Search Results for 'ኢትዮጵያ'

Home Forums Search Search Results for 'ኢትዮጵያ'

Viewing 15 results - 46 through 60 (of 730 total)
  • Author
    Search Results
  • Semonegna
    Keymaster

    ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ 2891 ተማሪዎችን በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመረቀ

    ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በድህረ ምረቃ፣ በቅድመ ምረቃ እና ዲፕሎማ ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን 2891 ተማሪዎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ሐምሌ 10 ቀን፥ 2014 ዓ.ም በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስመርቋል።

    የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶክተር ብርሃነመስቀል ጠና ለዕለቱ ተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ባሰሙበት ንግግራቸው፥ ነባሩ እና አንጋፋው ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ በማታና በተከታታይ የዲፕሎማ፣ የዲግሪ እና የማስትሬት መርሐግብሮች ትምህርታቸውን በሚገባ አጠናቀው፣ አስፈላጊውን የምረቃ መስፈርት አሟልተው በዕለቱ ለምረቃ የበቁት የ2014 ዓ.ም ተመራቂዎች 2891 መሆናቸውን ተናግረዋል። ከእነዚህም ተመራቂዎች መካከል ወንድ 1409፣ ሴት ደግሞ 1482 ሲሆኑ፣ ይህም የሴት ተመራቂዎች ቁጥር ብልጫ ያለው መሆኑንና ዩኒቨርሲቲውም ለሴቶች ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጥ ያሳያል ሲሉ ዶክተር ብርሃነመስቀል ተናግረዋል። በመጨረሻም ፕሬዝዳንቱ የዕለቱ ተመራቂዎች በዩኒቨርሲቲው አዲሱ ስያሜ፣ ተልዕኮ፣ ሎጎ እና ህብረ ዝማሬ በመመረቃቸው የተቋሙ ታሪክ አካል እንደሚያደርጋቸው አስገንዝበዋል።

    የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የዕለቱ የክብር እንግዳ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአዲስ መልክ እየተዋቀረ ያለው ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሀገሪቱን የትምህርት ችግሮች ለመቅረፍ በከፍተኛ ደረጃ ኃላፊነት የተጣለበት በመሆኑ፣ ይህንን ልዩ ተልዕኮውን ለመወጣት በሚያደርገው ጥረትም የትምህርት ሚኒስቴር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግለት ገልጸዋል።

    በሥነ ሥርዓቱ ላይም በትምህርታቸው ብልጫ ላሳዩ ተመራቂዎች የዋንጫ እና ሌሎች ሽልማቶች ተሰጥቷቸዋል። እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የሽግግር ወቅት ልዩ ልዩ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላትም የዕውቅና ምስክር ወረቀትና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡

    ከከፍተኛ ትምህርት ዜና ሳንወጣ፥ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጀርመን ስቱትጋርት ከተማ ውስጥከሚገኘው የሆኸንሃየም ዩኒቨርሲቲ (University of Hohenheim) ጋር የአጋርነት ስምምነት ተፈራርሟል።

    የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ ከዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝደንት እና ከዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች ጋር በመሆን በጀርመን ሀገር በግብርናና በሥነ ምግብ ሳይንስ ቀዳሚ ከሆነው ከሆኸንሃየም ዩኒቨርሲቲ (University of Hohenheim) ጋር ላለፉት 8 ዓመታት ሲተገበር በነበረው የCLIFOOD ፕሮጀክት ወርክሾፕ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ተመራማሪ በዶ/ር ስንታየሁ ይግረም አስተባባሪነት የሚመራው ይህ የCLIFOOD ፕሮጀክት በአየር ንብረት ለውጥና በምግብ ዋስትና ዙሪያ የሚሠራ ሲሆን ለ27 የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሦስትኛ ዲግሪና የድኅረ-ዶክትሬት (postdoctoral)  ትምህርት እንዲማሩና፣ የዩኒቨርሲቲው የምርምር ላቦራቶሪዎች አቅም እንዲያድግ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡ በዚሁ አጋጣሚ ሁለቱ አንጋፋ የትምህርትና ምርምር ተቋማት ግንኙነታቸውን ለማደስና በሌሎች ዘርፎችም አብረው ለመሥራት የሚያስችላቸውን ውል ተፈራርመዋል፡፡

    ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ

    Semonegna

    በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሪፈራልና ማስተማሪያ ሆስፒታል የእድሳት ግንባታ ሥራ በይፋ ተጀመረ

    ሰሞነኛ (ዲላ ዩኒቨርሲቲ) – በዲላ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሪፈራልና ማስተማሪያ ሆስፒታል የእድሳት ግንባታ ሥራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሄደ። የእድሳት ሥራው መጀመሩን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ይፋ አድርገዋል።

    ዶ/ር ችሮታው ባደረጉት ንግግር፥ ሆስፒታሉ ያሉበትን መሠረታዊ ችግሮች በትኩረት መፍታት ከተቋሙ ዋና ዋና ተግባራት አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

    በተለያዩ ሀገራዊና ተቋማዊ ምክንያቶች ግንባታው ቶሎ ያልተጠናቀቀውን አዲሱን የሕክምና እና ማስተማሪያ ሆስፒታል ለማጠናቀቅ ከሚደረገው ጥረት በተጓዳኝ ነባሩን ሆስፒታል በልዩ ሁኔታ እድሳት አድርጎ ለታካሚሆችና ለአካሚዎች ጭምር በሚመጥን ሁኔታ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ ይሠራል ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።

    ነባሩ ሆስፒታል አሁን ባለበት ደረጃ የጌዴኦ ዞንን እና አጎራባች አካባቢዎችን ማኅበረሰቦች የሕክምና ፍላጎት ለማስተናገድ ችግሮች እንዳሉ የሚታወቅ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ችሮታው፥ ስለሆነም በሆስፒታሉ ሥራ አመራር ቦርድ ታምኖበት አጠቃላይ የእድሳት ሥራው መንግሥት በሚፈቅደው የፋይናንስ ሂደት አልቆ ዛሬ [ሐምሌ 5 ቀን፥ 2014 ዓ.ም] በይፋ እንዲጀመር ተደርጓል ብለዋል።

    ዶ/ር ችሮታው አክለውም፥ እንደ ሀገር ከፍተኛ የሆነ የግንባታ ዘርፉ መቀዛቀዝ ውስጥ ቢሆንም ሆስፒታሉ ካለበት ደረጃ እንዲሁም ከሕብረተሰቡ የሕክምና አገልግሎት አንገብጋቢ ጥያቄ አንፃር አዲሱ እንሰኪጠናቀቅ ነባሩን ሆስፒታል በልዩ ሁኔታና በጥራት አድሶ ጥቅም ላይ ማዋል በትኩረት የሚሠራ ነው ብለዋል። ለዚህም ሥራውን በተቀላጠፈ እና ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ አድሶ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚመለከተው ሁሉ በርብርብ እንደሚሠራ ተገልጿል።

    የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ አባል አቶ አብዮት ደምሴ በበኩላቸው፥ ሆስፒታሉ ለጌዴኦ ዞን ብቻ ሳይሆን ለአጎራባች ክልሎች ጭምር አገልግሎት ሰጪ በመሆኑ “መከፈል ያለበት መስዋዕትነት ሁሉ ተከፍሎ በአጭር ጊዜ ውስጥ እድሳቱ እንዲጠናቀቅ ቦርዱም ሆነ የዞን አመራሩ ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል” ብለዋል። የሥራ ተቋራጭ ድርጅቱ የተጣለበት ኃላፊነት ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው፥ የዩኒቨርሲቲው አመራር፣ የዞኑና አካባቢው አመራር እንዲሁም ሕብረተሰቡ በጋራ ተባብረው ውጤታማ የሆነ እድሳት እንዲከናወን ይሠራሉ ብለዋል።

    የዲላ ከተማ ከንቲባና የሆስፒታሉ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተስፋፅዮን ዳካ በበኩላቸው፥ ሆስፒታሉ ብዙ ማኅበረሰብ የሚገለገልበት ሆኖ ሳለ ከጊዜ ወደ ጊዜ አገልግሎት አሰጣጡ እየተዳከመ ከአቅም በታች የሆነ አገልግሎት እየሰጠ መጥቷል፤ ስለሆነም ከዚህ ችግር እንዲወጣ እና ሕብረተሰቡ ማገኘት ያለበትን አገልግሎት የመስጠት አቅሙን በተሻለ ለመመለስ በርብርብ ይሠራል ብለዋል።

    የእድሳት ሥራውን ለማከናወን ውል የወሰደው ደሳለኝ አሥራደ ህንጻ ሥራ ተቋራጭ የተባለ ድርጅት ሲሆን ተወካዩ አቶ ፍጹም እምሩ ሆስፒታሉ ከአምስት ሚሊዮን ህዝብ በላይ የሚታከምበት ብቸኛ የዞኑ ሆስፒታል እንደመሆኑ የእድሳት ግንባታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለማስረከብ በትኩረት እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

    ተወካዩ አክለውም የተሻለ ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች በመመደብ በተሻለ ጥራትና በተፋጠነ ጊዜ ግንባታውን አጠናቀው በማስረከብ ሕብረተሰቡ እና ዩኒቨርሲቲው የጣሉብንን አደራ እንወጣለን ነው ያሉት።

    የዲላ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ፕሮጀክት ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ኢንጂነር በፍቃዱ መኩሪያ በዕለቱ የእድሳት ግንባታውን አስመልክቶ ባቀረቡት ገለፃ የሆስፒታሉን አጠቃላይ ገፅታ በከፍተኛ ጥንቃቄ ጥናት ተደርጎ ዲዛይን ተሠርቷል ብለዋል።

