Search Results for 'ኢትዮጵያ'

Home Forums Search Search Results for 'ኢትዮጵያ'

Viewing 15 results - 421 through 435 (of 730 total)
  • Author
    Search Results
  • Anonymous
    Inactive

    ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በቡራዩ ካምፓስ በአካውንቲንግና ፋይናንስ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በካምፓሱ ለመጀመሪያ ጊዜ አስመረቀ
    —–

    ቡራዩ (ሰሞነኛ)– ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ሰኔ 29 ቀን 2011 ዓ.ም, ለመጀመሪያ ጊዜ በቡራዩ ገፈርሳ ካምፓስ በአካውንቲንግና ፋይናንስ በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በቅድመ መደበኛ ትምህርት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ሕጻናትን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አረጋ ይርዳውና የሴኔት አባላት እንዲሁም የቡራዩ ከተማ ከንቲባ ተወካይ አቶ ተረፈ ንጋቱ በክብር እንግድነት በተገኙበት አስመርቋል።
    ዩኒቨርሲቲው በዚህ ዓመት በ36ኛው ዙር በተለያዪ ካምፓሶች ከ1500 በላይ ተማሪዎችን ያስመርቃል። በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ገፈርሳ ካምፓስ ለመጀመሪያ ጊዜ 18 ተማሪዎችን በዲግሪ እና በመዋዕለ ሕፃናት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን አስመርቋል። በዕለቱ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የተጀመረው በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙሮች እና በአካባቢው አባ ገዳዎች ምርቃት ነው።

    በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ አቶ ተፈራ ንጋቱ ባደረጉት ገለጻ ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በገፈርሳ ካምፓሱ ከተማሪ ብዛት ይልቅ የትምህርት ጥራት ላይ አተኩሮ በመንቀሳቀሱ ሊመሰገን እንደሚገባው ጠቅሰው የዛሬ ተመራቂዎች ዛሬ ተመርቃችሁ የጨረሳችሁ ሳይሆን ወደ ሌላ ምዕራፍ የሚያሸጋግራችሁ በመሆኑ በርቱ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

    ዩኒቨርሲቲው በገፈርሳ ካምፓሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ባካሄደው በዚሁ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተገለጸው፤ ካምፓሱ ስፋት ባለው ቦታ ላይ የተመሰረተና በአካውንቲንግና ፋይናንስ፣ በማኔጅመንት፣ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት፣ በአኒማል ፕሮዳክሽን ቴክኖሎጂ እና በሆርቲካልቸር በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት በመስጠት ላይ ይገኛል።

    በሌላ በኩል ዩኒቲ አካዳሚ ቡራዩ ካምፓስ በመጪው ዓመት መደበኛ እስከ 8ኛ ክፍል አካዳሚውን በማስፋፋት የቡራዩ ሕብረተሰብ የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ የማስፋፋት ሥራ እየሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

    በዚህ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተመራቂ ወላጆች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በዕለቱ የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አረጋ ይርዳው በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሜዳሊያና የፕሬዚዳንቱን ዋንጫ ሸልመዋል።

    ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ ውጭ በደሴና በአዳማ የስልጠና መስኮችን በመለየት የተለያዩ ፕሮግራሞችን ለሕብረተሰቡ በመስጠት ላይ ይገኛል።

    ምንጭ፦ ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    Anonymous
    Inactive

    ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ ለ6ኛ ጊዜ 3,144 ተማሪዎችን በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ
    —–

    ከ23,500 በላይ ተማሪዎችን በዋናው ግቢ፣ በዱራሜ፣ በንግስት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ሆስፒታል እያስተማረ የሚገኘው ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ ለ6ኛ ጊዜ 3,144 ተማሪዎችን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል።

    “አሁን የታየውን የአገራችን የለውጥ ተስፋ ማስቀጠል የሞት ሽረት ጉዳይ ነው። በመሆኑም በሁሉም ዘርፍ በእውቀትና ክህሎት የበቃ የሰው ሃይል ያስፈልጋታል” የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሀብታሙ አበበ በተማሪዎቹ የምርቃት ሥነ ስርዓት ላይ።

    ለዚህ ደግሞ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መጀመሪያ ራሳቸውን እየለወጡ በአዳዲስ ሳይንሳዊ ውጤቶች መደራጀት፣ ጊዜውን በሚመጥን መልኩ ዓለም አቀፋዊ አስተሳሰብ ተላብሰው መጓዝ አለባቸው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

    *** የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አዲሱ ፕሬዝዳንት ከዩኒቨርሲቲው ኮሌጆችና አስተዳደር ሠራተኞች ጋር ያዘጋጁት የምክክር መድረክ

    የተማረ ሰው ለብዙም ሆነ ለትናንሽ ችግሮች ብዙ መፍትሄ ይፈልጋል፤ አገራችን አሁን ካጋጠሟት ችግሮች እንድትላቀቅ እናንተ የዛሬ ተመራቂዎች በሰበሰባችሁት እውቀትና ክህሎት የመፍትሄ አካል እንድትሆኑ አደራ አለባችሁ ያሉት ደግሞ የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር አየለ ሄገና ናቸው።

    በሠላም ተምሳሌትነት የሚታወቀው የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከተቋቋመበት ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ 11,638 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ፥ ከእነዚህ ተመራቂዎች 60%ቱ በግልና በመንግስት ሥራዎች መሰማራታቸውን ዩኒቨርሲቲው በጥናት /tracer study/ እንዳረጋገጠ ጠቁሟል።

    የመቀጠር እና የስራ ፈጣሪነት አቅም ለማሳደግ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሥራ ፈጠራ ማዕከል ተቋቁሞ እየተሠራ እንደሚገኝ ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።

    ዩኒቨርሲቲው በ6 ኮሌጆች፣ በ2 ት/ቤቶች በ54 ቅድመ-ምረቃ እና በ7 ድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ትምህርት እየሰጠ ይገኛል።
    ከአገር በቀል እውቀቶች ልማት አንጻር ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሀድይሳ እና ከምባትኛ ቋንቋዎችን በዋና ግቢ እና በዱራሜ ካምፓሶች ማስተማር መጀመሩ ተገልጿል።

    ምንጭ፦ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    Anonymous
    Inactive

    ተመራቂዎች ለኢትዮጵያ አንድነትና ብልጽግና እንዲሰሩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሳሰቡ
    —–

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – ተመራቂዎች ከፊታቸው ውጣ ውረድ ያለበት ሕይወት ስለሚጠብቃቸው በትጋት ለመወጣት ጥረታቸው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

    አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ ምረቃ እና በድህረ ምረቃ በቀን፣ በማታ፣ በርቀት እና በክረምት መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 9,637 ተማሪዎችን ሐምሌ 6 ቀን 2011 ዓ.ም. የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ከፍተኛ የመንግስት ባስልጣናት፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ሙሁራን በተገኙበት በከፍተኛ ድምቀት በሚሊኒየም አዳራሽ አስመርቋል።

