲቲው በአጠቃላይ ከ7,000 በላይ ሠራተኞች (staff)፣ ሰባት ካምፓሶች፣ ስምንት ኮሌጆችና ሁለት ተቋማት (institutes)፣ እና ከ200 በላይ የትምህርት መርሀ ግብራት (programs) እንዳሉት ድረ-ገጹ ያሳያል።

    ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ)/ ዩኒቨርሲቲው (HU)

    ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ

    Anonymous
    Inactive

    ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 221 የህክምና ዶክተሮችና ስፔሻሊስቶችን አስመረቀ

    ሀዋሳ (ኢዜአ) – የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምንጮች ብቻ ሳይሆኑ በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፀ ዜጋን ማፍሪያ ማዕከላት ጭምር መሆን እንዳለባቸው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አሳሰቡ።

    ዩኒቨርሲቲው የካቲት 8 ቀን 2012 ዓ.ም. በአጠቃላይ 221 የጤና ባለሙያዎችን (192 የህክምና ዶክተሮችና 29 ስፔሻሊስት ዶክተሮችን) አስመርቋል። ከተመራቂዎች ውስጥ 22 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውም ተጠቁሟል።

    በምረቃ በዓሉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ እንደገለፁት፥ ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲግሪ፣ በህክምና ስፔሻሊስትና በሦስተኛ ዲግሪ በርካታ የትምህርት መስኮችን (ፕሮግራሞችን) በመክፈት ከ43 ሺህ 800 በላይ ተማሪዎችን በመደበኛና በተከታታይ ትምህርት መርሀ ግብሮች እያስተማረ ይገኛል። የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅም የመምህራን ልማት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል።

    ሀገሪቱ ካላት ውስን ሀብት ላይ አንድ አራተኛውን በጀት ለትምህርት ማዋሏን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፥ ተመራቂዎችም ያላቸውን ዕውቀት፣ ክህሎትና ጉልበት ላስተማራቸው ማኅበረሰብ በማበርከት ለሀገራቸው ዕድገት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ ጠይቀዋል።

    ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምንጮች ብቻ ሳይሆኑ በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፀ ዜጋን ማፍሪያ ማዕከላትም ናቸው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ ተመራቂዎች ራሳቸውን ከመጥፎ ምግባር በመቆጠብና ሙያው በሚጠይቀው ሥነ-ምግባር ህሙማንን በፍቅር ማገልገል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

    በምረቃ በዓሉ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ አባል ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በበኩላቸው ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

    ፕሮፌሰር በየነ እንዳሉት፥ ሀገሪቱ ባለፉት ሃያና ሰላሳ ዓመታት ውስጥ በጤናው ዘርፍ በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ እመርታ በማስመዝገብ የዓለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ ሌሎች ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ታላላቅ ዓለም ዓቀፍ ተቋማትና መንግሥታት ዕውቅና ማግኘቷን ተናግረዋል።

    ይሁን እንጂ አሁንም የጤና ሽፋንን ከመጨመርና ጥራትና ፍትሐዊነት ያለው አገልግሎት ከመስጠት አንጻር ብዙ ርቀት መጓዝ እንደሚጠይቅ የተናገሩት ፕሮፌሰር በየነ፥ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት ጠንክረን በጋራና በትብብር መንፈስ መሥራት አለብን ብለዋል። የዛሬ ተመራቂዎችም የነገዋ ኢትዮጵያ ተስፋዎች መሆናቸውን በመረዳት ሀገራቸውን ማገልገል እናዳለባቸው ጠቁመዋል።

    በሙያቸው ገፍተው ዕውቀትና ክህሎታቸውን በማዳበርም የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡና ችግር ፈቺ በሆኑ ምርምሮች ውስጥ በመሳተፍ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተተገበረ ያለውን ፈርጀ ብዙ ለውጥ የማቀጣጠልና የማስቀጠል ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል ።

    ከተመራቂዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት በማምጣት የሜዳልያ ተሸላሚ የሆነው ዶ/ር አቤል ጌታቸው በሰጠው አስተያየት፥ የህክምና ትምህርት ጽናትን የሚጠይቅ መሆኑን ገልፆ ሁኔታዎችን በትዕግስት በማለፍ ለዚህ መብቃቱን ተናግሯል።

    የህክምና ሙያ በራሱ ለሰዎች ክብር መስጠትና ርህራሄ መላበስን የሚያስተምር እንደሆነ የተናገረው ዶ/ር አቤል፥ ያለአድሎ ሰብዓዊነትን በመላበስ ህብረተሰቡን ለማገልገል ዝግጁ መሆኑን አስረድቷል።

    በውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻላይዝድ በማድረግ የተመረቀው ዶ/ር ሙባረክ ሁሴን በበኩሉ፥ የህክምና ሥነ-ምግባር ከሀሳብ ይልቅ በተግባር የሚገለፅ መሆኑንና ታካሚዎችን እንደ ቤተሰብ በማየት ያለአድሎ ለማገልገል መዘጋጀቱን ተናግሯል።

    የዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህክምና ዶክትሬት ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ለ11ኛ ዙር ሲሆን ስፔሻሊስት ሀኪሞችን ደግሞ ለ4ኛ ዙር መሆኑ ተዘግቧል።

    ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ)/ ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 221 የህክምና ዶክተሮችና ስፔሻሊስቶችን አስመረቀ

    Semonegna
    Keymaster

    የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በንሳ ዳዬ ካምፓስ ካለው ርቀትና የመሬት አቀማማጥ አኳያ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ራሱን ወደቻለ ዩኒቨርሲቲ ሊያድግ የሚችል በመሆኑ ግንባታዎቹ ይህንኑን ታሳቢ አድርጎ የተካሄዱ እንደሆነ ታውቋል።

    ሀዋሳ (ሰሞነኛ)– ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ያቋቋመውና ላለፉት 4 ዓመታት በግንባታ ሂዳት ላይ የነበረው የበንሳ ዳዬ ካምፓስ ጥቅምት 30 ቀን 2011ዓ.ም. ወደ ካምፓሱ ለተመደቡ 340 አዲስ ገቢ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል በማድረግ በይፋ ሥራውን ጀምሯል።

    በበንሳ ወረዳ ዳዬ ከተማ ውስጥ ወደተገነባው ካምፓስ ተማሪዎቹ በመጡበት ጊዜ በአከባቢው ማኀበረሰብ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቶ አያኖ በራሶ በቦታው በመገኘትለተማሪዎቹ የዩኒቨርሲቲው አባልነታቸውን አረጋግጠውላቸዋል።

    አቶ አያኖ ለተማሪዎች፣ ለአካባቢው ህብረተሰብ እና ለእንግዶች ባስተላለፉት መልዕክት መንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በያዘው የትኩረት አቅጣጫ ካምፓሱ የተገነባ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ባይጠናቀቅም የሰው ሃይልና አስፈላጊ ቁሳቁሶች በመሟላታቸው ወደ ሥራ መገባቱን አስረድተዋል።

    በንሳ ዳዬ ካምፓስ ካለው ርቀትና የመሬት አቀማማጥ አኳያ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ራሱን ወደቻለ ዩኒቨርሲቲ ሊያድግ የሚችል በመሆኑ ግንባታዎቹ ይህንኑን ታሳቢ አድርጎ የተካሄዱ እንደሆነ ያስታወቁት ፕሬዝዳንቱ፥ ተማሪዎች፣ ሠራተኞችና የአከባቢው ማኀበረሰብ እንደግል ንብረታቸው መንከባከብና ለመጭው ትውልድ የማስተላፍ ግዴታ እንዲወጡ አሳስበዋል።

    አዲስ የተመደቡ ተማሪዎችም ከቤተሰብ ተለይተው የመጡበትን ዓላማ በማንገብ ጊዜያዊ ተግዳሮቶችን በመቋቋም፣ ከአልባሌ ሱሶች (እና ድርጊቶች) በመራቅና በርትቶ በማጥናት ከቤተሰብና ሀገር የተጣለባቸውን አደራ ለመወጣት ራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸው አቶ አያኖ በራሶ አስገንዝበዋል።

    የካምፓሱ ማኔጅንግ ዳይሬክቴር አቶ ገነነ ካቢሶ በበኩላቸው ካምፓሱ በእርሻ ሜካናይዜሼንና በመምህራን ስልጠና የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያሰለጥን ሲሆን፥ በተማሪዎቹ በሚካሄዱ አሳታፊና ችግር ፌች ምርምሮች የአከባቢውን ማሀበረሰብ ያሳተፈ እንዲሆን ህብረተሰቡ እንዲተባበር ተከታታይ ስልጠናዎች የሚሰጡ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

    በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንቶች፣ የበንሳ ዳዬ ከተማ፣ የአከባቢው ቀበሌ ገበሬ ማኀበራት አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ከአከባቢው ማኀበረሰብ የወጣቶችና ሴቶች ተወካዮች መገኘታቸው ታውቋል።

    ምንጭ፦ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
    ——
    ተመሳሳይ ዜናዎች፦

    በንሳ ዳዬ ካምፓስ

Viewing 5 results - 1 through 5 (of 5 total)