    ይሄው የእድሳት ዲዛይን ለጤና ሚኒስቴር ቀርቦ ከተገመገመ በኋላ የሚጠበቀውን ደረጃ ማሟላቱ በመረጋገጡ የእድሳት ግንባታው መፈቀዱን ገልፀው፣ በጥናቱ የተለየቱን ችግሮች የሚፈታ እድሳት እንደሚሠራ እና የተወሰኑ ተጨማሪ አዳዲስ ግንባታዎችም እንደተካተቱ አስረድተዋል።

    በእድሳት ግንባታ ሥራ ማስጀመሪያ መርሃግብሩ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሆስፒታሉ የሥራ አመራር ቦርድ ኃላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲውና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሆስፒታሉ ማኅበረሰብ አካላት የተገኙ ሲሆን ግንባታው መጀመሩን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ይፋ አድርገዋል።

    ምንጭ፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ

    የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሆስፒታል እድሳት ተጀመረ

    Semonegna
    Keymaster

    ሰሞኑን የወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውድቅ ተደረገ፤ ዕጣ አወጣጡ ላይ ችግር የፈጠሩ ባለሙያዎችም በቁጥጥር ስር ዋሉ

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰሞኑን የወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውደቅ መደረጉን አስታውቋል። ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም የወጣው የ20/80 እና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣን አስተዳደሩ ውድቅ ማድረጉን ነው ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያስታወቁት።

    ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ የተፈጠረው ስህተት ሕዝቡ በመንግሥት ላይ እምነት እንዲያጣ ለማድረግ ታስቦ የተሠራ የፖለቲካ ሸፍጥ መሆኑን በመግለጽ፥ በጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ላይ የተፈጠረውን ስህተት በተመከለተ ሐምሌ 6 ቀን፥ 2014 ዓ.ም መግለጫ ሰጥተዋል።

    የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ነዋሪዎችን የቤት ፍላጎት ለማሟላት በ14ኛው ዙር የ20/80 እንዲሁም የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለ25 ሺህ 491 እድለኞች ዕጣ ማውጣቱ ይታወሳል።

    በመረጃ መረብ ደኅንነት አስተዳደር (Information Network Security Agency /INSA/) አስተባባሪነት የተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ ዕጣው የወጣበት መንገድ/ሂደት (system) ሙያዊ ሂደትን ያልተከተለ መሆኑን አረጋግጧል። ዕጣው የወዳበት ሂደት ሲበለጽግ ቅድመ ማበልጸግ፣ በማበልጸግ ወቅት፣ ከበለጸገ በኋላ ያሉ የኦዲትና የማረጋገጥ የኢንዱስትሪ ሂደቶችን የተከተለ አይደለም ተብሏል።

    የአጣሪ ኮሚቴው አስተባባሪ አቶ በኃይሉ አዱኛ ሙሉ ሂደቱ በአንድ ግለሰብ ብቻ የተከናወነና በሚመለከተው የመረጃ መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ያልጸደቀ መሆኑን አረጋግጠናል ብለዋል። ሂደቱ የደኅንነት ፍተሻን ያላለፈ፣ የበለጸገበትና ዕጣው የወጣበት መንገድ ትክክለኛ አካሄድ ያልተከተለ እንዲሁም የኢንተርኔት ግንኙነት ያለው መሆኑ ተዓማኒነቱን ያጎድለዋል ነው ያሉት።

    የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዳሉት፥ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ ማውጣት ሂደቱ ግልጽና ፍትሃዊ እንዲሆን ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም ተገንብቷል። ይሁን እንጂ በግለሰብ አመራርና ባለሙያዎች አማካኝነት የቴክኖሎጂ ውንብድና ተፈጽሞ ለዓመታት ካለው ቀንሶ የቆጠበውን ሕብረተሰብና ከተማ አስተዳደሩን ያሳዘነ ድርጊት መፈጸሙን ተናግረዋል።

    የከተማ አስተዳደሩ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባገኘው መረጃ መሠረት ለዕጣው ብቁ የሆኑ 79 ሺህ ዜጎች ቢሆኑም ኃላፊነት የተሰጣቸው አካላት ግን በሲስተሙ ላይ 93 ሺህ ተጨማሪ ሰዎች በሕገ-ወጥ መንገድ እንዲካተቱ ማድረጋቸውን ነው ከንቲባዋ የገለጹት። ይህም ሆኖ ዝናብና ቁር ሳይበግረው ወጥቶ የመረጠ፣ በሕግ ማስከበርና ህልውና ዘመቻ ከተማውን የጠበቀ እንዲሁም የኑሮ ውድነት ሳይበግረው ቤት ለማግኘት የቆጠበን ሕዝብ ከመጭበርበር ታድገነዋል ብለዋል።

    በወቅቱ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዕጣው የሚካተቱት ሰዎች የተጣራ መረጃ ይዘን ነበር ያሉት ከንቲባዋ፥ በዕለቱ የሚያጠራጥሩ ነገሮች ስለነበሩና ጥቆማም ስለደረሰን ዕጣው በወጣ በሰዓታት ልዩነት ኮሚቴ በማዋቀር ምርምራ መጀመሩን ጠቅሰዋል።

    ቴክኖሎጂው በመረጃ መረብ ደኅንነት አስተዳደር (INSA) ያልተረጋገጠ፣ በግለሰቦች ግንኙነት ብቻ የተፃፈ ደብዳቤ እንዲሁም ማንም ሊያስተካክለው የሚችል በግለሰቦች ሲነካካ የነበረ መሆኑን አረጋግጠናል ብለዋል። በመሆኑም የአዲስ አበባን ሕዝብ የማይመጥን በጥቂት ግለሰቦች የተቀነባበረ የቴክኖሎጂ ውንብድና ስለተፈጸመ ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም የወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ሙሉ በሙሉ ውድቅ መደረጉን ገልጸዋል።

    ከንቲባዋ አክለውም፥ በጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ ማውጣት ሂደት ከሕዝቡ ጋር በማቃቃር የከተማ አስተዳደሩን እምነት ለማሳጣት ታስቦ የተዘጋጀ የፖለቲካ ሸፍጥ መሆኑን በመግለጽ፥ በዚህ ሂደት የወጣው ዕጣ ውድቅ ከመሆኑም ባሻገር በቅርቡ የመረጃ መረብ ደኅንነት አስተዳደር (INSA) የተረጋገጠ ቴክኖሎጂ በመፍጠር ዕጣ እንዲወጣ ይደረጋል ብለዋል።

    የመረጃ መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው በጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ላይ የተፈፀመው ተግባር የቴክኖሎጂ ውንብድና መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም ከዚህ ስህተት በመማር ሲስተም ሲበለጽግ ምስጢራዊ የሆኑ የቴክኖሎጂ ልማት ሂደቶችን ማለፍ ይኖርበታል ብለዋል።

    የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ላይ ችግር በመፍጠር እርምጃ የተወሰደባቸው አመራሮችና ባለሙያዎች ዝርዝር ስም ዝርዝር  ይፋ ሆኗል።

    1. ዶ/ር ሙሉቀን ሃብቱ:- ቢሮ ኃላፊ ከኃላፊነቱ የተነሳ

    በቁጥጥር ስር የዋሉ፡-

    1. አብርሀም ሰርሞሎ:- የዘርፉ ምክትል ቢሮ ኃላፊ
    2. መብራቱ ወልደኪዳን:- ዳይሬክተር
    3. ሀብታሙ ከበደ:- ሶፍትዌር ባለሙያ
    4. ዮሴፍ ሙላት:- ሶፍትዌር ባለሙያ
    5. ጌታቸው በሪሁን:- ሶፍትዌር ባለሙያ
    6. ቃሲም ከድር:- ሶፍትዌር ባለሙያ
    7. ስጦታው ግዛቸው:- ሶፍትዌሩን ያለማ
    8. ባየልኝ ረታ፡- ሶፍትዌር ተቆጣጣሪ
    9. ሚኪያስ ቶሌራ፡- የቤቶች የመረጃ ቴክኖሎጂ (IT) ባለሙያ
    10. ኩምሳ ቶላ ፡- የቤቶች የመረጃ ቴክኖሎጂ (IT) ዳይሬክተር

    ሰሞኑን የወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውድቅ ተደረገ

    Semonegna
    Keymaster

    የ2014 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከቦች ተሸለሙ

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – የ2014 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመዝጊያ እና የውድድር ዓመቱ ምርጦች ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ሰኔ 30 ቀን፥ 2014 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል። በሥነ-ሥርዓቱም ላይ በውድድር ዓመቱ በየዘርፉ ምርጥ ብቃት ያሳዩ ኮከቦች ተለይተው ተሸልመዋል።

    በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የውድድር ዓመቱ ኮከብ ተጫዋቾችን ይፋ ያደረጉት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ ሲሆኑ፥ የቅዱስ ጊዮርጊሱ ተጫዋች ጋቶች ፓኖም የውድድር ዓመቱ ኮከብ ተጫዋች በመሆን ተመርጧል።

    ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለብ (ፈረሰኞቹ) ከአራት ዓመት በኋላ ወደ ቻምፒዮንነት ክብራቸው ተመልሰው አስራ አምስተኛውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ባነሱበት በዘንድሮው የውድድር ዓመት አስደናቂ ብቃቱን በማሳየት ለክለቡ ስኬት ትልቅ ሚና የነበረው ጋቶች ፓኖም ከክብር እንግዳው እጅ የ210 ሺህ ብር እና የማስታወሻ ዋንጫ ሽልማት ተበርክቶለታል።

    በተመሳሳይ ፈረሰኞቹ ገና በውድድር ዓመቱ መጀመሪያ አካባቢ አዲስ ከቀጠሯቸው ሰርቢያዊው አሰልጣኝ ዝላትኮ ክራምፖቲች ጋር መለያየታቸውን ተከትሎ የውድድር ዓመቱን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ፈረሰኞቹን እየመራ ለቻምፒዮንነት ክብር ያበቃው አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የውድድር ዓመቱ ኮከብ አሰልጣኝ በመሆን ተመርጧል። በዚህም ከክብር እንግዳው የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አሥራት ኃይሌ የ200 ሺህ ብር እና የክብር ዋንጫውን ተቀብሏል።