    ከተመረቁት 9,637 ተማሪዎች ውስጥ በቅድመ ምረቃ 5,876፣ በድህረ ምረቃ 3,761 ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ 2,763 ሴቶች ናቸው።

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ምንም እንኳን በቀጣይ የሚጠብቃቸውና መውደቅና መመረቅ ያሉባቸው ሰፊ ትምህርት ቤቶች ቢኖሩም የዛሬውን መመረቅ ልዩ የሚያደርገው የዛሬ ተመራቂዎች ለቀጣይ ሕይወታቸው ስንቅ ይዘው በብዛትና በአንድነት የሚመረቁበት ዕለት መሆኑ ነው። በቀጣይ የሚጠብቃቸውም የትዳር ዩኒቨርሲቲ፣ የሥራና የሕይወት ዩኒቨርሲቲ ከባድ ፈተና በታላቅ ስብዕና ለማለፍ እንዲሁም በሕይወት የሚገጥማቸውን ችግሮች በጽናት ለመወጣት ጥረትና ትጋት ያስፈልጋቸዋል ብለዋል።

    ”የሕይወት ፈተናን ተጋፍጣችሁ ሌላውን ሕይወት በብቃት ለመወጣት ማንበብና እራስን ማብቃት ወሳኝ ነውም” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ።

    በተለይ በዩንቨርሲቲ ሕይወት ያገኙትንና ያዳበሩትን አብሮ የመኖር ባህል ለትውልድ በማስተላለፍ የተሻለች ኢትዮጰያን ለመመስረት ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

    በተለይም ለሰው ልጅ ለመማር ወይም ለመላቅ ብዙ ገፊ ምክንያቶች እንዳሉት ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ከእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ሕይወትን በትርጉም ለመምራት የሚያስችሉና ማፍቀር፣ መስጠት እንዲሁም ማገልገል ትልቁ መርህ አድርጋችሁ አገራችሁን አገልግሉ ብለዋል።

    በመስጠትና በማገልገል መርህም በዘንድሮው ክረምት ብቻ በአዲስ አበባ ከ400 በላይ ትምህርት ቤቶች፣ ከ10 በላይ ሆስፒታሎች እና ከ1000 በላይ የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶች የማደስ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በአዲስ አበባ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለሚማሩት ከ600 ሺህ በላይ ተማሪዎች የደብተርና ዩኒፎርም ስጦታ መዘጋጀቱንም አውስቷል።

    አገሪቷ በችግኝ ተከላ ዘመቻ ላይ መሆኗን ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ስንኖር ኢትዮጵያዊ ለመሆን የምንችለው አረንጓዴ ኢትዮጵያን መፍጠር ከቻልን ነው፤ ስንሞት ኢትዮጵያም መሆን የምንችለው ቢያንስ በለምለምና በጥላ ስር ዘላለማዊ እረፍት ማድረግ ስንችል ነው” በማለት ተማሪዎቹ ጠንክረው እንዲሠሩ አሳስበዋል።

    ሳይማር ያስተማረውን ህብረተሰብ በማገልገል፣ አርሶ አደሩን ከሞፈርና ከቀንበር የማላቀቅ፣ የጽናትንና የማገልገል ልምድ ዛሬ መጀመር ማድረግ እንዳለባቸውም ጠቁመዋል። ዜጎች ሳይቸገሩ በሁሉም ቦታ ተንቀሳቅሰው እንዲኖሩና ለኢትዮጵያ ጽናትና ብልጽግና እንዲሠሩም ጠይቀዋል። ትምህርት መነሻ እንጂ መድረሻ አይደለም የሚሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ እውቀታቸውን ለማሻሻል ጥረት ማድረግ እንዳለባቸውም አመልክተዋል። ተመራቂዎች አባቶች ያቆዩዋትን ኢትዮጵያ ጉዳይ ለክርክርና ለድርድር እንዳያቀርቡም አክለው አሳስበዋል።

    በዘንድሮው የምረቃ በዓል ላይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሁለት የክብር ዶክትሬቶችን፥ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም እና ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ካውንስል ኃላፊ እና የዑለማ ኃላፊ ሀጂ ሙፍቲ ሼክ ዑመር እድሪስ ሰጥቷል።

    ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ)/ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ/ ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    Anonymous
    Inactive

    እነዚህን የተከለከሉ የምግብ ምርት ዓይነቶች ዝርዝራቸውን በማውጣት ምርቶቹን ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸውና ተቆጣጣሪ አካላት ምርቶቹን በአፋጣኝ ከገበያ ላይ ባለስልጣኑ ጥሪውን አቅርቧል።

    አዲስ አበባ (ኤፍ.ቢ.ሲ.) – የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን 57 የምግብ ምርት ዓይነቶችን ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀም አሳሰበ።

    ባለስልጣኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በላከው መግለጫ በምግቦቹ ጥራትና ደኅንነት ላይ ባደረገው የገበያ ጥናት የምግብ ምርቶቹ መሰረታዊ የገላጭ የፅሁፍ ክፍተት ያለባቸው፣ የሚመረቱበት ቦታ የማይታወቅ፣ የንጥረ ነገር ይዘት የሌላቸው፣ አምራች ድርጅቶቹ የማይታወቁ፣ የምርት መለያ ቁጥር፣ የተመረቱበት ጊዜ እና የምርቱ ማብቂያ ጊዜ ገላጭ ፅሁፍ የሌላቸው ናቸው ብሏል።

    ከዚህ ጋር ተያይዞም ምርቶቹን ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸውና ተቆጣጣሪ አካላት ምርቶቹን በአፋጣኝ ከገበያ ላይ እንዲሰበስቡም ጥሪውን አቅርቧል።

    የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ሕብተረሰቡ እንዳይጠቀማቸው የተከለከሉ የምግብ ምርት ዓይነቶች ዝርዝር፤