    የ2014 ዓ.ም የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ግብ ጠባቂ በመባል የዋንጫ እና የአንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር ተሸላሚም የቅዱስ ጊዮርጊሱ ቻርለስ ሉክዋጎ ሆኗል። ዩጋንዳዊው የግብ ጠባቂ በተወካዩ አማካኝነት ሽልማቱን ከቀድሞ ግብ ጠባቂ በለጠ ወዳጆ እጅ ተቀብሏል። የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ተጫዋች የሆነው የሲዳማ ቡናው ተጫዋች ይገዙ ቦጋለ የዋንጫ እና የ2 መቶ ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል። ይገዙ ቦጋለ በውድድር ዓመቱ ለክለቡ ምርጥ አቋም በማሳየት አስራ ስድስት ግቦችን ከመረብ በማሳረፍ ነው ኮከብ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ ማጠናቀቅ የቻለው።

    የውድድር ዓመቱ ምርጥ ዋና ዳኛ ኃይለኢየሱስ ባዘዘው (ዶ/ር) ሆኖ ሲመረጥ፥ የ105 ሺህ ብር እና የዋንጫ ሽልማት ከቀድሞ ዳኛ ኃይለመላክ ተሰማ እጅ ተቀብሏል። በተመሳሳይ የውድድር ዓመቱ ምርጥ ረዳት ዳኛ በመሆን ትግል ግዛው የ105 ሺህ ብር እና የዋንጫ ሽልማቱን ከቀድሞ ዳኛ ይግዛው ብዙአየሁ ተቀብሏል።

    የውድድር ዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሆኖ የተመረጠው ዓመቱን በሀዋሳ ከተማ ጀምሮ በጅማ አባጅፋር ያገባደደው አልዓዛር ማርቆስ ከክብር አንግዳው የቀድሞ የፕሪምየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች አንዋር ያሲን እጅ የ105 ሺህ ብር እና የዋንጫ ሽልማቱን ተረክቧል።

    በ2014 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ለእያንዳንዳቸው ከሰባት ሚሊዮን ስድስት መቶ ዘጠና ስድስት ሺህ ሦስት መቶ ሰባ ሦስት (7,696,373) ብር እስከ አስር ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ዘጠና አራት ሺህ ስምንት መቶ አስራ ዘጠኝ (10,994,819) ብር ተበርክቶላቸዋል።

    በተጨማሪም ውድድሮቹን በማስተናገድ ላይ ለነበሩት ለአምስቱም ስታድየሞች ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ሚሊዮን ብር ተበርክቶላቸዋል።

    የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ዓመቱን በደማቅ ሁኔታ በማጠናቀቁ እንዲሁም በኮከብነት ለተሸለሙት በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ሲል ልባዊ ደስታውን ገልጿል።

    ምንጭ፦ አዲስ ዘመን ዕለታዊ ጋዜጣ

    የ2014 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከቦች ተሸለሙ ኮከብ ተጫዋች ጋቶች ፓኖም

    Semonegna
    Keymaster

    በአዲስ አበባ 25 ሺህ 491 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለነዋሪዎች በዕጣ ተላለፉ

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ14ኛ ዙር የ20/80 እና የ3ኛ ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ሐምሌ 1 ቀን፣ 2014 ዓ.ም ተካሂዷል። በዚህም በድምሩ 25 ሺህ 491 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ዕድለኞች ተለይተዋል።

    በዕለቱ የዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ አዲስ የመረጃ መያዣ እና ዕጣ ማውጫ የቴክኖሎጂ ሥርዓት በጥቅም ላይ መዋሉ ተገልጿል። ይህንን ተከትሎም የቤት ተጠቃሚዎች በአዲሱ ሲስተም በቀጥታ የወጣውን የአሸናፊዎችን ሙሉ መረጃ በ‘ኦንላይን’ ማረጋገጥ እንደሚችሉም ተገልጿል።

    በማዘጋጃ ቤት አዳራሽ በተካሄደው የዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች፣ ቤት ፈላጊዎች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

    በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለቤት ፈላጊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት በማስተላለፍ የዕጣ አወጣጥ መርሐ ግብሩን አስጀምረዋል።

    በብዙ ፈተናዎች መካከል ውስጥ ሆነንም ቢሆን ግንባታቸው የተጓተቱ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በማጠናቀቅ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ በቅተናል ነው ያሉት ከንቲባዋ።

    ከንቲባ አዳነች አቤቤ፥ “የከተማ አስተዳደራችን የከተማዋን የቤት ችግር ለመፋታት የተለያዩ የቤት ልማት አዳዲስ አማራጮችን በመዘርጋት የጀመረውን ርብርብ አጠናክሮ ይቀጥላል።” በማለት መልዕክታቸውን አስተላልገዋል።

    በተጨማሪም ከንቲባዋ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል።

    ለረጅም ዓመታት በትዕግስት ገንዘባችሁን እየቆጠባችሁ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን በጉጉት የተጠባበቃችሁ የቤት ባለእድለኞች በሙሉ፤ እንኳን ደስ አላችሁ! የከተማ አስተዳደሩ የተረከበውን በርካታ ውስብስብ ችግሮች የነበሩባቸው ቤቶች እንዲሁም በተረከብነው ከ54 ቢሊዮን ብር በላይ የባንክ እዳ ተስፋ ባለመቁረጥ ይልቁንም በቁጭትና እልህ ሌት ተቀን በመረባረብ ከ21 ቢሊየን ብር በላይ በጀት በመጠቀም ለዛሬ ውጤት በመብቃታችን መላውን የከተማ በተለይም የቤቶች ልማትና የቤቶች ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሰራተኞች፤ ኮንትራክተሮች፤የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ እና ሌሎች ለዚህ ስራ ስኬታማነት ሚናችሁን የተወጣችሁ በሙሉ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ! የከተማዋን የቤት ችግር ለመፍታት የተለያዩ የቤት ልማት አዳዲስ አማራጮችን በመዘርጋት የጀመረውን ስራ አጠናክረን የምንቀጥል ሲሆን የከተማችን ነዋሪዎች እንደ ሁልጊውም ከጎናችን በመሆን ጉዞ ከጫፍ እንድናደርስ ጥሪዬን ማስተላለፍ እወዳለሁ!

    የከተማ አስተዳደሩ ለቤቶቹ መሠረታዊ ግንባታ የሚሆን ወደ 21 ቢሊዮን ብር በማውጣት ሥራውን ሲያከናውን መቆየቱንና ለበርካቶችም የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን አክለዋል።

    በዕጣው የተካተቱት በ1997 እና በ2005 ዓ.ም ተመዝግበው እስከ የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በአማካይ ለ60 ወራት የቆጠቡ የ20/80 እና 40 በመቶ እና ከዚያ በላይ የቆጠቡ የ40/60 ቤት ፈላጊዎች ናቸው ተብሏል።

    በዚሁ መሠረት በ20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም 27 ሺህ 195 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም 52 ሺህ 599 በአጠቃላይ 79 ሺህ 794 ተመዝጋቢዎች ለዕጣ ብቁ ሆነው በዕጣ እንዲካተቱ ተደርጓል ነው የተባለው።

    በዕለቱ ዕለት ዕጣ የወጣባቸው ቤቶች የሚገኙባቸው ሳይቶችም በ40/60 መርሃ ግብር የተገነቡ ቤቶች አያት 2፣ ቦሌ በሻሌ እና ቡልቡላ ሎት 2 እንዲሁም በ20/80 መርሃ ግብር የተገነቡ ቤቶች በረከት፣ ቦሌ አራብሳ (ሳይት 3፣5፣6)፣ ወታደር፣ የካ ጣፎ፣ ጀሞ ጋራ፣ ጎሮ ሥላሴ፣ ፉሪ ሃና እና ፋኑኤል መሆናቸው ተገልጿል።

    ሐምሌ 1 ቀን፣ 2014 ዓ.ም የተላለፉ የጋራ መኖርያ ቤቶችን የተመለከቱ መረጃዎች፡-

    • አሁናዊ የአንድ ካሬ የቤት ማስተላለፊያ ዋጋ፦ የሥራ አመራር ቦርዱ ታህሳስ 5 ቀን 2014 ዓ.ም በወሰነው መሠረት አሁን በሥራ ላይ ያለው አሁናዊ የአንድ ካሬ ማስተላለፊያ ዋጋ፡-
      • 20/80 ቤት ልማት ፕሮግራም 7,997.17 ብር
      • 40/60 ቤት ልማት ፕሮግራም 11,162.97 ብር ነው።
    • ለዕጣ የቀረቡ ቤቶች የሚገኙባቸው ሳይቶች፣ የቤት ዓይነትና ብዛት በተመለከተ
      • የ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም — አያት 2፤ ቦሌ በሻሌ፤ ቡልቡላ ሎት 2 ሲሆኑ
      • የ20/80 ቤት ልማት ፕሮግራም — በረከት፣ ቦሌ አራብሳ (ሳይት 3፣ 5፣ 6)፣ ወታደር፣ የካ ጣፎ፣ ጀሞ ጋራ፣ ጎሮ ስላሴ፣ ፉሪ ሃና እና ፋኑኤል
    • በቤት ዓይነትና ብዛት ሲታይ
      • በ20/80 የቤቱ ብዛት ስቱዲዮ ፡-3318 ባለአንድ መኝታ ፡- 7171 ባለሁለት መኝታ፤- 8159 በድምሩ 18648 ናቸው።
      • በ40/60 ባለአንድ መኝታ፤- 1870 ባለሁለት መኝታ 4220 እና ባለሶስት መኝታ 753  በአጠቃላይ በድምሩ 25491 ቤቶች ናቸው።
    • በዚህ ዙር ለዕጣ የቀረቡ ቤቶች የግንባታ አፈጻጸም ሁኔታ በጋራ መኖሪያና ንግድ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ በወጣ መመሪያ ቁጥር 3/2011 በሥራ አመራር ቦርድ በማስወሰን
      • የ20/80 ከ96% በላይ፣ በ40/60 ከ87% በላይ የግንባታ አፈጻጸም ያላቸው ቤቶች ለዕጣ ቀርበዋል።
    • የዚህ ዙር የዕጣ ተሳታፊዎች ሁኔታ (የቤት ፈላጊ ተመዝጋቢ ሁኔታ) የ20/80 ነባር ተመዝጋቢዎች (1997) በመመሪያው መሠረት ዝቅተኛውን የ60 ወራት ቁጠባ መጠን ያሟሉ ለእጣ ውድድር ብቁ የሆኑ እስከ የካቲት 21 2014 ዓ.ም ድረስ እና የ40/60 40% እና ከዚያ በላይ ቁጠባ ያላቸው እስከ የካቲት 21 2014 ዓ.ም የቆጠቡ ናቸው።
    • በዕጣ ውስጥ የተካተቱት ተመዝጋቢዎችን በተመለከተ ከባንክ በተገኘው መረጃ መሠረት በ20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም 27,195 እና 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም  52,599 በአጠቃላይ 79,794 ተመዝጋቢዎች ለዕጣ ብቁ ሆነው በዚህ ዙር ዕጣ እንዲካተቱ ተደርጓል። የዕጣ ተሳታፊዎች ሁኔታ ለዕጣ ከቀረቡ የቤት ዓይነቶች አኳያ በዝርዝር ሲታይ
    • በልዩ ሁኔታ ተጠቃሚ የሚደረጉ ማህበረሰብ ክፍሎችን በተመለከተ  በመመሪያ ቁጥር 3/2011 በተገለጸው መሠረት ከ20/80 ነባር ተመዝጋቢዎች (1997) እና 40/60 ተመዝጋቢዎች ውስጥ
      • መንግሥት ሠራተኞች 20 በመቶ፣
      • ሴቶች 30 በመቶ፣
      • አካል ጉዳተኞች 5 በመቶ እና አጠቃላይ ተመዝጋቢዎች 45 በመቶ በዕጣ የቤት ተጠቃሚዎች የሚለዩ ይሆናሉ።
    • በከተማ አስተዳደሩ ፕሮጀክቱን ለመኖር ብቁ ለማድረግ ና ቤቶቹን ለማጠናቀቅ ከባንክ ቦንድ ብድር ብር 18.7 ቢሊዮን እና ለመሠረተ ልማት ግንባታ ከመደበኛ በጀት ብር 2.871 ቢሊዮን  በድምሩ ብር 21.571 ቢሊዮን በሥራ ላይ ውሏል።
    • በ20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም 27,195 እና 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም 52,599 በአጠቃላይ 79,794 ተመዝጋቢዎች ለዕጣ ብቁ ሆነው በዚህ ዙር ዕጣ እንዲካተቱ ተደርጓል።
    • በዚህ ዙር ከተላለፉ ቤቶች ውስጥ ከዚህ በፊት በማጣራት ሂደት የተገኙ ቤቶች ለልማት ተነሺ ሲስተናገዱበት ቆይተው የቀሩት ተካተዋል።
    • የቤት ልማት ፕሮግራም ከጀመረበት አንስቶ በ17 ዓመታት ውስጥ ለህብረተሰቡ ማቅረብ የተቻለው 300 ሺህ ያህል ቤቶችን ብቻ ነው።
    • የቤት ዕጣ አወጣጡ  እንደ ቅደም ተከተል ሲሆን በ20/80 ፕሮግራም  የ97 ተመዝጋቢዎች ቅድሚያ አግኝተዋል።
    • የባለ ሦስት መኝታ ቤት በተመለከተ ፕሮግራሙ ባለፈው ዙር  በቦርድ ውሳኔ በመዘጋቱ  በቀጣይ በልዩ ሁኔታ የሚስተናገዱ ይሆናል።

    የጋራ መኖሪያ ቤቶች

    ቡና ባንክ የውጭ ምንዛሪ በባንክ ያከናወኑ ደንበኞቹን ሸለመ

    • የዕጣ አሸናፊ ደንበኞች ከዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል እስከ ሞባይል ስልክ ቀፎዎች ባለቤት የሚያደርጋቸው ዕጣ ወጥቶላቸዋል

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – ቡና ባንክ ጥቁር ገበያ በኢኮኖሚው ላይ የሚያሳደረውን ተጽዕኖ ለመከላከል በማቀድ የውጭ ገንዘብን በሕጋዊ መንገድ መመንዘርን ለማበረታታት የቀረጸው “የውጭ ገንዘብ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” አስረኛ ዙር መርሃግብር በይፋ በተካሄደ የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ተጠናቋል።

    ሰኔ 23 ቀን 2014 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ በተካሄደው የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓትም 1ኛ ዕጣ የዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል አሸናፊው ቁጥር 0004079 መሆኑ ተረጋግጧል ።

    ባንኩ ላለፉት ወራት ያካሄደው ይኸው የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ መርሃግብር “በቡና ይቀበሉ፣ በቡና ይመንዝሩ፣ ከቡና ይሸለሙ” በሚል መርህ የተካሄደ ሲሆን፥ ደንበኞች ከውጭ ሀገር ከወዳጅ ዘመዶቻቸው በተለያዩ ገንዘብ ማስተላለፊያ ድርጅቶች በኩል ገንዘብ ሲላክላቸውና በቡና ባንክ በኩል ሲቀበሉ እንዲሁም የውጭ ሀገር ገንዘብ በቡና ባንክ ሲመነዝሩ ዕድለኛ የሚሆኑበት የሎተሪ መርሃግብር ነው፡፡

    በዚሁ የሎተሪ ዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ወቅት አንደኛ ዕጣ የሆነውን የ2021 ሞዴል ሱዙኪ ዲዛየር መኪና ጨምሮ ዘመናዊ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች፣ ፍሪጆች፣ የውሃ ማጣሪያዎች፣ ፍላት ስክሪን ቴሌቪዥኖችና ስማርት ስልኮች ለ30 ዕድለኞች ደርሰዋል፡፡

    ወደሀገራችን ከሚመጣው የውጭ ገንዘብ ውስጥ አብዛኛው ከመደበኛ የባንክ አገልግሎት ይልቅ በተለያየ ምክንያት ወደጥቁር ገበያ የሚገባ በመሆኑ፥ ሀገሪቱ በተደጋጋሚ ጊዜ ለሚገጥማት የውጭ ምንዛሪ እጥረት አንዱ ምክንያት ተደርጎ ሊጠቀስ ይችላል።

    የውጭ ምንዛሪ እጥረት አንድ ሀገር ለሚያስፈልጋት ማናቸውም የንግድ ልውውጥ ተግባር ከፍተኛ እንቅፋት የሚፈጥር ሲሆን፥ በዚህም ሳቢያ የሚከሰት የገቢ ንግድ መቀዛቀዝ፣ የሸቀጦች ዋጋ መጨመርን ብቻ ሳይሆን የአስፈላጊ ግብዓቶችን እጥረት በመፍጠር የኑሮ ውድነትን ያባብሳል፤ ዜጎችም በመሠረታዊ ግብዓቶች እጥረት ለችግር እንዲጋለጡ ምክንያት ይሆናል።

    የውጭ ገንዘቦች ምንዛሪና መቀበል ሂደት በባንክ ብቻ እንዲተገበርና ከጥቁር ገበያ ተጽዕኖ እንዲላቀቅ ፣ በውጤቱም ሀገርና ሕዝብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማስቻል ቡና ባንክ የበኩሉን ኃላፊነት ለመወጣት በተከታታይ ዙሮች ለውጭ ገንዘብ ተቀባዮችና መንዛሪዎች የማበረታቻ ሽልማት በማዘጋጀት የዘመቻ ሥራዎችን ሲሠራ ቆይቷል።

    እስካሁን ባንኩ በአስር ዙር ባካሄደው “የውጭ ገንዘብ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” መርሃግብር በርካቶች በሕጋዊ መንገድ የውጭ ገንዘብ እንዲመነዝሩ ከማስቻሉ ባሻገር፥ ወደጥቁር ገበያ የሚገባውን የውጭ ገንዘብ መጠን ለመቀነስ የበኩሉን አስተዋጽዖ አበርክቷል።

    ቡና ባንክ ባለፉት አስር ዙሮች ባካሄደው የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ መርሀግብር ካገኛቸው ልምዶች በመነሳት የባንኩን ደንበኞች የበለጠ ለማበረታታትና ለማትጋት አሥራ አንደኛ ዙር የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ መርሃግብሩን በቅርቡ ይጀምራል፡፡

    አንድ ሀገር በምጣኔ ሃብት ጎልብታ ዜጎቿን ተጠቃሚ ማድረግ የምትችለው ጤናማ የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት ማስፈን ስትችል ሲሆን የገንዘብ ዝውውር ደግሞ በኢኮኖሚው ውስጥ ገንቢ ሚና እየተወጣ እንዲቀጥል ለማድረግ ባንኮች የማይተካ ድርሻ አላቸው።

    ቡና ባንክም በየጊዜው በሚያካሂደው ጥናት ብዙኃኑን ሕብረተሰብ ወደባንክ ሥርዓት እንዲገባ፣ በዚህም የቁጠባ ባህሉን በማሳደግ ህይወቱን እንዲያሻሽል ለማስቻል የተለያዩ አገልግሎቶችን እየቀረጸ ለጥቅም ሲያውል ቆይቷል። በዚህም ከ1.9 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን በማፍራት ወደራዕዩ ስኬት የሚያደርገውን ግስጋሴ ቀጥሏል።