    • የከረሚላ ምርቶች፦
      • ጆሊ ሎሊፖፕ፣
      • አናናስ ከረሚላ፣
      • ኮላስ ከረሚላ፣
      • ኦሊ ፖፕ፣
      • ቤስት ከረሚላ፣
      • የስ ከረሚላ (ኮፊ ከረሚላ)፣
      • ማሚ ሎሊ ፖፕ፣
      • ሳራ ከረሚላ፣
      • ጃር ሎሊ ፖፕ፣
      • ጸሃይ ሎሊ ፖፕ፣
      • ዩኒክ ሎሊ ፖፕ፣
      • እንጆሪ ከረሚላ፣
      • ብርቱካን ከረሚላ፣
      • ይናቱ ሎሊ ፖፕ እና
      • ሃላዋ ከረሚላ፤
    • የማር ምርቶች፦
      • አፍያ የተፈጥሮ ማር፣
      • ሪትም ማር እና
      • በላይ ማር፤
    • የገበታ ጨው፦
      • ዊዲ የገበታ ጨው፣
      • ሱላ የገበታ ጨው፣
      • ናይ የገበታ ጨው፣
      • ሃያት የገበታ ጨው፣
      • አቤት የገበታ ጨው፣
      • በእምነት የገበታ ጨው፣
      • እናት የገበታ ጨው፣
      • አባይ የገበታ ጨው፣
      • አባት የገበታ ጨው፣
      • ሴፍ የገበታ ጨው እና
      • ጣዕም የገበታ ጨው፤
    • የለውዝ ቅቤ፦
      • ደስታ የለውዝ ቅቤ፣
      • አስነብ የለውዝ ቅቤ፣
      • ኑኑ የለውዝ ቅቤ፣
      • አቢሲኒያ የለውዝ ቅቤ፣
      • ብስራት የለውዝ ቅቤ፣
      • ፈሌ የለውዝ ቅቤ፣
      • ሳባ የለውዝ ቅቤ፣
      • አዳ የለውዝ ቅቤእና
      • አደይ የለውዝ ቅቤ፤
    • የኑግ ዘይት፦
      • አደይ አበባ የኑግ ዘይትእና
      • ቀመር የኑግ ዘይት፤
    • አልሚ የህጻናት ምግቦች፦
      • ምሳሌ የህጻናት ምግብ፣
      • ኤልሞ የልጆች ምግብ፣
      • ሂሩት የህጻናት አጃ፣
      • ዘይነብ የህጻናት አጥሚት፣
      • ተወዳጅ ገንቢ የህጻናት አጥሚት፣
      • ተወዳጅ የህጻናት ሽሮ እና
      • ፋሚሊ ሃይል ሰጭና ገንቢ የህጻናት ሽሮ፣
    • ሌሎች የተከለከሉ የምግብ ምርት ዓይነቶች፦
      • ቪንቶ፤ ዴኮ፣ እስፔሻል፣ ዳና፣ ቃና፣ ላራ፣ ዛጎል አቼቶ፣ ናይስ አቼቶ፣ አምቴሳ አቼቶ፣ ማይ አቼቶ፣ መስ አቼቶ እና ቫይኪንግ አቼቶ ምርቶች

    እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን የምግብና ምግብ ነክ ምርቶች ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ታግደዋል። ባለስልጣኑ ከሦስት ሳምንታት በፊትም 46 የብቃት ማረጋገጫ የሌላቸው የታሸጉ የምግብ ምርቶች ላይ እርምጃ መውሰዱንና፤ ሕብረተሰቡም እንዳይጠቀማቸው መከልከሉን መዘገባችን ይታወሳል። ዘገባውንና የተከለከሉትን የምግብ ዓይነቶች ዝርዝር ለማግኘት እዚህ ጋር ይጫኑ

    ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ./ ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    የተከለከሉ የምግብ ምርት ዓይነቶች


    Anonymous
    Inactive

    ሠመራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ፕሮግራሞች ስያስተምር የቆየውን 1,800 ተማሪዎችን አስመረቀ
    —–

    ሠመራ (ሰሞነኛ) – ሠመራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ፕሮግራሞች ስያስተምር የቆየውን 1800 ተማሪዎችን የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት አስመርቋል። ክብርት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማርያም በተመሪዎች የምርቃት ሥነ ስርዓት ላይ በመገኘት ለተመራቂዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።

    ክብርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማርያም ለተመራቂዎቹ፣ “በሰው ዘር መገኛ አፋር ሆነን በብሔር ላይ የተመሠረተ ግጭት አያምርብንም ብላችሁ የህይወት ግባችሁ ላይ በማተኮር በወንድማማችነት እና እትማማችነት ሰላማችሁን አስጠብቃችሁ ዓመቱን በማጠናቀቃችሁ አመሰግናችኋለሁ” ብለዋል።

    በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ ወቅት በቀጣይ ትውልድ የምንመኘው አንድነቷ በማይናወጥ መሠረት ላይ የተጣለ፣ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገቷ የበለፀገች ሀገር እና ዜጐችዋ የተደላደለ ሕይወት የሚመሩባትን ኢትዮጵያን ነው፤ ይህን የምናሳካው የዛሬው ትውልድ በዕውቀት፣ በክህሎት፣ በመልካም አስተሳሰብና ሥነ-ምግባር በሀገርና በሕዝብ ፍቅር ታንፆ ሲወጣ ብቻ ነው፤ ለዚህ ደግሞ እናንተ የዛሬ ተመራቂዎች ከፍተኛ አደራ ተጥሎባችኋል ብለዋል ሚኒስትር ሒሩት።

    ከተማሪዎች ምርቃት በኋላም በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተካሂዷል።

    ምንጭ፦ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

    Anonymous
    Inactive

    አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለ32ኛ ጊዜ 6,857 ተማሪዎችን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል
    —–

    አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በቅድመ ምረቃና በድኅረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 6,857 ተማሪዎች ሰኔ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. አባያ ካምፓስ በሚገኘው አዳራሽ እና ሰኔ 30 ቀን2011 ዓ.ም. በሣውላ ካምፓስ በድምቀት አስመርቋል። ከተመራቂዎች መካከል 4,434 ወንዶች ሲሆኑ 2,423 ሴቶች ናቸው።

    የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ በመክፈቻ ንግግራቸው ተመራቂዎች የሥራ ዓለምን ሲቀላቀሉ ከዩኒቨርሲቲው በገበዩት እውቀት፣ ክህሎትና መልካም ሥነ-ምግባር መንግሥትና ህዝብ የአገሪቱን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ እያደረገ ባለው ጥረት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እንዲሁም ራሳቸውን፣ ወገናቸውንና አገራቸውን ለማሳደግ እንዲተጉ ጥሪ አቅርበዋል።

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እና የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ለተመራቂዎች ባስተላለፉት መልዕክት ተመራቂ ተማሪዎች በተለያየ መልኩ ወደ ሥራው ዓለም ሲቀላቀሉ በአገራችን የተጀመረውን የለውጥ ሂደት የተሳካ እንዲሆን የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

    በአሁኑ ጊዜ በአገራችን መልካም ተስፋ እየታየ ቢሆንም ተስፋውን የሚያደበዝዙ ችግሮች ይስተዋላሉ ያሉት ዶ/ር ይናገር፥ ችግሮች እንዳይከሰቱና ከተከሰቱም በሰከነ ሁኔታ እንዲፈቱ በማኅበራዊ ሚዲያ ለሚሠራጩ ሀሰተኛ ወሬዎች ቦታ ሳይሰጡ ለአገራችን አንድነትና አብሮነት የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል።

    የዕለቱ እንግዳና የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድ አባል ዶ/ር አብርሃም አላኖ በበኩላቸው የአንድ አገር ልማት ያለ ትምህርት መስፋፋት እውን ሊሆን እንደማይችል መንግሥት ተረድቶ ለከፍተኛ ትምህርት ፍትሃዊ መስፋፋትና ተደራሽነት በትኩረት ሲሠራ የቆየ በመሆኑ በዘርፉ አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል። መንግሥትና የዘርፉ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በትምህርት ጥራት ላይ ትኩረት አድርገው እየሠሩ መሆናቸውን የገለፁት ዶ/ር አብርሃም አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲም በአገሪቱ ከሚገኙ የመጀመሪያ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል በሁሉም መስኮች ቀዳሚ የመሆን ራዕይ ሰንቆ እየሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