    ከ13 ሺህ በላይ በሆኑ ባለአክሲዮኖች የተቋቋመው ቡና ባንክ 343 በደረሱ ቅርንጫፎቹ በመላው ኢትዮጲያ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ የግል ባንክ ነው።

    ምንጭ፦ ቡና ባንክ

    ቡና ባንክ የውጭ ምንዛሪ በባንክ ያከናወኑ ደንበኞቹን ሸለመ

    Semonegna
    Keymaster

    ድርድሩ የሚደገፍ ቢሆንም በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል የሚደረግ እንዳይሆን ጥንቃቄ ይደረግ!
    በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
    እናት ፓርቲ

    በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውና ሁለት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት የቀረው ጦርነት ምን አልባት ኢትዮጵያ በታሪኳ ካጋጠሟት ጥፋቶችና ውድመቶች ሁሉ ከቀዳሚዎቹ ሊቆጠር የሚችል ነው። ሰዋዊ፣ ቁሳዊ፣ ሥነ ልቡናዊና ድፕሎማሲያዊ ጉዟችንን ለብዙ አስርት ዓመታት ወደኋላ መልሷልና! ፓርቲያችን ይህ ጦርነት ሊያመጣ የሚችለው ምስቅልቅልና ዳፋ አሳስቦት በእርቅና ሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ሽማግሌዎችን ከማፈላለግ ጀምሮ የተለያዩ ጥረቶች ሲያደርግ ቆይቷል። አሁንም ያ ውድመትና ‘ውረድ እንውረድ’ ዳግም እንዳይከሰት ጦርነቱን በድርድር ለመፍታት የታየው መነሳሳት ፓርቲያችን በደስታ የሚመለከተው ኩነት ነው። በእርግጥ ብንታደል በመጀመሪያ ችግሩ እንዳይከሰት ብንከላከለው፥ ከተከሰተም በኋላ የውጭ አካል ገብቶ በድርድር መልክ ከሚፈታ ይልቅ በሀገሬው ባህል በእርቅና ይቅርታ ቢፈታ በውደድን።

    ይህ ድርድር ብዙ ውስብስብ ጉዳዮችን ተሸክሞ የሚደረግ ነው፤፡ ስለሆነም ሂደቱ ከቅድመ ድርድር ጀምሮ ዘለቄታዊ መፍትሔ በሚያመጣ መልኩ ታቅዶ ካልተፈጸመ እና የውጭ ኃይሎችን “አላስፈላጊ” ጣልቃ ገብነት መከላከል ካልተቻለ “ጅብ ፈርቸ ዛፍ ብወጣ፣ ነብር ቆየኝ” ዓይነት መሆኑ አይቀሬ ነው። በማዕከላዊ መንግሥት በኩል ከአሁኑ የአካሄድ መጣረስ /procedural fallacy/ እየታየ ነው። አዎ፤ ችግሩን የፈጠረው የህወሓትና ብልጽግና የስልጣን ሽኩቻ ነው፤ የተዋጋውና ዳፋው የተረፈው ግን ሕዝብና መንግሥት በመሆኑ ወደአንድ ፓርቲ ለመጎተት የሚደረገው ጥረት አዋጭ እንዳልሆነ ግንዛቤ ውስጥ ሊገባ ይገባል። ወዲህም ፓርላማው ህወሓትን አሸባሪ በሚል ፈርጇል። ምንም እንኳን እንዳለመታደል ሆኖ የአንድ ፓርቲ ውቅርም ቢሆን ድርድሩን መፍቀድ፣ ከሽብርተኝነት መሰረዝ፣ የድርድር ነጥቦችን ማውጣት፣ ብቁና ወካይ ተደራዳሪዎችን መሰየም፣ ሂደቱን በየጊዜው መከታተል፣ ውጤቱንም ማጽደቅ ያለበት ፓርላማው ሆኖ ሳለ የፓርቲ ውሳኔ እንደመንግሥት ውሳኔ ተቆጥሮ ዘሎ የማለፍ አዝማሚያ አደገኛ ውጤት ያለው ነው ብለን እናምናለን። ስለሆነም ፓርቲያችን ለድርድሩ ውጤታማነት ቀጥሎ ያሉ ነጥቦችን ከግንዛቤ እንዲገቡ ያሳስባል።

    1. በፌደራል መንግሥት ከሚወከሉት በተጨማሪ የጦርነቱ ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ የነበሩት የአፋር እና የአማራ ክልሎች ተወካዮች የድርድር ቡድኑ አባላት መሆን እንደሚገባቸው አጽንዖት በመስጠት እናሳስባለን። በዚህ አጋጣሚ የትግራይ ሕዝብንም ስሜት በትክክል የሚያንጸባርቁ አካላት እንዲወክሉት ጥሪያችንን እናቀርባለን።
    2. የእኛን የኢትዮጵውያንን ችግር ከእኛ የተሻለ ማንም የሚረዳው እንደማይኖር በመገንዘብ በገለልተኛ አካላት (ሲቪክ ተቋማት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ምሁራን) አማካኝነት ተደራዳሪዎች በሚስማሙበት ቦታ እንዲካሄድ፤ ይህ ካልሆነ ድርድሩ በአፍሪካ ኅብረት አመካኝነት እንዲካሄድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
    3. አጠቃላይ ድርድሩ እንደመንግሥት እንዲመራና ፓርላማው ሙሉ ሂደቱን እንዲመራው፤ ውጤቱም ተግባራዊ የሚሆነው በፓርላማው ሲጸድቅ ብቻ እንዲሆን፤ ተደራዳሪዎችም የአንድ ፓርቲ ተወካዮች ብቻ ሳይሆኑ በዕውቀታቸው፣ ልምዳቸው፣ በሀገራቸው ጥቅምና ሉዓላዊነት የማይደራደሩና የፓርቲ ውክልና የሌላቸው አካላት ጭምር እንዲካተቱበት አበክረን እንጠቃይለን።
    4. ለድርድሩ ስኬታማነት ከመንግሥት ጥረት ጎን ለጎን ሕዝብ፣ ፓርቲዎች፣ መገናኛ ብዙኃን አዎንታዊ አስተዋጽዖ በማድረግ በተለይ ከሁለቱም ወገን አላስፈላጊ የአደባባይና የውስጥ እንካ ስላንትያዎች እንዲቆሙ ጥሪያችንን እናስተላለፍለን።
    5. ድርድሩ ሕዝብን የሚያቀራርብ፣ ቂምና ቁርሾን የሚሽር፣ ግልጽና ጥፋተኛን በውል የሚቀጣ፣ ከሴራና እልኸኝነት የራቀ ለሕዝብ በየጊዜው ይፋ የሚደረግ እንዲሆን እንጠይቃለን።
    6. በአጠቃላይ ወደ ድርድር የምንገባው ከጦርነት ተላቀን እንደሀገር ብዙ ለማትረፍ እንጂ ለበለጠ ኪሣራ አይደለምና ሂደቱ የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት በምንም መልኩ ለድርድር የማያቀርብ እንዲሆን አበክረን እናሳስባለን።

    በመጨረሻም ድርድርና እርቅ የሚወደድ ተግባር ነው። የምንደራደረው ግን ከ“ህወሓት” ጋር በመሆኑ የጸጥታ ኃይሉ ከመዘናጋት ይልቅ ከመቸውም ጊዜ በላይ በመናበብ፣ ከፍ ባለ ዝግጅት እና በተጠንቀቅ እንዲቆም አበክረን ማሳሰብ እንወዳለን።

    ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ
    እናት ፓርቲ (ENAT Party)
    ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም
    አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

    እናት ፓርቲ

    Semonegna
    Keymaster

    ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሁለተኛውን የምገባ ማዕከል ለማቋቋም የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከአዲስ አበባ ሴቶች ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር ለድርጅቱ ሁለተኛውን የምገባ ማዕክል (ተስፋ ብርሀን አሙዲ ቁጥር 2) ለማቋቋም የስምምነት ሰነድ ሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ተፈራርሟል።

    በከተማዋ የሚገኙ በቀን አንድ ጊዜ መመገብ ለማይችሉ ዜጎች ጤናውን የጠበቀ ምግብ እንዲያገኙ ስድስት የምገባ ማዕከላት መገንባታቸውን ከተማ አስተዳደሩን በመወከል የስምመነት ሰነድ የተፈራረሙት የአዲስ አበባ ሴቶች ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሀና የሺንጉስ ተናግረዋል።

    መንግሥት ከድርጅቶችና ግለሰቦች ጋር በመተባበር ስራዎች እያከናወነ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊዋ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከዳሽን ባንክ ኃ.የተ.የግ.ማ. ጋር በመተባበር ለከተማችን ሰባተኛ ለድርጅቱ ደግሞ ሁለተኛ የሆነ የምገባ ማዕከል ለማቋቋም አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጸዋል፤ ለዚህ የሚውል የ40 ሚልየን ብር ወጪ ለማድረግ የስምምነት ሰነድ መፈራረሙንም አስረድተዋል።

    በሚድሮክ ኢቨስትመንት ግሩፕ የኮርፖሬት ማኅበራዊ ኃላፊነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አምባሳደር አሊ ሱለይማን በበኩላቸው ሀገራችን እያስተናገደችው ያለው ማኅበራዊ ችግር በሀገሪቷ ብሎም በከተማዋ ድጋፍ የሚሹ ዜጎችን ቁጥር ከፍ አድርጎታል ብለዋል። ለዚህም ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለፈው ዓመት “ተስፋ ብርሀን አሙዲ” የተሰኘ የምገባ ማዕከል በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አቋቁሞ እየሠራ መሆኑን አስታውሰዋል።

    በዚህ ሰዓትም ቁጥር ሁለት ተስፋ ብርሀን አሙዲ የምገባ ማዕከልን በልደታ ክፍለ ከተማ በመገንባት ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ስራ መጀመሩን ገልፀዋል።

    በስምነት ሰነዱም ቢሮው የመገንቢያ ቦታ የማመቻቸት፣ ከቦታው ጋር ተያይዘው ለሚነሱ የሦስተኛ ወገን የመብት ጥያቄ ኃላፊነት ወስዶ ለማመቻቸት እና የተመጋቢ ምልመላና መረጣ የመሳሰሉ የከተማ አስተዳደሩ ኃላፊነቶችን እንደሚወጣ ተገልጿል።

    ሚድሮክ የኢንቨስትመንት ግሩፕ ከዳሽን ባንክ ኃ.የተ.የግ.ማ. ጋር በመተባበር በሚገነቡበት ቦታ ላይ የሚገኙና በዝቅተኛ ኑሮ ለሚኖሩ ስምንት አባወራዎች ስምንት የመኖሪያ ቤቶች ለመገንባት እንዲሁም ባሉበት የልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን 16 የሱቅ ቤቶች በመገንባት ለማስረከብ እንደሚሠራምዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

    ከዚህም በተጨማሪ በምገባ ማዕከሉ ቅጥር ግቢ ያለውን ክፍት ቦታ በከተማ ግብርና ለማልማትና የልማቱን ውጤትም ለተመጋቢዎች በምግነት እንዲጠቀሙ ለማድረግ እንደሚሠራ በሚድሮክ በኩል ስምምነቱን የፈረሙት አምባሳደር አሊ አረጋግጠዋል።

    በተያያዘ ዜና፥ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ (ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ/የተ/የግል ማኅበር) እና በላይነህ ክንዴ ግሩፕ (ፊቤላ ኢንዱስትሪስ ኃላ/የተ/የግል ማኅበር) በጥምረት በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ውስጥ በምትገኘው ማንኩሳ ከተማ ያስገነቡት ዘመናዊ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቆ ሥራውን ጀምሯል

    ማንኩሳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፥ ግንባታው ብቻ 43 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል፤ የወጪው 75 በመቶ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ተሸፍኗል፤ ትምህርት ቤቱን ገንብቶ ለመጨረስ የወሰድው ጊዜ ስምንት ወራትን ብቻ ሲሆን፥ ትምህርት ቤቱ 36 የመማሪያ ክፍሎች፣ ዘመናዊና የተሟሉ የአስተዳደር ህንጻዎች፣ ቤተ-መጽሐፍት፣ የተሟላ ቤተ-ሙከራ፣ የመረጃና ግንኙነት ቴክኖሎጂ (ICT)፣ ንጹህ የሴትና የወንድ መፀዳጃ ቤት ህንጻዎች እና ሌሎችም የትምህርት ግብዓቶች ተሟልተውለታል።

    ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ

    Semonegna
    Keymaster

    አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በቅድመና ድኅረ ምረቃ መርሃ ግብሮች ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ለ35ኛ ጊዜ አስመረቀ

    አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና በ2ኛ ዲግሪ መርሃ ግብሮች በመደበኛ፣ በማታ፣ በክረምት፣ በሳምንት መጨረሻ እና በተከታታይና ርቀት፣ እንዲሁም በ3ኛ ዲግሪ በመደበኛ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 2,561 ተማሪዎችን ሰኔ 25 ቀን፥ 2014 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 662ቱ ሴቶች ናቸው፡፡

    የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ የኢትዮጵያን እድገትና ክብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በሀገሪቱ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማኅበረሰብና ምሩቃን ድርሻቸው የጎላ መሆኑን ጠቅሰው ተመራቂዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የሀገር ሰላምን ለማደፍረስ የሚሰራጩ እኩይ ተልዕኮዎችን ሳያስተናግዱ በስኬት አጠናቀው ለምረቃ በመብቃታቸው አድናቆትና ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ይህን መልካም ሥነ ምግባር በማስቀጠል በሚሄዱበት የሀገራችን አካባቢዎች ሁሉ ለሰላም፣ ልማትና ዲሞክራሲ ቅድሚያ ሰጥተው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉም አደራ ብለዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በ6 ካምፓሶች በ75 የመጀመሪያ፣ በ114 የ2ኛ እና በ26 የ3ኛ ዲግሪ በአጠቃላይ ከ25 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በመደበኛና መደበኛ ባልሆኑ መርሃ ግብሮች በማስተማር ላይ ሲሆን የዛሬዎቹን ተመራቂዎች ጨምሮ ዩኒቨርሲቲው ከ72 ሺህ በላይ ምሩቃንን ማፍራቱን ፕሬዝደንቱ ገልጸዋል፡፡

    የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ጄኔራል፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ አባልና የእለቱ የክብር እንግዳ አቶ ፈጠነ ተሾመ ለተመራቂዎች ባስተላለፉት መልዕክት ትምህርት ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ እድገት ቁልፍ መሣሪያ እንዲሁም የማይከስር ሀብት መሆኑን በመገንዘብ እንዲሁም የሀገራችንን ሁለንተናዊ ለውጥ ለማረጋገጥ ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው በመረዳት ተመራቂዎች በትምህርት ቆይታቸው በንድፈ ሃሳብና በተግባር ያገኙትን ዕውቀት በሚሰማሩበት ዘርፍ ሁሉ ለዘላቂ እድገትና ሽግግር እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል፡፡

    የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ምሩቃን /አልሙናይ/ ማኅበር ፕሬዝደንት አቶ ኤርሚያስ ዓለሙ ተመራቂዎች በትምህርት ያገኙትን ዕውቀት በተግባር ውጤታማ ለማድረግ ብዙ የሚጠበቅባቸው መሆኑን ተናግረው በቀጣይ ራሳቸውን ለማሻሻል እንዲሁም ያስተማራቸውን ቤተሰብ፣ ማኅበረሰብና ሀገር ለማገልገል በታማኝነትና በትጋት እንዲሠሩ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ምሩቃን አባል በመሆን ለአካባቢው ማኅበረሰብና ለዓለም መልካም አስተዋጽኦዎችን እንዲያበረክቱ ጠይቀዋል፡፡

    በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ጄኔራልና የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ አባል፣ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችና ተጋባዥ እንግዶች የተገኙ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ዓለማየሁ ጩፋሞ እጩ ምሩቃንን ለምረቃ በማቅረብ አስመርቀዋል፡፡

    ምንጭ፦ የዩኒቨርሲቲው የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

    አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

    Semonegna
    Keymaster

    ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢዜማ መሪ ሆነው ስለተመረጡ እንኳን ደስ ያለዎት!
    አቶ አንዱዓለም አራጌ

    ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች አያሌ ኪሎ ሜትሮች አቆራርጣችሁ ለሁለት ቀናት በዚህ ታላቅ ጉባዔ ላይ የታደማችሁ፣ የተከበራችሁና የተወደዳችሁ የጉባዔ አባለት፥ አንደኛ መደበኛ ጉባዔያችንን በአማረና በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቅ በመቻላችን እንኳንም ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ ያለን ለማለት እወዳለሁ።

    ኢዜማ ለሀገራችን እንግዳ የሆነዉን የዴሞክራሲ ባህል ናሙና በጓዳዉ ሲጠነስስ ጀምሮ የፓርቲያችንን መፈረካከስ የሚሹ፣ ፓርቲያችንን የሚደግፉና የፓርቲያችን አባላት ሳይቀሩ ተመሳሳይ ድምፀት ያለዉ ሀሳብ ሲያስተላልፉ ሰምተናል፤ ኢዜማ ይፈረካከሳል የሚል። ይህ ታላቅ ጉባዔ በአካሄደዉ ጥብብ የተሞላ ዉይይት ኢዜማ ከመሰነጣጠቅ ይልቅ ተጠናክሮና ፈርጥሞ እንዲወጣ ለማድረግ በመቻሉ በድጋሚ እንኳን ያላችሁ ለማለት እወዳለሁ።

    ዴሞክራሲን አምጣ ለመዉለድ ባልቻለችዉ ሀገራችን ማህፀን የተፈጠረዉ ኢዜማ በራሱ ጓዳ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማድረግ እዉነተኛዉንና መሠረታዊዉን የዴሞክራሲ ችግኝ በመትከል ታሪክ ሠርቷል። ይህ በኢዜማ ጓዳ ዉስጥ የተፈላዉ የዴሞራሲ ችግኝ ነገ አባጣ ጎርብጣዉን የሀገራችንን የፖለቲካ መልክዐ-ምድር በመሸፈን፣ ሀገራችንን ለዘመናት እያቆረቆዛት የመጣዉን ዘመን ጠገብ የፖለቲካ ስብራት ለመፈወስ የመሠረት ድንጋይ እንዳስቀምጥን አማናለሁ።

    የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የዚህ ጉባዔ አባለት፥ አንድ ከዚህ ወጣ ወደ አለ ጉዳይ ልዉስዳችሁ። ይህን ሰሞን የምርጫ ቅስቀሳ አድርጌ ስመለስ ልጆቼ አንድ ቀልድ ይቀልዱብኝ ነበር፤ ልክ እዚህ መድረክ ላይ የተገኙ በማስመሰል የምርጫዉን ዉጤት በድራማ መልክ ያሳዩኝ ነበር –እንዲህ እያሉ “እባካችሁ ከሦስት ተወዳዳሪዎች አራተኛ ለወጣዉ ለአንዱዓለም አራጌ ሞቅ ያለ ጭብጨባ አድርጉለት” በማለት ሲቀልዱብኝ ነዉ የሰነበቱት። ዛሬ ሟርታቸዉ ሰምሮ በምርጫዉ በመሸነፌ ጥሩ አለንጋ ገዝቼ ወደ ቤት በመግባት ብስጭቴን እንደምወጣባቸዉ ቤቱ እንዲያዉቅልኝ እፈልጋለሁ። ዛሬ እነርሱን አያድርገኝ!