    አገራችን ኢትዮጵያ በዕድገት ላይ የምትገኝ አገር መሆኗን ያወሱት የክብር እንግዳው ከለውጡ ጋር ተያይዞ በርካታ መልካም አጋጣሚዎች እንዳሉ ሁሉ ከፍተኛ ተግዳሮቶችና ፈተናዎች የተጋረጡ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ ረገድ የዕለቱ ተመራቂዎች ምክንያታዊ በመሆንና ከግለኝነት አስተሳሰብ በመውጣት ለማኅበረሳባችን ለውጥ ብሎም አገሪቱ ከገጠማት ፈተና እንድትወጣና የተጀመረው ለውጥ እውን እንዲሆን የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

    ከአጠቃላይ ተመራቂዎች መካከል 4 ነጥብ በማምጣት የሜዳልያና ዋንጫ ተሸላሚ የሆነው የማርኬቲንግ ማኔጅመንት ተመራቂ እስማኤል ፈድሉ በሰጠው አስተያየት ጠንክሮ መሥራቱና ጊዜውን በአግባቡ መጠቀሙ ለስኬት እንዳበቃው ገልጿል። ማንኛውም ሰው በተሰማራበት መስክ ዓላማ በመሰነቅ በቁርጠኝነት ከሠራ ውጤታማ መሆን ይችላል ያለው ተሸላሚው አሁን ላይ የደረሰበት ደረጃ ጅምር በመሆኑ የትምህርት ደረጃውን በማሻሻል አገሩን በታማኝነትና በቅንንት እንደሚያገለግል ተናግሯል።

    በአጠቃላይ ውጤት 3.98 በማምጣትና 43 A+ በማስመዝገብ በ2ኛነት የተሸለመው የአርክቴክቸርና ከተማ ፕላን ትምህርት ክፍል ተመራቂ ቃለአብ ወንድሙ ታሪኩ በዓላማ መንቀሳቀስና ተግቶ መሥራት ለስኬት ያበቃል ብሏል። ሰሚራ ዲልቦ አወል ከኮኦፕሬቲቭ አካውንቲንግ እና ኦዲቲንግ ትምህርት ክፍል 3.94 ከሴቶች ከፍተኛውን ውጤት በማምጣት እንዲሁም ተመራቂ ዘሀራ ያሲን አማን ከኮምፒውተር ሣይንስ ትምህርት ክፍል 3.92 በማምጣትና 16A+ በማስመዝገብ ልዩ የወርቅ ሀብል ተሸላሚዎች ሆነዋል።

    በዕለቱ ከየትምህርት ክፍላቸው 1ኛ ለወጡ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ሽልማት፣ ከኢንስቲትዩት፣ ከኮሌጅና ከት/ቤት 1ኛ ለወጡ ምሩቃን የወርቅ ሜዳልያ፣ ከኢንስቲትዩት፣ ከኮሌጅና ከት/ቤት 1ኛ ለወጡ ሴት ምሩቃን ልዩ ሽልማት፣ በአጠቃላይ ሴት ምሩቃን መካከል ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገበች ምሩቅ የአንገት ሐብል ሽልማት እንዲሁም ከአጠቃለይ ምሩቃን ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገበው ምሩቅ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቷል።

    ምንጭ፦ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

    Anonymous
    Inactive

    የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ 6 ሺህ 824 ተማሪዎችን አስመረቀ
    —–

    አዲስ አበባ – የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በ42 የትምህርት ዘርፎች በመደበኛና በተከታታይ መርሃ ግብር ያስተማራቸውን 6 ሺህ 824 ተማሪዎችን ሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ.ም. አስመርቋል።

    በመጀመሪያ፣ በማስተርስና በዶክትሬት ዲግሪ ከተመረቁት አጠቃላይ ተማሪዎች መካከል 180 የሚሆኑት ከደቡብ ሱዳን፣ ሶማሌላንድ፣ ሶማሊያና የመጡ ናቸው። እነዚህ የውጭ ዜጎች በዩኒቨርስቲው የተማሩት የኢትዮጵያ መንግስት በሰጠው ነጻ የትምህርት እድል አማካኝነት ነው።

    በምረቃው ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ፍቅሬ ደሳለኝ ዩኒቨርሲቲው ትኩረቱን በሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት ላይ በማድረግ ዘንድሮ 29 ተማሪዎችን በዶክትሬት ዲግሪ ማስመረቁን ተናግረዋል።

    ዩኒቨርሲቲው የአንድ ፓርቲ አገልጋይ ነው የሚለውን አስተሳሰብ ለመቀየር በርካታ የገጽታ ግንባታ ታገባራት መከናወናቸውንም ጠቅሰው፥ ዩኒቨርሲቲው ለሁሉም ዜጎች ክፍት የሆነ የምሁራን መፍለቂያ አምባና የእውቀት ማዕከል ለማድረግ በትኩረት እየሠራን ነው ብለዋል።

    ዩኒቨርሲቲው ተቋቁሞ ሥራ ላይ በቆየባቸው ባለፉት 25 ዓመታት ከዲፕሎማ አንስቶ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ የትምህርት ደረጃዎች ከ35 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል።

    በአሁኑ ወቅት ትኩረቱን በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ላይ ያደረገው የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፥ የቅበላ አቅሙን በማሳደግ በስድስት የትምህርት ዘርፎች በዶክትሬት ደረጃ ትምህርት እየሰጠ ይገኛል።

    ዘንድሮ ከተመረቁት መካከል በ25 የእውቀት ዘርፎች በሁለተኛ ዲግሪ እና በቅድመ ምረቃ ደግሞ በ11 ዘርፎች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ይገኙበታል።

    በምረቃው ሥነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በዛብህ ገብረኢየሱስ እንዳሉት፥ መንግስት የጀመረውን አካባቢን የመንከባከብ ተግባር በጋራ እውን በማድረግ ኢትዮጵያን ለአሁኑና ለመጪው ትውልድ ምቹ የመኖሪያ ስፍራ መፍጠር ይጠበቅባቸዋል። ተማራቂ ተማሪዎችም አገራቸውን ወደፊት ለማራመድ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል።

    መንግስት በተለይ በመጪው ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም. 200 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል የያዘውን እቅድ ለማሳካት ተመራቂዎች የአካባቢያቸውንና የዩኒቨርሲቲውን ማኅበረሰብ በማስተባበር ችግኝ እንዲተክሉ ጥሪ አቅርበዋል። የሚተከሉት ችግኞችም የምርቃታችሁ ማስታወሻ ይሆናሉ ሲሉም አክለዋል።

    በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቱን የፈጸመው ተስፋዬ አባተ በተመረቀበት ሙያ አገሩን ለማገልገል ቁርጠኛ መሆኑን ተናግሮ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የቀረበውን የችግኝ ተከላ ጥሪ በመቀበል ኃላፊነቱን እንደሚወጣ ገልጿል። “ከዚህም ባለፈ በክረምት በበጎ ምግባር አገልግሎት ላይ በመሰማራት የሚጠበቅብኝን አስተዋጽኦ አበረክታለሁ” ብሏል።

    Anonymous
    Inactive

    መቐለ 70 እንደርታ የ2011 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ሆነ
    —–

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – መቐለ 70 እንደርታ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 30ኛ ሳምንት ዛሬ ድሬ ዳዋ ከነማን 2ለ1 በመርታት ዋንጫ አንስቷል።

    ከስሑል ሽረ ጋር የተገናኘው ፋሲል ከነማ 1ለ1 በሆነ አቻ ግብ ሲለያይ መቐለ 70 እንደርታ ድሬ ዳዋን 2ለ1 በሆነ ልዩነት በመርታት ነው አሸናፊ የሆነው።

    መቐለ 70 እንደርታ ከድሬ ዳዋ ከነማ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ጎሎቹን ያስቆጠሩት ለመቐለ 70 እንደርታ ኦሴይ ማውሊ (በጨዋታው የመጀመርያ የመጠናቀቂያ ደቂቃ ላይ በፍፁም ቅጣት ምት) እና አማኑኤል ገብረሚካኤል (በሀምሳ አራተኛው ደቂቃ ላይ በፍፁም ቅጣት ምት) ሲሆኑ፤ ለድሬ ዳዋ ከነማ ብቸኛዋን ጎል ያስቆጠረው ኤልያስ ማሞ (በሰባ ዘጠነኛው ኛው ደቂቃ ላይ) ነበር።

    መቀመጫውን መቐለ ከተማ ያደረገውና ራሱን በአዲስ መልክ በ2000 ዓ.ም. ካዋቀረ በኋላ በ 2010 ዓ.ም. ፕሪምየር ሊጉን የተቀላቀለው መቐለ 70 እንደርታ የእግር ኳስ ክለብ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ሲያሸንፍ ለመጀመርያ ጊዜው ነው።

    በፕሪምየር ሊጉ ማጠናቀቂያ ዕለት (ሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ.ም.) በተካሄዱ ጨዋታዎች ደደቢትን ያስተናገደው ሀዋሳ ከተማ 5ለ2 በሆነ ሰፊ ልዩነት ረቷል። ሲዳማ ቡና ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 3 ለ0፣ ኢትዮጵያ ቡና ከመከላከያ 3ለ4፣ ጅማ አባጅፋር ከደቡብ ፖሊስ 3ለ2 እና አዳማ ከተማ ከባህር ዳር ከተማ 0ለ3 ተለያይተው የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተጠናቋል።

    https://semonegna.com/wp-content/uploads/2019/07/Mekelle-70.jpg

    ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    Anonymous
    Inactive

    ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አስመረቀ
    —–

    ጂጂጋ (ሰሞነኛ) – ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ለ11ኛ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸው 2 ሺህ 107 ተማሪዎች አስመረቀ።

    ዩኒቨርሲቲው ሰኔ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል 101 በሁለተኛ የዲግሪ መረሀ ግብር የተማሩ ናቸው።

    በምረቃ ሥነ ስርዓት ወቅት የዩኒቨርሲቲው ቦርድ አመራር አባል ዶክተር አብዲቃድር ኢማን ባስተላለፉት መልዕክት “ተመራቂዎቹ በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው በንድፍ ሀሳብና በተግባር የቀሰሙትን ዕውቀት ለህብረተሰብ ለውጥ እና እድገት ማዋል ይጠብቅባቸዋል” ብለዋል።

    የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት አቶ ኢልያስ ኡመር በበኩላቸው ተቋሙ ያስመረቃቸው ተማሪዎች ች በ ምህንድስና፣ በጤና ሳይንስ፣ በግብርና፣ በሕክምና እና በሌሎችም የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸው መሆኑን አስረድተዋል።

    ዩኒቨርስቲው ከመደበኛው ሥራው ሳይወሰን በክልሉ ሰባት ከተሞች ማዕከላትን ከፍቶ ለማ ኅበረሰቡ የከፍተኛ ትምህርት ፍላጎት ለማሟላት እየሠራ መሆኑን አመልክተዋል።

    በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂና አስተዳደር ተመራቂ ወጣት አብዲ መሀመድ በሰጠው አስተያየት፥ ከዩኒቨርስቲው በቀሰመው ዕውቀት ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር ሥራ ለመፍጠር ጥረት እንደሚያደርግ ተናግሯል።

    ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የሚያስተምራቸው ከ24ሺህ 400 በላይ ተማሪዎች እንዳሉት በምረቃው ሥነስርዓት ወቅት ተገልጿል።

    ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ)

    Anonymous
    Inactive

    የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወሰናቸውን ኢ-ፍትሃዊ እርምጃዎችን እንዲመረምር እና ያላአግባብ የተወሰነበትን ፎርፌ እንዲያነሳ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የጠየቀ ሲሆን፥ ያቀረባቸው ቅሬታዎች ምላሽ እስከሚያገኙ ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮች ራሱን ማግለሉን አስታውቋል።

    አዲስ አበባ – የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ላቀረባቸው ጥያቄዎች ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮቸ ራሱን ማግለሉን አስታወቀ።

    የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር ሰኔ 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሊግ ኮሚቴ የቅዱስ ጊዮርጊስን የሜዳ ተጠቃሚነት ለማሳጣት ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ሊያደርገው የነበረን ጨዋታ በዝግ ወይም አዳማ ከተማ ላይ ተጫወቱ በማለት ሁለት ጊዜ እንዲቋረጥ አድርጎል ብሏል።

    ይህን ጨዋታ ከዚህ በፊት የተቋረጡ የሌሎች ክለቦች ጨዋታወችን ባስተናገደበት ሁኔታ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብን አላስተናገደም ሲል በፌዴሬሽኑ ላይ ቅሬታውን አቅርቧል።

    እንዲሁም በ29ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ለፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ የተሰጠው ፎርፌ አግባብነት የሌለውና አድሏዊ መሆኑንም ነው በመግለጫው ያመላከተው።

    አዲስ ከመጡት የፌዴሬሽኑ አመራሮች ጋር በመተባበር፣ በመቻቻል እና በመተጋገዝ ለመሥራት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ ቆይቷልም ነው ያለው።

    በመሆኑም ፌዴሬሽኑ የወሰናቸውን ኢ-ፍትሃዊ እርምጃዎችን እንዲመረምር እና ያላአግባብ የተወሰነበትን ፎርፌ እንዲያነሳ የጠየቀ ሲሆን፥ ያቀረባቸው ቅሬታዎች ምላሽ እስከሚያገኙ ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮች ራሱን ማግለሉን አስታውቋል።

    ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ. / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
    —–
    ተመሳሳይ ዜናዎች፦

    የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ


    Semonegna
    Keymaster

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – በአዳዲስ የቢዝነስና የሥራ ፈጠራ ሃሳቦች አፍላቂነታቸውና በፈር-ቀዳጅ ኢንቬስተርነታቸው (entrepreneur) በሚታወቁት ኢትዮጵያዊው ኢኮኖሚስትና ባለሃብት በአቶ ኤርሚያስ አመልጋ የሕይወት ታሪክና ሥራዎች ዙሪያ የሚያጠነጥነውና በደራሲና ጋዜጠኛ አንተነህ ይግዛው የተጻፈው < የማይሰበረው – ኤርሚያስ አመልጋ > የተሰኘው የሕይወት ታሪክ (biography) መጽሐፍ ከሐምሌ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በገበያ ላይ ይውላል።

    አጠቃላይ ዝግጅቱ ከስድስት ዓመታት በላይ ፈጅቶ የተጠናቀቀው ይህ መጽሐፍ፥ ከወላጆቻቸው የበስተጀርባ ታሪክ አንስቶ የአቶ ኤርሚያስ አመልጋን የልጅነት ሕይወትና አስተዳደግ፣ የወጣትነት ዘመንና የትምህርት ቆይታ እንዲሁም ወደ አሜሪካ አቅንተው ከዘበኝነትና የዩኒቨርሲቲ ተማሪነት እስከ ግዙፉ የዓለማችን የፋይናንስ ማዕከል ዎልስትሪት (Wall Street) የኢንቨስትመንት ባንኪንግ ስመጥር ባለሙያነት የዘለቁበትን የረጅም ዓመታት ጉዞ የሚያስቃኝ ሲሆን፥ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ ከ20 ዓመታት በላይ የተጓዙበትን በስኬትና በውድቀት የታጀበ፣ ፈተናና ውዝግብ ያልተለየው ረጅም የሕይወት ጎዳናም በዝርዝር ይዳስሳል።

    ኤርሚያስን የትኛው “ወንጀል” ሊያሳስረው ይችላል?

    አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በተለይም ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ የወጠኗቸውን አዳዲስና ሰፋፊ የፋይናንስ፣ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕቅዶቻቸውን ከዳር ለማድረስ ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ጉዞ ውስጥ ያጋጠሟቸውን እሾህ አሜካላዎች፣ የተጋፈጧቸውን ፈተናና እንቅፋቶች በዝርዝር የተረኩበት መጽሐፉ፣ ከባለታሪኩ የግልና የሥራ ሕይወት ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም ተሰምተው የማይታወቁ በርካታ አዳዲስና አነጋጋሪ መረጃዎችን ያካተተ ነው።

    በሁለት ክፍሎች ተከፋፍሎ የቀረበውና 12 ዋና ዋና ምዕራፎች ያሉት < የማይሰበረው – ኤርሚያስ አመልጋ > የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ፣ “ማረፊያ አንቀጾች” እና “ድህረ-ታሪክ” የሚሉ ተጨማሪ ንዑሳን ክፍሎችን ጨምሮ አጠቃላይ የገጽ ብዛቱ 394 ነው።

    < የማይሰበረው – ኤርሚያስ አመልጋ > በአዲስ አበባና በሁሉም የክልል ዋና ዋና ከተሞች በሚገኙ መጽሐፍት መደብሮችና በአዟሪዎች፣ በአዲስ አበባ በሁሉም የዳሽን ባንክ ቅርንጫፎችና በሸዋ ሱፐርማርኬቶች፣ በስልክ ትዕዛዝ የቤት ለቤት እደላና በአማዞን ድረ-ገጽ አማካይነት ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የሚሸጥ ሲሆን፣ የመሸጫ ዋጋውም 300 ብር እንደሆነ ተነግሯል።

    ዘመን ባንክ እንደ ይሁዳ – (ኤርሚያስ አመልጋ – ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት)

    በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የታሸገ ውሃ “ሃይላንድ” ለገበያ በማቅረብ እንዲሁም “ዘመን ባንክ” እና “አክሰስ ሪል ስቴት”ን ጨምሮ ባቋቋሟቸው የተለያዩ ኩባንያዎች የሚታወቁት አወዛጋቢው ኢኮኖሚስት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፥ ከብረታ ብረት ኮርፖሬሽን የሙስና ክስ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ከወራት በፊት በቁጥጥር ስር መዋላቸውና በአሁኑ ወቅትም በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሆነው የፍርድ ሂደታቸውን በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።

    ጸሃፊው ደራሲና ጋዜጠኛ አንተነህ ይግዛው ከዚህ ቀደም “መልስ አዳኝ” እና “ባቡሩ ሲመጣ” የተሰኙ የአጫጭር ልቦለድ ስብስብ መጽሐፍትን ለንባብ ያበቃ ሲሆን፥ ለ54 ተከታታይ ሳምንታት በፋና ኤፍ ኤም 98.1 የተላለፈውንና “ስውር መንገደኞች” የተሰኘውን ተከታታይ የሬዲዮ ድራማ በደራሲነትና በተዋናይነት ለአድማጭ ማብቃቱም ይታወሳል።

    ለተጨማሪ መረጃ፦
    Email: yemayseberew@gmail.com, amelgaermiyas283@gmail.com
    Facebook: Ermyas Tekil Amelga
    ሰሞነኛ ኢትዮጵያ

    የማይሰበረው - ኤርሚያስ አመልጋ


    Anonymous
    Inactive

    ክብርት ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት በዓል ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
    —–

    ክብርት ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምርቃት በዓል ላይ በመገኘት ለ2011 ዓ.ም. ምሩቃን (Class of 2019) “የዓመታት ልፋታችሁ ውጤት ለሚታዩበት ዕለት እንኳን በቃችሁ፤ እንኳን ደስ አላችሁ” በማለት የደስታ መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል።

    ምሩቃኑ ሚዛናዊና ምክንያታዊ በሆነ አስተሳሰብ በመመራት አገራችን ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ፈታኝ ሁኔታ ለመታደግ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ፕሮፌሰር ሂሩት ጥሪ አቅርበዋል።

    መማር ማለት እውቀት መሰብሰብ ብቻ አይደለም ያሉት ሚኒስትሯ፥ የተማረ ሰው በእያንዳንዱ በሚያጋጥመው ነገር ላይ ጠለቅ ያለ ዕይታ ያለውና ለሁሉም ነገር በቂ ምርምር በማድረግ ሚዛናዊና ምክንታዊ መፍትሄ የሚፈልግ በመሆኑ ተመራቂ ተማሪዎች የቀሰሙትን ዕውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር ለአገርና ለወገናቸው እንዲሰሩበትም አስገንዝበዋል።

    የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሃይማኖት ዲሳሳ በበኩላቸው፥ ዩኒቨርሲቲው ከ3ኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች (3rd Generation Universities) አንዱ ሲሆን ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ዘንድሮ ለ6ኛ ጊዜ 2,711 ተማሪዎችን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ማስመረቁን ገልጸዋል።