    ወደ ፍሬ ሀሳባችን ልመልሳችሁ፤ ኢዜማ ሲጠነስስ ሀሳብ ነበር። ባለፉት ሦስት ዓመታት ደግሞ ድርጅታዊ ዉቅሩን አስቀምጠናል። ከዚህ አንደኛ መደበኛ ጉባዔያችን ቀጥሎ ደግሞ መሬት የቆነጠጠና፣ ሰንጥቆ መዉጣት የሚችል ድርጅት እንዲሆን ስጋ የማልበስ ሥራችንን እንቀጥላለን። ግዙፉን መዋቅራችንን አስፈላጊ የሆኑ አካላዊና ርዕዮታዊ ትጥቆችን በጥንቃቄ ካስታጠቅነዉ ከፊታችን በሚመጡ ዓመታት ለኢትዮጵያችን ፖለቲካዊ ተዓምራቶችን መሥራት የሚችል ድርጅት ይሆናል ብዬ አምናለሁ። አብዛኛዎቻችን በመርከብ ተጉዘን የምናዉቅ አይመስለንም ይሆናል። ነገር ግን መለስተኛ ከተማን የሚያክል መርከብ፣ በባህር ላይ ሲንሳፈፍ ብዙዎቻችን በቴሌቪዥን መስኮት [ሳናይ] አንቀርም። ብዙዎቻችን ይህንን ግዙፍ አካል አንድ ካፒቴን ሺህ ማይሎችን እንዴት ሊያንሳፍፈዉ እንደቻለ እያሰብን እንደመም ይሆናል፤ ነገር ግን መርከቡ ሁለንተናዊ ጤንነቱ ተጠብቆ እንዲንሳፈፍ የሚያስችሉትን አያሌ ቴክኒሽያኖች እንዘነጋለን። በአንድ ቴክኒሽያን ስህተት አንድ ኤሌክራቲካል ወይንም ሜካኒካል ክፍሉ ቢበላሽ ካፒቴኑ ምንም መፈየድ እንደማይችል የምናስተዉል ስንቶቻችን እንሆን?

    ኢዜማን የሚያክል ግዙፍ ድርጅትም ያስመዘገባቸዉን በጎ ዉጤቶች ሁሉ ያስመዘገበዉ ሁለንተናቸሁን ለትግሉ ሰጥታችሁ በየአከባቢያችን ኢዜማን ባቆማችሁ ያልተዘመራለቸሁ ጀግኖች ትልቀ ተጋድሎ ጭምር እንጅ በጥቂት አመራሮች ብቻ አልመሆኑን በአንክሮ እገነዘባለሁ። እናንተን ከመሰሉ ጀግኖች ፊት ስቆም ከአክብሮት በላይ ከልቤም ዝቅ የምለዉ ለተጋድሏችሁ ካለኝ ክብር የተነሳ ነዉ። የምርጫዉንም ዉጤት የምቀበለዉ ለእናንተ ካለኝ ትልቅ አክብሮትና ከፍ ያለ ትህትና ጋር ነዉ። ከአንድ ደሃ የገበሬ ቤተሰብ ብገኝም ሁልጊዜም የነፃነትና እኩልነት ጉዳይ ሕይወቴ የሚሾርበት ምህዋር ነዉ። ዴሞክራሲ ስንል አሸንፎ መደሰት ብቻ ሳይሆን ሽንፈትን በፀጋ መቀበልንም ያካትታል። በሂደቱ ግን ከምንም በላይ ድርጅታችን አሸናፊ አድርገናል። በቅስቀሳ ወቅት ቃል እንደገባሁላችሁ ቃሌን እጠብቃለሁ። በማያሻማ ቋንቋ ፕ/ር ብርሃኑ ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት እንዲመሯችሁ መርጣችኋቸዋል፤ ምርጫችሁን ተቀብያለሁ። ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ የመርጣችኋቸዉ የእናንተ ብቻ ሳይሆኑ የተፎኮካርኳቸዉ እኔና እኔን የመረጡ የጉባዔ አባላትም መሪ መሆናቸዉን ለመግለፅ እወዳለሀ! በዚህ አጋጣሚ ፕ/ር ብርሃኑን እንኳን ደስ ያለዎት እያልኩ፥ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸዉ ከልብ እመኛለሁ!!

    የምርጫ ዘመቻ ቡድኔን፣ በገንዘብና በምክር የረዳችሁኝ ዜጎች ሁሉ ከልብ እያመሰገንኩ፥ ለሽንፈታችን ተጠያቂዉ እኔና እኔ ብቻ እንደሆኑኩ ለመግለፅ እወዳለሁ!

    ዘመኑ የፈተና ነዉ፤ ዘመኑ የትግል ነዉ። በድል የሚወጣዉ ደግሞ በጠንካራ መሠረት ላይ የቆመና አንድነቱን በብርቱ የሚያስጠብቅ ድርጅት ነዉ። ሁላችንም ከዚህ ሰዓት ጀምሮ እጅ ለእጅ በመያያዝ ትግላችንን እንድንቀጥል አደራ እላለሁ!

    ፍትህ እንደ ቀጥር ፀሐይ፣ ፍቅር እንደ ኃይለኛ ጅረት፣ ወንድማማችነት እንደ አበባ ጉንጉን በኢትዮጵያ ላይ ለዘላለም ይንገስ!!

    [caption id="attachment_48242" align="aligncenter" width="600"]ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ አንዱዓለም አራጌ ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ አንዱዓለም አራጌ[/caption]

    Semonegna
    Keymaster

    ዳሸን ባንክ ዘመናዊ የመረጃ ማዕከል አስመረቀ

    አዲስ አበባ (ሰሞነኛ) – ኢትዮጵያ የባንክ አገልግሎት ታሪክ ውስጥ የአዲስ ዘመን ጅማሮ ተደርጎ ሊወሰዱ የሚችሉትን የኤሌክትሮኒክ ክፍያ እና የሞባይል ካርድ አገልግሎቶች በማስተዋወቅ ረገድ ፈር ቀዳጅ የሆነው ዳሸን ባንክ፣ ዘመናዊና በግል የፋይናንስ ተቋም ደረጃ የመጀመሪያ የሆነውን Tier III የውሂብ/የመረጃ ማዕክል (data center) አስመረቀ።

    ዳሸን ባንክ ያለውን የመረጃ ቴክኖሎጂ (information technology /IT/) ለማሳደግ በከፍተኛ ደረጃ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነና፤ ለመረጃ ቴክኖሎጂ (IT) መሠረተ ልማትና ግንባታ ብቻ በ2014 በጀት ዓመት አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በጀት በመመደብ እየሠራ መሆኑን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ ለኢትዮጵያ ሪፖርተር ጋዜጣ አብራርተዋል። አሁን የተመረቀውን የውሂብ/የመረጃ ማዕከል (data center) ለመገንባት ባንኩ በአጠቃላይ 230 ሚሊዮን ብር ማውጣቱን አቶ አስፋው ጨምረው ገልጸዋል።

    የመረጃ ማዕከሉ ከፍተኛ ኃይል ያላቸውን ከ1,000 ያላነሱ ሰርቨሮችና ሌሎች ተያያዥ የኔትወርክ መሣሪያዎችን የማስተናገድ አቅም ያለው ነው። በጥገና ወቅትም መደበኛ የባንኩን ሥራ ሳያቋርጥ ዓመቱን ሙሉ አገልግሎት መስጠት የሚችል ነው።

    የመረጃ ማዕከሉ በአካባቢው የሚስተዋሉ የተለያዩ ክስተቶችን በመለየት ለማዕከሉ ዋና የመቆጣጠሪያ ክፍል መረጃ ማስተላለፍ የሚችል ሲሆን፣ ችግር ሲከሰትም ችግሩን በመለየት ስጋቶችን ለማስቀረት በሚችል ዓለማቀፋዊ ደረጃውን የጠበቀ ቴክኖሎጂ የተሟላ ነው።

    ይህ የመረጃ ማዕከል ዘመናዊ የባንክ አገልግሎትን ከየትኛውም ቦታ ማግኘት የሚያስችልና ባንኩ የተለያዩ አዳዲስ አገልግሎቶችን ያለምንም ችግር ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያግዘው ይሆናል። በተጨማሪም ባንኩ በዲጂታል ዘርፍ አዳዲስ አገልግሎቶችን በማስተዋወቅና የአገልግሎቱንም ደህንነትና ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ሁነኛ ሚና ይኖረዋል።

    ይህ ማዕከል የዳሸን ባንክን ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር በሥራ ላይ ለሚገኙ እና ወደ አገሪቱ የባንክ ኢንዱስትሪ ለሚቀላቀሉ የአገር ዉስጥም ሆነ የዉጭ ባንኮች እንዲሁም ለሌሎች ተቋማት አገልግሎት መስጠት የሚችል አቅም ያለዉ ነዉ።

    በመረጃ ማዕከሉ ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ፣ የባንኮች ሥራ አስፈፃሚዎች፣ የተለያዩ ድርጅት ኃላፊዎች፣ የባንኩ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የባንኩ የበላይ አመራሮች፣ ተገኝተዋል።

    ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ቀደምት እና እጅግ አትራፊ ከሆኑት የግል ባንኮች አንዱ የሆነው ዳሸን ባንክ በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከ450 በላይ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን፥ በባለፈው (2013) የበጀት ዓመት ከግብር በፊት 2.4 ቢሊየን ብር ትርፍ አስመዝግቧል። ባንኩ ከሦስት ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ሲኖሩት፤ የአሞሌ (በስልክ የባንክ አገልግሎት) ተጠቃሚቾ ቁጥርም ከ2.4 ሚሊየን በላይ ነው። የባንኩ አጠቃላይ ሀብት ደግሞ ከ94 ቢሊዮን ብር በላይ ነው።

    Semonegna
    Keymaster

    የአማራን ሕዝብ ሰቆቃ እያየ እንዳለየ፣ እየሰማ እንዳልሰማ…
    ጋዜጠኛ አበበ ገላው

    የአማራ ሕዝብ በደለኝ የሚል ካለ ማስረጃውን ይዞ ይቅረብ። አንድም ሰው አይገኝም። የኦሮሞም ይሁን የትግራይ፣ የአፋርም ሕዝብ ይሁን የሲዳማ፣ የጋምቤላም ይሁን የሶማሌ፣ የጉራጌም ይሁን የወላይታ ሕዝብ… ፈጽሞ ማንንም በድለው አያውቁም። የትኛውም ሕዝብ በጅምላ ግለሰቦችንም ይሁን ቡድኖችን ሊበድል ፈጽሞ አይችልም። ስለዚህም ነው በዓለማችን ላይ እጅግ አሰቃቂው ግፍ በተፈጸመበት አውሮፓ ናዚዎች ለፈጸሙት ወንጀል ተጠያቂ አድርጎ ጀርመኖችን እያደነ የሚገድልና የሚያፈናቅል ቡድን ኖሮ አያውቅም። በእኛም ሀገር ሞሶሎኒ በመርዝ ጋዝ ሳይቀር ለፈጸመው ግፍ ንጹኃን የጣሊያን ዜጎችን አሳደንም ይሁን ጨፍጭፈን አናውቅም። እንዲህ ዓይነቱን አስነዋሪ ወንጀል ብንሞክረውም ግፍ እንጂ ፍትሃዊ ሊሆን ፈጽሞ አይችልም።

    በእኛ ሀገር በክፋት ህወሓት በዋነኛነት ከፋፍሎ ለመግዛት እንዲያመቸው መዋቅርና ቅርጽ የሰጠውን ተረት በማንገብ በጥንታዊ ነገሥታትና መንግሥታት ለተፈጸሙ በደሎች መላውን የአማራ ሕዝብ በነፍጠኛነት ፈርጆ ከምንም የሌሉበትን ምሲኪን ድሆች በጅምላ መግደል፣ ማሳደድ፣ ማፈናቀል፣ አፍኖ መውሰድ፣ አካላዊና ስለልቦናዊ ጥቃት መሰንዘር የተለመደ ክስተት ከሆነ አርባ አመታት ተቆጥረዋል። አብዛኛው የአማራ ተወላጅ ሀገሩ እንዳይፈርስ፣ ሕዝብ ለበቀል እንዳይነሳ እና ማለቂያ የሌለው እልቂትና ውድመት እንዳይደርስ በሚል የአስተዋይነት መንፈስና ባህል የሆዱን በሆዱ ይዞ በትዕግስት ህመሙን እና ሀዘኑን አፍኖ በኢትዮጵያዊነት ጨዋነት ከየትኛውም ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር ተቻችሎና ተከባብሮ ለመኖር የሚቻለውን ሁሉ አድርጓል።

    ይሁንና አሳዛኙ ሃቅ የሕዝቡን ትዕግስት እንደ ፍርሃት የቆጠሩ እኩይ ኃይሎች የአማራን ሕዝብ በጅምላ ዘውትር ከማሸማቀቅ አልፈው የጅምላ ጭፍጨፋ፣ ግፍና ማፈናቀል ያለማቋረጥ እየፈጸሙበት ይገኛሉ። የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነትን የተረከበው “የለውጥ” ኃይልና መንግሥትም ከእነ መለስ ዜናዊ ባልተለየ ሁኔታ የአማራን ሕዝብ ሰቆቃ እያየ እንዳለየ፣ እየሰማ እንዳልሰማ… ሕዝቡ በገፍ እያለቀና እየተሰቃየ ባለስልጣናቱ ሌላው ቀርቶ የረባ የሀዘን መግለጫ፣ ማጽናኛም ይሁን የአንዲት ሰከንድ የህሊና ጸሎት ነፍገውታል።

    የዚህ ታጋሽ ሕዝብ ትግስት አልቋል። መንግሥት የሕዝብን ደህንነትና ሰላም በአግባቡ መጠበቅ ካልቻለና የዜጎቹ የጅምላ ሞት፣ ሰቆቃ መፈናቀል፣ የደም ጎርፍና እንባ ግድ የማይለው ከሆነ ሕዝቡ ሰላሙን፣ ደህነንቱና ዜግነታዊ መብቱን ሙሉ በሙሉ የሚያከብርለትና እኩልነትና አንድነትን የሚያረጋግጥለት መንግሥት እንዲመጣ አምርሮ ከመታገል ውጭ አማራጭ እንደማይኖረው ሊታወቅ ይገባል።

    ጋዜጠኛ አበበ ገላው (facebook.com/agellaw)

    [caption id="attachment_41752" align="aligncenter" width="600"] በጀርመን የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ሰላማዊ ሰልፍ ላይ[/caption]

    Semonegna
    Keymaster

    “የአማራ ባንክ አርሶ እና አርብቶ አደሮች የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር ባለአክሲዮን እንዲሆኑ አስችሏል” የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር)

    አዲስ አበባ (አሚኮ) – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) አማራ ባንክ መከፈቱንና መይፋ ሥራ መጀመሩን አስመልክተው ለባንኩ ባለድርሻ አካላት እና ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

    ዶክተር ደሴ ይናገር አማራ ባንክ አጀማመሩ ከሌሎች ባንኮች የተለየ የሚያደርገው ጉዳዮች እንዳሉት አስረድተዋል። የባንኩ አክሲዮን በስፋት በገጠርም በከተማም የተሸጠ መሆኑ፤ በባለ አክሲዮን ብዛት ትልቅ ባንክ መሆኑ ልዩ ባንክ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።

    ዶክተር ይናገር የባንኩ እውን መሆንን ያሳኩ አደራጆች እና የባንኩ የሥራ አመራር ሊመሰገኑ እንደሚገባም ነው የገለጹት። በተለይ የአማራ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ መላኩ ፋንታ በባንክ ምሥረታ ሂደት አሰልቺውን ጉዞ በተለይም ከተቀመጡት መስፈርቶች አንድ እንኳን ቢጎድል መሳካት የማይችለውን ሂደት በማሳካት ያከናወኑት ሥራ ትልቅ በመሆኑ ሊመሰገኑ ይገባል ነው ያሉት። አቶ መላኩ ከበርካታ የሕይወት ውጣውረድ እና እስር በኋላ ተቋም መርተው ለሕዝብ የሚጠቅም ባንክ ማቋቋም በመቻላቸው እሳቸው እና የሚመሩት አደራጅ እና የሥራ አመራር ቦርዱ ምሥጋና አቅርበዋል።

    በአማራ ባንክ ምሥረታ ላይ ከሀገር ውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች ያበረከቱት አስተዋጽኦ እና ባንኩ እውን እንዲሆን ያደረጉት ተሳትፎ የሚመሰገን እንደሆነም ነው ዶክተር ይናገር የገለጹት።

    በባንክ ምሥረታ በአንድ ቀን 72 ቅርንጫፍ ለመክፈት ቀን ብቻ ሳይሆን ሌሊትም ተሠርቶ ካልሆነ የማይቻል እንደሆነ የተናገሩት ዶክተር ይናገር ደሴ፥ ለዚህ ውጤት የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሄኖክ ከበደ እና የሥራ አጋሮቻቸው ያበረከቱት አስተዋጽኦ ትልቅ በመሆኑ ሊመሰገኑ እንደሚገባም ነው የተናገሩት።

    ኢትዮጵያ ውስጥ የባንክ አቅም ገና ያልተነካ በመሆኑ አሁን የተከፈተውን አማራ ባንክ ጨምሮ አዳዲስ እየተከፈቱ ካሉ ባንኮች በተጨማሪ ከተሳካ የሌሎች ሀገር ባንኮች እንዲገቡ እንደሚደረግ ነው የተናገሩት። ይህም የሀገርን ልማት በማፋጠን የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚቻል ነው ያስገነዘቡት። ባልተነካው የሀገሪቱ የንግድ እንቅስቃሴ እና የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት የአማራ ባንክ ትልቅ ሚና እንደሚጫወትም ዶክተር ይናገር ያላቸውን እምነት ተናግረዋል።

    አርሶ እና አርብቶ አደሮች የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማድረግ ባሻገር የባንክ ባለአክሲዮን እንዲሆኑ ማስቻል አስፈላጊ በመሆኑ በዚህ ረገድ አማራ ባንክ ሰፊ የአክሲዮን ሽያጭን በገጠር በመሸጥ የሚስተካከለው እንዳልተገኘም ነው የጠቆሙት። ባለአክሲዮኖቹም በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ መሆናቸው ባንኩን ልዩ እንደሚያደርገውም ተናግረዋል። ይህም ባንኩን የመላው ኢትዮጵያዊያን ባንክ እንደሚያደርገው ዶክተር ይናገር አስረድተዋል።

    አማራ ባንክ በአገልግሎት አሰጣጡ እና በፍትሐዊ አሠራሩ ልቆ ከወጣ የውጭ ባንኮች ቢገቡ እንኳን ተወዳዳሪ መሆን ስለሚችል ጠንክሮ መሥራት እንዳለበት ነው ያሳሰቡት። ባንኩ ቁጠባን በማበረታታት ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንዳለበት ገልጸዋል፤ ለባንኩ መንግሥት የሚያደርገው እገዛ እንደተጠበቀ ሆኖ ባንኩ ኢትዮጵያዊያንን ሊያገለግል እንዲችል የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን በስፋት ገቢራዊ ማድረግ እንዳለበት ነው ዶክተር ይናገር የተናገሩት። አማራ ባንክ ዘመኑ የቴክኖሎጅ በመሆኑ በቴክኖሎጅ ዘርፍ ልቆ እንደሚወጣም ያላቸውን እምነት ተናግረዋል።

    ምንጭ፦ አሚኮ

Viewing 15 results - 46 through 60 (of 730 total)