    ፕሬዚዳንቱ ዘንድሮ በዩኒቨርሲቲው ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግሮች ተቋቁሞ የመማር ማስተማር እና የማኅበረሰብ አገልግሎት ሥራዎችን በአግባቡ በመፈፀም ለዚህ እለት እንዲበቃ ትብብርና ድጋፍ ላደረጉት የአካባቢው ህብረተሰብ፣ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ፣ የጸጥታ ኃይሎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

    ተመራቂ ተማሪዎችም በቀሰሙት ዕውቀት እና ክህሎት ህብረተሰባቸውን ከማገልገል ባሻገር ለሀገሪቱ ሰላምና እድገት መረጋገጥ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

    ምንጭ፦ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር / ሰሞነኛ ኢትዮጵያ
    null

    Anonymous
    Inactive

    ኢትዮጵያ ውስጥ የደረስንበትን የሞራል ድቀት፣ የዕውቀት ውድቀት እና የሰብዓዊነት ውርደት የሰሞኑ ሞት ፍንትው አድርጎ አሳይቷል
    (ሙሉዓለም ጌታቸው)

    የሞራል ድቀት

    • ገዳይ እና ሟች እኩል ጀግና የሚባልበት አገር ሆናለች ኢትዮጵያ። ዳቦ ስለራበኝ በዘላቂነት ዳቦ ለመብላት የዳቦ ቤቱን ባለቤት ገድዬ ዳቦውን ሁሉ ልውረስ የሚል ሌባ ወንጀለኛ ተብሎ ሀገር ካላወገዘው ወንጀለኛ ማን ሊባል ነው? ከእስር አስፈትተው ሹመት በሰጡ፣ 27 ዓመት ቃል ሳይተነፍሱ፥ ትላንት በተፈጠረ ዕድል ‘አማራ አማራ’ ብለው እንደ ጀግና ሲታዩ ዝም ባሏቸው በጥይት አረር ጨረሷቸው። እነዚህን የ21ኛው ዘመን አውሬዎችን በክብር መቅበር እና ጀግና ማለት ካላስነወረ ምን ሊያስነውር ነው? ‘የትም ፍጭው ዱቄቱን አምጭው፣’ ያነገብከው ዓላማ እንጂ ዓላማህን የምትፈጽምበት መንገድ ግድ አይሰጠኝም እንደሚል ሰው በዚህ ምድር ላይ አረመኔ የለም። ኦሳማ ቢን ላደን ያነገበውን ዓላማ ምናልባት ሁላችን የምንደግፈው እና በሞራልም ደረጃ ልክ የሆነ ነው። ያን ለመፈጸም የሄደበት መንገድ፣ የተጠቀመበት መሣሪያ ግን ርኩስ እና አረመኔ አስብሎታል። ሰብዓዊ የሆነ ሁሉ ሰው ይሄን ያምናል። ባዶ እጃቸውን የነበሩ፣ ለአገር ለወገን እረፍት አጥተው የሠሩ ግለሰቦችን አረመኔያዊ በሆነ መልኩ መግደል ሰይጣንነት ነው። የትኛውም ዓይነት ዓላማ ይሄን ግፍ ጽድቅ አያደርገውም። አሳምነው ጽጌን እንደ ጀግና የቆጠሩ ለእኔ ክርስቶስን እንደሰቀሉ መንጎች ናቸው። ክርስቶስን የሰቀሉ ግብዝ አይሁዶች እግዚአብሔርን እያገለገሉ ያሉ ይመስላቸው ነበር። ለዛ ግፋቸው መበተን እጣ ፈንታቸው ሆነ። ዛሬ ከእነዚህ ግፈኞች ጋር መተባበር የደም ዋጋን በራስ ላይ መሳብ ነው። ገዳይም ተገዳይም ጀግና ሊሆን አይችልም፤ ካልዞረብን በቀር።

    የዕውቀት እጥረት

    • የኢትዮጵያ መሪዎች በ21ኛው ክፈለ ዘመን ሀገርን የሚያክል ነገር በ“try and error” እየመሩ ነው። የእነሱን ነፍስ ብቻ ሳይሆን በፍጥነት አገሪቷን ገደል እየከተቱ ነው። 8 እና 9 ዓመት ከጨለማ በቀር ሌላ ነገር ያላዩን ግለሰቦች እና ከመንግስት ቢሮክራሲ ተለያይተው የነበሩ ሰዎችን በግዙፍ ስልጣን ላይ አሰቀመጡ። በሰለጠነው ዓለም ቢሆን ከፍተኛ የህክምና እርዳታ የሚደረግላቸውን ግለሰቦች በጡዘት ላይ ያለ አገርን እንዲመሩ ስልጣን አንበሻበሿቸው። ኤርትራ በርሀ ሊታገል የሄደን ወጣት ጉርጓድ ቆፍረው የሚቀብሩ ግለሰቦችን ሽግግር ምሩ ብለው ስልጣን ሰጡ። የቀደመው መንግስት ካጠፋው ይልቅ ይሄን ጥፋት ልናርም እየሄድንበት ያለው መንገድ የበለጠ ጥፋት እየከሰተ ነው።
    • ዲሞክራሲ ባህል ነው። ይሄ ባህል ፈጽሞ ባልገባው ማኅበረሰብ ፊት ሰው ሆኖ መታየት የደካማነት መገለጫ ነው። መሪዎቻችን ሆይ ዲሞክራሲ ያለንን ነገር እንዲያሳጣን ሳይሆን ባለን ነገር ላይ እንዲጨምርልን ተደርጎ መተግበር ካልቻለ፥ ዲሞክራሲ ለእኛ የሞት የሽረት ጉዳይ አይደለም። እባካችሁ በዲሞክራሲ ሳይሆን በዕውቀት ይሄን ሕዝብ ምሩት።

    የሰብዓዊነት ውርደት

    • ዘረኞች ስለሰው አንዳች ክብር እንደሌላቸው ድጋሚ ያየንበት ወቅት ነው። ጄነራል ሰዓረ መኮንን ድንቅ ኢትዮጵያዊ ነው። የሞተው ለኢትዮጵያዊነት በመቆሙ ነው። እንደነ አሳምነው ባለማበዱ ነው። እንደነሱ በዘር ልክፍት ገምቶ ዙሪያውን በራሱ ወገን እና ዘሮቼ በሚላቸው ሰዎች ተከቦ ቢሆን ኖር ዛሬ የተከሰተው ባልደረሰበት ነበር። አንዳንዶች ግን ዛሬም በሱ ሞት ፖለቲካ በመሥራት የእሱን ድንቅ ሰብዓዊነት ሊያራክሱ ይሞክራሉ። ምናለ ሞቱን እንኳ ቢያከብሩለት? ምናለ ለጥቂት ጊዜ እንኳ የሞተለትን ኢትዮጵያዊነት እና ሰብዓዊነት ከፍ ቢያደርጉ?
    • አንድ ቀን መንገድ ላይ የፈሰሰውን የአማራ የኔቢጤ እና መስኪን ለመርዳት፣ በየጎዳናው የወደቀውን የአማራን ተወላጅ ረሃብ ለመቅረፍ ገንዘብ አወጥቶ የማያቅ ሁላ ‘አማራ አማራ’ እያለ በውንድማማቾች መካከል ጥላቻን እየዘራ ያለ፥ ለሞታቸው ከቶ ደንታ የሌለው፣ በምዕራብ አገራት ሸሽቶ ተሰዶ እነሱ የከፈሉትን መስዋዕትነት በጣቱ ለመንካት አቅም የሌለው ሰው ‘ዘሬ!’ ሲል መስማት እጅግ ያማል። የግብዞች መዓት ኢትዮጵያን እያወካት ነው።

    ሙሉዓለም ጌታቸው

    የሞራል ድቀት፣ የዕውቀት ውድቀት እና የሰብዓዊነት ውርደት የሰሞኑ ሞት ፍንትው አድርጎ አሳይቷል


     

    Semonegna
    Keymaster

    የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል
    —–

    አዲስ አበባ – የተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎቻቸውን ሰኔ 22 ቀን 2011 ዓ.ም. አስመርቀዋል።

    በዕለቱ ተማሪዎቻቸውን ካስመረቁ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥም የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ፣ መቱ ዩኒቨርሲቲ፣ ዲላ ዩኒቨርሲቲ እና አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ይገኙበታል።

    የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 313 ተማሪዎቹን በዕለቱ አስመርቋል። ከተመረቁት ውስጥም 1 ሺህ 112 በቅድመ ምረቃ መርሃ ግብር (በመጀመሪያ ዲግሪ) ያስመረቀ ሲሆን፥ 201 ተማሪዎችን ደግሞ በድህረ ምረቃ መርሃ ግብር ነው ያስመረቀው።

    ጅማ ዩኒቨርሲቲም በዕለቱ በመጀመሪያ ዙር ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 683 ተማሪዎቹን አስመርቋል። ከእነዚህም ውስጥ 341 በድህረ ምረቃ ሲሆን፥ 1 ሺህ 11 ደግሞ ሴቶች መሆናቸው ታውቋል።

    በተመሳሳይ ዲላ ዩኒቨርሲቲም በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 4 ሺህ 726 ተማሪዎቹን በዕለቱ አስመርቋል። በዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የምረቃ በዓል ላይ የተገኙት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስተር ዲኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ፥ በዘንድሮው ዓመት በመላው ሀገሪቱ ከ175 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንደሚመረቁ አንስተዋል። ተመራቂ ተማሪዎች ለሀገራቸው የሚሰሩ ሊሆኑ እንደሚገባም ፕሮፌሰር አፈወርቅ መልእክት አስተላልፈዋል። ዲላ ዩኒቨርሲቲ በዕለቱ ካስመረቃቸው ተማሪዎቹ ውስጥ 500 ተማሪዎችን በሁለተኛ ዲግሪ ነው ያስመረቃቸው።

    ወለጋ ዩኒቨርሲቲም በዕለቱ በተለያየ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 3 ሺህ 682 ተማሪዎቹን በዕለቱ አስመርቋል። ከተመረቁት ተማሪዎች ውስጥ 2 ሺህ 139 ሴቶች ሲሆኑ 1 ሺህ 543 ደግሞ ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል። በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው 295 ተማሪዎችን በሁለተኛ ዲግሪ ያስመረቀ2 ሲሆን፥ 8 ተማሪዎችን ደግሞ በ3ኛ ዲግሪ ወይም በዶክትሬት ዲግሪ አስመርቋል።

    መቱ ዩኒቨርሲቲም በተለያየ የትምህርት መሰኮች ሲያሰለጥናቸው የነበረውን ከ2 ሺህ 300 በላይ ተማሪዎቸ በዛሬው ዕለት አስመርቋል። በምረቃ ሥነ-ስርዓት ላይ የተገኙት ግብርና ሚኒስተር ዲኤታና የመቱ ዩኒቨርሰቲ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሳኒ ሬዲ መንግስት ለሰው ሀብት ልማት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥው እየሠራ ባለበት መመረቃቸውንና ከተመራቂ ተማሪዎች የሚጠበቀው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል።

    የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ተካልኝ ቃጄላ በበኩላቸው፥ ዩኒቨርሲቲው በዚህ ዓመት ብዙ ፈታኝ የሆኑ የውስጥና የውጭ ተግዳሮቶችን አልፎ ለዚህ መብቃቱን አስታውሰዋል።

    በተመሳሳይ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ 2 ሺህ 714 ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት መርሓ ግብሮች አስመርቋል። ከነዚህ ውስጥ 930 ሴት ተመራቂዎች መሆናቸው ታውቋል። ዩኒቨርሲቲው አሁን ለ6ኛ ጊዜ እያስመረቀ ሲሆን ከተመሰረተበት ከ2004 ዓም ጀምሮ አጠቃላይ 12 ሺ 450 ተማሪዎችን አስመርቋል። በዕለቱ በተካሄደው የምረቃ ሥነ-ስርዓት ላይ የሳይንስ እና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያምን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ተገኝተዋል። ፕሮፌሰር ሂሩት ኢትዮጵያ ካለችበት ሁኔታ እንድትወጣ የተማረው ሀይል ዋነኛ አካል ነው ብለዋል።

    ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

    Anonymous
    Inactive

    አክሱም ዩኒቨርሲቲ ኤርትራዊያን ተማሪዎችን አስመረቀ
    —–

    አክሱም ዩኒቨርሲቲ ኤርትራዊያን ተማሪዎችን አስመረቀ። ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ያስመረቃቸው 14 ኤርትራዊያን በመጀመሪ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ናቸው። አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) የሰጡ ኤርትራዊያን ተመራቂዎች እንዳሉት በቀጣይ የሁለቱን ሀገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ኃላፊነታቸውን ይወጣሉ።

    በፓለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት የተመረቀው ዮናስ አሸብር እንዳለው የሁለቱ ሀገራት የሕዝብ ለሕህዝብ ግንኙነት ብዙ ዓመታት ያስቆጠረ ነው።

    ሀገራቱ በመካከላቸው ተፈጥሮ በነበረው አለመግባባት ከ20 ዓመታት መለያየት በኋላ ዳግም ግንኙነታቸውን ማደሳቸውን አስታውሶ፥ “በቀጣይ የሀገራቱን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ድልድይ ሆነን እንሠራለን” ብለዋል።

    ከዩኒቨርሲቲው በቢዝነስ ማኔጅመንት የተመረቀው ዮሐንስ ጉዕሽ በበኩሉ፥ በኢትዮጰያ መንግስት የትምህርት ዕድል በማግኘቱ ደስታ እንደተሰማው ገልጾ “የጋራ ባህልና እሴት ያላቸው የኢትዮጰያና የኤርትራን ህዝቦችን ማለያየት አይቻልም” ብሏል።

    በቀጣይም የሁሉቱ ሀገራት የጋራ ልማትና ተጠቃሚነት ለማሰቀጠል የበኩልን እንደሚወጣ ተናግሯል።

    ምንጭ፦ ኢዜአ

Viewing 15 results - 421 through 435 (of 730 total)